.የኢሳት አማርኛ ዜና

በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አጠባበቅ ላይ አሜሪካን የውጭ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ አዲስ ህግ አጸደቀ

ኢሳት (ሰኔ 21 ፥ 2008) የአሜሪካ መንግስት የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በኢትዮጵያ መንግስት የሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ ስጋቱን በተደጋጋሚ ሲገልጽ ከቆየ በኋላ S.RES432 የተሰኘ የሰብዓዊ መብቶች ህግ በምክር ቤቱ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ አማካኝነት አጸደቀ። ሰኔ 16 ቀን 2008 ዓም በሜሪካን ህግ መወሰኛ ምክር ቤት (ሴኔት) አባል በሆኑት የሜሪላንድ ግዛት ሴናተር ቤንጃሚን ካርቲን አቅራቢነት በውጭ ጉድዮች ቋሚ ኮሚቴ የጸደቀው ህግ የኢትዮጵያ ...

Read More »

የኮንሶ ወረዳ ወደዞን እንድታድግ የቀረበው ጥያቄ በደቡብ ክልል መንግስት ውድቅ ተደረገ

ኢሳት (ሰኔ 21 ፥ 2008) የኮንሶ ወረዳ ነዋሪዎች ወረዳዋ የተሻለ እድገት እንዲኖራት በማለት ወደ ዞን እንድትሻገር ሲሉ ያቀረቡትን ጥያቄ የደቡብ ክልል ምክር ቤት ውድቅ ማድረጉ ተገለጸ። በኮንሶ የተነሳው ራስን የማስተዳደር ጥያቄ በተወሰኑ ጥቂት ሰዎች የተጠየቀ እንጂ የአብዛኛው ህዝብ ጥያቄ አይደለም ያለው የደቡብ ክልል መንግስት ምክር ቤት፣ ጥያቄው ተቀባይነት የለውም ሲል በመንግስት መገናኛ ብዙሃን አስታውቋል። የኮንሶ የራስ አስተዳደር ጥያቄ አስተባባሪዎች በበኩላቸው ...

Read More »

በመኪና ተጭነው ወደ እንግሊዝ ሲጓዙ የነበሩ 28 ስደተኞች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ኢሳት (ሰኔ 21 ፥ 2008) የእንግሊዝ ፖሊስ ከኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ኤርትራ የፈለሱ 28 ስደተኞችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ። በእቃ መጫኛ መኪና ውስጥ የተገኙት እነዚህ ስደተኞች አስራ አንዱ ኤርትራውያን፣ አስሩ ሱዳናውያን  ሰባቱ ደግሞ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ዴይሊ ሜይል የተባለ በእግሊዝ አገር የሚታተመው ጋዜጣ ማክሰኞ ባወጣው ዘገባ አመልክቷል። በእቃ መጫኛ ከባድ መኪና ታጭቀው ከተገኙት ከእነዚሁ ስደተኞች መካከል ህጻናትና ሴቶች ይገኙበታል ተብሏል። ስደተኞቹ መጸዳጃ ቤት ...

Read More »

የህወሃት አባላት ያልሆኑ የደህንነት አባላት በጥርጣሬ እየታሰሩ ነው

ሰኔ ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት አባል የነበሩና በደህንነት መስሪያ ቤት ውስጥ በተለይም በሶማሊያ በሚካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ ላይ ቁልፍ ሚና ነበራቸው የተባሉ 3ቱ ነባር የደህንነት አባላትና አስተባባሪዎች ከተገደሉ በሁዋላ፣ ከግድያው ጀርባ እጃቸው ሊኖርበት ይችላል ተብለው የተጠረጠሩ የህወሃት አባላት ያልሆኑ የሌሎች ብሄረሰቦች የደህንነት አባላት እየተያዙ ነው። እስካሁን ከተያዙት መካከል አብዛኞቹ የኦሮሞ ተወላጅ ...

Read More »

ቤታቸው በህገወጥ መንገድ ይፈርስባችሁዋላ በመባላቸው ሰዎች ተቃውሞአቸውን ገለጹ

ሰኔ ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ ወረዳ 11 በአካባቢው መጠሪያ ቀርሳና ኮንቱማ በሚባሉ አካባቢዎች ቤቶችን በህገወጥ መንገድ ሰርታችሁዋል የተባሉ ነዋሪዎች፣ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ቤታቸውን እንዲያፈርሱ ካላፈረሱ ግን መንግስት እንደሚያፈርስባቸው ከተነገራቸው በሁዋላ ተቃውሞአቸውን ገልጸዋል። “አንድ የአራት እናት ልጆችና የአንድ ሳምንት አራስ የሆኑት እናት “ መሄጃ የለኝም፣ መሞቴ ነው ድረሱልኝ “ ብላለች። ልጆቼን ...

