ኢሳት (ሰኔ 15 ፥ 2008) በደቡብ ክልል ኮንሶ ወረዳ በቅርቡ ከአስተዳደራዊ ጥያቄ ጋር የተነሳው ተቃውሞ ዳግም ቀጥሎ በትንሹ አንድ ነዋሪ መገደሉንና በወረዳዋ አዲስ ውጥረት መንገሱን ነዋሪዎች ለኢሳት ገለጹ። ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉት ነዋሪዎች በወረዳዋ ሰፍረው የሚገኙ የጸጥታ ሃይሎች ከአስተዳደራዊ ጥያቄ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ሰዎችን እያሰሩ እንደሆነ ከዜና ክፍላችን ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ አስረድተዋል። የጸጥታ ሃይሎች በወረዳዋ ዳግም መውሰድ የጀመሩትን ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የሰማያዊ ፓርቲ አባል የነበረችው ሜሮን አለማየሁ አርበኞች ግንቦት ሰባት ተቀላቀለች
ኢሳት (ሰኔ 15 ፥ 2008) የሰማያዊ ፓርቲ የአዲስ አበባ ም/ቤት አባል የነበረችው ወጣት ሜሮን አለማየሁ በረሃ ወርዳ አርበኞች ግንቦት ሰባት መቀላቀሏን አስታወቀች። ማክሰኞ ሰኔ 14 ቀን 2008 ዓም ለንቅናቄው ልሳን በሰጠችው ቃለ-ምልልስ እንዳስታወቀችው በሰላማዊ መንገድ ለውጥ እናመጣለን የሚለው ፅኑ እምነቷ በመክሸፉ መሳሪያ ለማንሳት መገደዷን ገልጻለች። የኢትዮጵያን በአሲስ ታጣቂዎች የደረሰባቸውን ግድያ በማውገዝ በተጠራው ሰልፍ ላይ መንግስት መወገዙን ተከትሎ ወደ እስር ቤት ...
Read More »በአዳማ ወረዳ በፈነዳ ቦምብ 6 ህጻናት ቆሰሉ
ኢሳት (ሰኔ 15 ፥ 2008) በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል አዳማ ወረዳ ውስጥ በፈነዳ ቦምብ 6 ህጻናት መቁሰላቸውን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ። ማክሰኞ ዕለት ከረፋዱ 4 ሰዓት አካባቢ በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳማ ወረዳ ዋቄ ሚኡ ቀበሌ ውስጥ በፈነዳት ቦምብ ሰለባ የሆኑት ዕድሚያቸው ከ 5 አመት እስከ 17 አመት ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ህጻናትና ታዳጊዎች መሆናቸውም ተመልክቷል። ያረጁና የተበላሹ ብረታብረትና መሰል ነገሮችን ለሚገዙትና ...
Read More »ኢትዮጵያና ኬንያ በጸጥታ ጉዳይ ላይ እየተወያዩ ነው ተባለ
ኢሳት (ሰኔ 15 ፥ 2008) ኢትዮጵያና ኬንያ በሶማሊያ አሰማርተው ያለው የሰላም አስከባሪ ሃይል ተቀናጅቶ በሚሰራበት ጉዳይ ዙሪያ የሁለቱ ሃገራት መሪዎች በኬንያዋ የወደብ ከተማ ሞምባሳ በመምከር ላይ መሆናቸው የኬንያ መገናኛ ብዙሃን ረቡዕ ዘገቡ። መቀመጫውን በዚህ በአሜሪካ ያደረገ አንድ የደህንነት ተቋም የሁለቱ ሃገራት ወታደሮች በሶማሊያ ባላቸው ተልዕኮ ተቀናጅተው ባለመስራታቸው ምክንያት በአልሻባብ ታጣቂ ሃይል ላይ ሲካሄድ የቆየው ዘመቻ ውጤት ሳያመጣ መቅረቱን መግለጹ ይታወሳል። ...
Read More »የመከላከያ መሃንዲሶችና መምህሮቻቸው ወደ ጦር ግንባር እንዲዘምቱ መደረጉን ተቃወሙ
ሰኔ ፲፭ (አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሜ/ጄኔራል ሙሉጌታ ቡሊ ቴክኒክ ኮሌጅና በደብረዘይት ወታደራዊ ምህንድስ ክፍል ውስጥ ሲሰሩ የነበሩ በርካታ ወታደራዊ መሃንዲሶች፣ የጥገና ሰራተኞች እና መምህራን የኢትዮ-ኤርትራ ግጭት ከመነሳቱ ከ2 ሳምንት በፊት ወደ ኢትዮ-ኤርትራ ድንበር መላካቸውን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ሰራተኞቹ “ከዚህ ቀደም ተደርጎ የማያውቅ ነው” በማለት ወደ ግንባር መላካቸውን ቢቃወሙም፣ የሚሰማቸው አለማግኘታቸውን ገልጸዋል። ከሁለቱ ወታደራዊ ማሰልጠኛዎች ብቻ ...
