ዜና (ሰኔ 20 ፥ 2008) የአውሮፓ ህብረት በሶማሊያ ተሰማርተው ለሚገኙ የኢትዮጵያና የሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ሰላም አስከባሪ ወታደሮች በየወሩ ከ20ሺ ብር የሚበልጥ የኪስ ገንዘብ እንደሚከፍል አስታወቀ። ህብረቱ ለወታደሮቹ የሚሰጠው ይኸው ወርሃዊ ገንዘብ ወታድሮቹ ከመንግስታቸው ከሚከፈላቸው ገንዘብ የሚበልጥ መሆኑንና በመንግስታቸው በኩል ወታደሮቹ ኪስ የሚገባ እንደሆነ ቢቢሲ የህብረቱን መረጃ ዋቢ በማድረግ ሰኞ ዘግቧል። የአውሮፓ ህብረት እያንዳንዱ ወታደር በወር 1ሺ 28 ዶላር (ከ20ሺ ብር ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በርሃብ በተጎዱ አካባቢዎች የሚገኙ ወጣቶች “ከረሃብ ወትድርና ይሻላችሁዋል” እየተባሉ ወደ ውትድርና እንዲገቡ እየተቀሰቀሱ ነው
ሰኔ ፳ ( ሃያ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመላ አገሪቱ አዳዲስ ወጣቶችን ለመመልመል የሚደረገው ጥረት ከፍተኛ እክል ያጋጠመው መሆኑን ተከትሎ፣ የኢህአዴግ ካድሬዎች አዲስ የምልመላ ስልት ይዘው ብቅ ያሉ ሲሆን፣ በተለይ በአማራ ክልል ድርቅ ባጠቃቸው አካባቢዎች የሚገኙ ወጣቶች ለውትድርና እንዲመዘገቡ ለማድረግ ከፍተኛ ስራ እየተሰራ ነው። የክልሉ ዘጋቢያችን እንደገለጸው የብአዴን አባላት በሙሉ ሰሞኑን በወጣው የመከላከያ ሰራዊት ምልመላ ዙሪያ ወጣቱን ...
Read More »በአዲስ አበባ አትክልት ተራ “ ደረሰኝ የላችሁም” የተባሉ ነጋዴዎች ንብረታቸውን ተወረሰ
ሰኔ ፳ ( ሃያ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የከተማው መዘጋጃ በተለምዶ አትክልት ተራ ወደ ሚባለው አካባቢ በመሄድ በአነስተኛ የንግድ ስራ የተሰማሩ አትክልት ነጋዴዎችን ንብረት በመቀማት ከጥቅም ውጭ አድርጓል። አንዳንድ ነጋዴዎች እንደገለጹት የመዘጋጃ ሰራተኞች “ ደረሰኝ አልሰጣችሁም” በሚል ሽንኩርት፣ ቲማቲምና ሌሎችንም አትክልት በመቀማት እየወሰዱ በመፍጨት ከጥቅም ውጭ አድርገዋቸዋል። ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው ነጋዴዎች ህጋዊ ፈቃድ የሌላቸው ነጋዴዎች አላሰሩን አሉ ...
Read More »በረሃብ የተጎዱ ዜጎች የእርዳታ አሰጣጡን አሰራር ነቀፉ
ሰኔ ፳ ( ሃያ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ በርሃብ የተጎዱ ዜጎች የሚቀርብላቸው እርዳታ በቂ አለመሆኑና በአንዳንድ ቦታዎች እስከ 7 ሰአት ተጉዘው 14 ኪሎ እህል ለወር ይዘው እንደሚመለሱ ተናግረዋል። በምስራቅ አማራ እርዳታ የሚያከፋፍሉት በአብዛኛው የህጻናት አድን ድርጅትና የአሜሪካ ልማት ተራድኦ ( ዩ ኤስ አይ ኤድ) ሲሆኑ፣ ድጋፋቸው ያነጣጠረው በሴፍትኔት ለታቀፉ ተጎጂዎች ነው። እርዳታው በየወሩ የሚሰጥ ...
Read More »በኦጋዴን ሴቶች ላይ የተፈጸመው ወንጀል ይፋ ሆነ
ኢሳት (ሰኔ 17 ፥ 2008) በሶማሌ ክልል ከሁለት አመት በፊት የተፈጸመ የሰብዓዊ ጥሰት ወንጀልን የሚተነትነው አጭር ዘጋቢ ፊልም ተቀማጭነቱ በእንግሊዝ አገር በሆነ አንድ ግብረ ሰናይ ድርጅት ተዘጋጅቶ ለህዝብ ይፋ ሆነ። እኤአ በ2013 እና በ2014 በኬንያ የሚገኘው ደዳብ የተባለውን የስደተኞች ካምፕ የጎበኙት The Create Trust በተባለ በሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ላይ የሚሰራው ድርጅት ሰራተኞች፣ በኢትዮጵያ መንግስት የሚፈጸመውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በመሸሽ ወደኬንያ የሄዱትን የኦጋዴን ...