Read More »

ፍርድ ቤት እነ አቶ አግባው ሰጠኝ እንዲከላከሉ ወሰነ

ሰኔ ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 14ኛ ወንጀል ችሎት በእነ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን የክስ መዝገብ በተከሰሱ 16 ተከሳሾች ላይ ብይን የሰጠ ሲሆን፣   አቶ አግባው ሰጠኝን ጨምሮ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮነን፣  በላይነህ ሲሳይ፣  አለባቸው ማሞ፣  አወቀ ሞኝሆዴ ፣ ተስፋየ ታሪኩ፣  ቢሆነኝ አለነ፣ ተፈሪ ፈንታሁን ፣ፈረጀ ሙሉ፣  አትርሳው አስቻለው ፣ እንግዳው ...

Read More »

ከ100 በላይ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች መዘጋታቸው ተነገረ

ኢሳት (ሰኔ 20 ፥ 2008) የኢትዮጵያ ህግ ከሚፈቅደው ውጪ ሲንቀሳቀሱ ተገኝተዋል የተባሉ ከ100 በላይ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተዘጉ። ከበርካታ አመታት በተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎቶችን በመስጠት ስራ ላይ የነበሩ ድርጅቶች ከተቋቋሙበት አላማ ውጭ ሲንቀሳቀሱ እና ያለመንግስት ፈቃድ የባንክ ሂሳብ ሊከፍቱ የነበሩ ናቸው ሲል የኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ ሰኞ አስታውቋል። የዘንድሮ በጀት አመት ሪፖርቱን ያቀረበው ኤጀንሲው እርምጃ የተወሰደባቸው 108 ድርጅቶቹ የገቢ ...

Read More »

በታንዛኒያ የሞቱ የ19 ኢትዮጵያውያን ሬሳ ኢትዮጵያ ገባ

ኢሳት (ሰኔ 20 ፥ 2008) ለውዝ፣ ጥራጥሬና አሳ በጫነ የጭነት መኪና ተጭቀው ከታንዛኒያ ወደ ዛምቢያ ለመሻገር ከሞከሩ 95 ኢትዮጵያውያን 19ኙ ህይወታቸው ማለፉ ሲታወስ፣ የ19ኙም አስከሬን ኢትዮጵያ መግባቱ ታውቋል። መድረሻቸውን ደቡብ አፍሪካ ለማድረግ ከኢትዮጵያ ተነስተው ኬንያ አቋርጠው ታንዛኒያ የደረሱት ኢትዮጵያውያን ዛምቢያ ላይ ህይወታቸው ያለፈው በሳምንቱ መጨረሻ ነበር። በረሃ አቋርጠው ሲጓዙ ታፍነው ከሞቱን 19 ኢትዮጵያውያን በተጨማሪ፣ ሌሎች 76 ኢትዮጵያውየን በመኪና ውስጥ የነበሩ ...

Read More »

በሶማሊያ በቅርቡ የተፈጸመውን ጥቃት ሳይጨምር ከ20 በላይ የኢትዮጵያ ወታደሮች መገደላቸው ተነገረ

ዜና (ሰኔ 20 ፥ 2008) በተያዘው አመት ብቻ ሰሞኑን በአልሸባብ የተፈጸመውን ጥቃት ሳይጨምር ከ20 የሚበልጡ የኢትዮጵያ ወታደሮች በሶማሊያ መሞታቸውን ቢቢሲ ዘገበ። በሚያዚያ ወር በቤይ ግዛት በደረሰ የፍንዳታ አደጋ ስድስት ኢትዮጵያውያን እንዲሁም በጥር ወር 15 የኢትዮጵያ ወታደሮች በታችኛው ሸበሌ ግዛት በተካሄደ ግጭት መሞታቸውን የዜና አውታሩ አመልክቷል። በተያዘው ወር መግቢያ ላይ በአንድ የኢትዮጵያ ወታደራዊ ማዘዣ ጣቢያ ላይ በተፈጸመ ጥቃት ወደ 160 የሚደርሱ ...

Read More »

እነ አቶ በቀለ ገርባ ጨለማ ቤት ታስረው ተፅዕኖ እየተደረገባቸው መሆኑ ተገለጸ

ኢሳት (ሰኔ 20 ፥ 2008) በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ሰኞ ዕለት የቀረቡት እነ አቶ በቀለ ገርባ አሁንም በጨለማ ቤት እንደሚገኙና ተፅዕኖች እንደቀጠሉባቸው ተገለጸ። ፍርድ ቤቱም ክሱ በሽብር ያስከስሳል አያስከስስም በሚል ውሳኔ ለመስጠት ከሃምሌ 25 ቀጠሮ በመስጠት መነሳቱም ታውቋል። በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰን ከመንፈቅ በላይ የቀጠለውን ተቃውሞ ተከትሎ በቁጥጥር ስር የዋሉት የኦፌኮ ምክትል ፕሬዚደንት አቶ በቀለ ገርባና ሌሎች አመራሮች ከግንቦት ...

Read More »