Read More »የፌደራል ፖሊስ አባላት ኮንሶ ከተማን እንደገና መቆጣጠራቸው ተሰማ
ሰኔ ፲፭ (አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሰኔ 13 ቀን 2008 ዓም ጀምሮ በኮንሶ የሚታየው ውጥረት መጨመሩን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። የፌደራል ፖሊስ አባላት ከተማዋን ከተቆጣጠሩ በሁዋላ 4 ነዋሪዎችን አፍነው መውሰዳቸው ታውቋል። ይህንን ተከትሎ ህዝቡ ተቃውሞ ያስነሳ ሲሆን፣ ወታደሮቹ በወሰዱት እርምጃ በርካታ ነዋሪዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል። ጉዳዩን በማስመልከት ጥያቄ ያቀረብንላቸው የደቡበ አሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ኅብረት ም/ሊቀመንበርና የዞኑ ጽ/ቤት ቤት ...
Read More »የተቀናሽ ሰራዊት አባላት በረንዳ ላይ እያደሩ መሆኑን ተናገሩ
ሰኔ ፲፭ (አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሌሎች አገር ዜጎች ለተቀናሽ የሰራዊት አባላት ተገቢውን እንክብካቤ ሲያደርጉ፣ በኢትዮጵያ ግን ማረፊያ ጎጆ እንኳን በማጣታቸው በረንዳ ላይ እየተጣሉ መሆኑን የተቀናሽ ሰራዊት አባላት ተናግረዋል። በባህርዳር በርካታ የተቀናሽ ሰራዊት አባላት ያሉ ሲሆን ብዙዎቹ በረንዳ ላይ ያድራሉ። “ሰራዊቱ አካሉን አጥቶና ተጎድቶ እያለ” መኖሪያ ቤት እንኳን ማግኘት አልቻለም የሚሉት የተቀናሽ ሰራዊት አባላት፣ አቤቱታቸውን የሚሰማላቸው ...
Read More »በአውስትራሊያ የአቶ አባይ ወልዱን ጠባቂ የመታው ግለሰብ ክስ ተመሰረተበት
ሰኔ ፲፭ (አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በታስማኒያ ሆባርት ከተማ የገቢ ማሰባሰብ ስራ ለመስራት በሄዱት በትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አባይ ወልዱ ጠባቂ ላይ ድብደባ አድርሰሃል በሚል አንድ ወጣት መከሰሱን ሄራልድ ሰን የተባለው የአገሪቱ ጋዜጣ መዘገቡን ተከትሎ ኢሳት ባደረገው ማጣራት ፣ ወጣቱ ላይ ክስ የመሰረተው የሶማሊያ ዜግነት ያለው አብዱ ባራክ አብዲ የተባለ የአቶ አባይ ወልዱ ጠባቂ ሲሆን፣ ፍርድ ...
Read More »የተባበበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት የኢትዮጵያን ጭፍጨፋ ጨምሮ በአራት አገራት ላይ የተወሰዱ የጅምላ ግድያዎችን እንዲያጣራ ሂውማን ራይትስ ወች ጥሪ አቀረበ።
ሰኔ ፲፭ (አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- እስካሁን ድረስ በገለልተኛ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ማጣራት መሰረት ቁጥራቸው ከ400 በላይ የሚሆኑ ንጹሃን ዜጎች መገደላቸውንና ከ10 ሽህ በላይ የሚሆኑ ሰላማዊ ዜጎች በእስርቤት ሰቆቃ ዘግናኝ ግፍ እየተፈጸመባቸው እንደሚገኙ ሂውማን ራይትስ ወች ለተ መ ድ የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት በሪፓርቱ ገልጿል። የጸጥታው ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ ትኩረት በመስጠት ካለምንም ቅድመ ሁኔታዎች ...
Read More »በደቡብ ሱዳን የተሰማራው የሰላም አስከባሪ ጦር ትችት ቀረበበት
ሰኔ ፲፭ (አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሥር የደቡብ ሱዳን የሰላም አስከባሪ ጦር ሰላማዊ ዜጎችን ከለላ መስጠት አልቻለም ተባለ። በእርስበርስ ጦርነት የምትታመሰው አዲሲቷ አገር ደቡብ ሱዳን በማላካል ከተማ ውስጥ እልቂት ሲፈፀም በስፍራው የነበሩት የሰላም አስከባሪ ጦር አባላት የሰላማዊ ዜጎችን ሕይወት ለመታደግ እንዳልቻሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምርመራ ቡድን ጥናት ሪፓርት አስታውቋል። ቁጥራቸው 48 ሽህ በላይ ...
Read More »