Read More »የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ለመስኖ ልማት ግንባታ ተጨማሪ 90 ሚሊዮን ዶላር አካባቢ መደበ
ኢሳት (ሰኔ 17 ፥ 2008) ከአመታት በፊት ከ700 ሚሊዮን ብር በላይ ለስኳር ፋብሪካዎች ግንባታ መድቦ ክፍተኛ ኪሳራ ውስጥ የገባው የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ለመስኖ ልማት ግንባታ ለማካሄድ ተጨማሪ 90 ሚሊዮን ዶላር (ወደ 2 ቢሊዮን ብር) አካባቢ መደበ። ይህንኑ የመስኖ ግንባታ ለማካሄድ ባራን ግሩፕ የተሰኘ የእስራዔል ኩባንያ ኮንትራት እንደተሰጠው ኩባንያው ይፋ አድርጓል። 61 ኪሎሜትር የሚሸፍነው የግድብ ስራ በ19ሺ ሄክታር መሬት ላይ የሚከናወን ...
Read More »በሊቦ ከምከም ወረዳ የተፈጸመውን ጥቃት በአገር ውስጥ የተደራጁ ሃይሎች የፈጸሙት መሆኑን ምንጮች ገለጹ
ሰኔ ፲፯ (አሥራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ጎንደር ሊቦ ከምከም ወረዳ ትናንት የመንግስት ተቃዋሚ ሃይሎች ባደረሱት ድንገተኛ ጥቃት 6 ፖሊሶች ሲገደሉ አንድ ብሬን መትረጌስ፣ 4 ክላሽንኮቭ ጠመንጃዎችና በርካታ ቦንቦች ተማርከዋል። ኢሳት ከአምስተርዳም ባስተላለፈው ዜና ጥቃቱን አቶ አረጋ የሚባሉ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የመንግስት ተቃዋሚ እንደፈጸሙት ቢዘግብም፣ በአካባቢው ከሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ባገኘው አስተማማኝ መረጃ፣ ጥቃቱ የተፈጸመው የተጠቀሰውን ግለሰብ ባካተተው በአካባቢው ...
Read More »የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ሲገደሉ በክብር አለመቀበራቸው በሶማሊ ክልል ከፍተኛ የስነልቦና ቀውስ እየፈጠረ ነው ተባለ
ሰኔ ፲፯ (አሥራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት በባይዶዋ፣ ሞቃዲሹና ሌሎችም የሶማሊያ ግዛቶች በአልሸባብ ተዋጊዎች የሚገደሉ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ፣ በመኪኖች እየተጫኑ በኢትዮጵያና በሶማሊያ ድንበር አካባቢ መጣላቸው በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ የስነ ልቦና ቀውስ ፈጥሯል። የበርካታ ወታደሮች አስከሬን እንደ አልባሌ ሜዳ ላይ እየተጣለ በመሆኑ የአውሬ ራት እየሆኑ ነው የሚሉት ነዋሪዎች፣ የወዳደቀ እና በአውሬ ...
Read More »መምህራን በግዳጅ የመምህራንን ቀን ሊያከብሩ ነው
ሰኔ ፲፯ (አሥራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰኔ 22 ቀን 2008 ዓም በሚከበረው በአል ላይ መምህራን በግዳጅ በቦታው ተገኝተው እንዲያከብሩ ታዘዋል። የመምራን ነጻነት ባልተከበረበት ሁኔታ፣ የመምህራንን ቀን ማክበሩ ትርጉም የለውም በሚል ተቃውሞ ያነሱ መምህራን “ ትታሰራላችሁ” የሚል ማስፈራሪያ ደርሷቸዋል። መንግስት ከመምህራን ሊደርስበት የሚችለውን ተቃውሞ በመፍራት ሰሞኑን የደሞዝ ጭማሪ እንደሚያደርግ አስታውቋል። ጭማሪው መታወጁን ተከትሎ በቤት ኪራይና በእቃዎች ላይ ዋጋ ...
Read More »በደቡብ ሱዳን የስደተኞችን መጠለያ ጠባቂ የነበሩ የኢትዮጵያ ወታደሮች ካምፓቸውን ጥለው በመሸሻቸው 40 ሰዎች ተገደሉ
ኢሳት (ሰኔ 16 ፥ 2008) በደቡብ ሱዳን የሚገኝ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያን በመጠበቅ ላይ የነበሩ የኢትዮጵያ ወታደሮች ስደተኞቹ በታጣቂዎች ሲጠቁ ካምፑን ጥለው መሄዳቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መርማሪ ቡድን አጋለጠ። የሩዋንዳ ወታደሮችም ስደተኞቹን ለመታደግ ያልተገባ ጥያቄ ማቅረባቸውም ተመልክቷል። ይሕም ለ40 ሰዎች መገደልና ለ20ሺ ሰዎች መፈናቀል ምክንያት ሆኗል። አልጀዚራ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው ድርጊቱ የተፈጽመው በዚህ በፈረንጆቹ አመት መጀመሪያ በየካቲት 2016 ...
Read More »