ኢሳት (ሰኔ 27 ፥ 2008) የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን አሜሪካ 33ኛ ዓመት በዓል በካናዳ ቶሮንቶ በድምቀት ተከፈተ። ከተለያዩ የካናዳ ግዛቶች እንዲሁም ከዩኤስ አሜሪካ የተጓዙ ኢትዮጵያውያን ጭምር እንደታደሙበት በተገለጸው በዚህ ዓመታዊ የኢትዮጵያውያን በዓል፣ ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ከኢትዮጵያ ጭምር የተጓዙ ኢትዮጵያውያን በዝግጅቱ መሳተፋቸውን መረዳት ተችሏል። የኢትዮጵያውያን የስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ ፕሬዚደንት አቶ ጌታቸው ተስፋዬ ይህ ታላቅ የኢትዮጵያውያን መሰባሰቢያ መድረክ፣ “የኢትዮጵያውያን ሰንደቅ አላማ በባዕድ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ኢትዮጵያዊ አርሶአደሮች 5 የሱዳን ወታደሮችን ገደሉ
በሰሜን ጎንደር ዞን በታች አርማጭሆ ወረዳ በሲናር በረሃ የኢትዮጵያን የእርሻ መሬት ለመውሰድ በተንቀሳቀሱ የሱዳን ወታደሮች ላይ ተኩስ የከፈቱት ኢትዮጵያዊ አርሶአደሮች 5 የሱዳን ወታደሮችን ገድለዋል። ሰኔ 25 ቀን 2008 ዓም የሱዳን ወታደሮች የጓንግን ወንዝ ተሻግረውና አንድ የእርሻ ካም አቃጥለው ጦርነት ሲከፍቱ ፣ በተለይ ጎዳና አምዴ የተባለው ወ ጣት አርሶአደር እና አብረውት የነበሩት 5 የሱዳን ወታደሮችን ገድለው 3 ክላሽንኮቭ እና አንድ መትረጊስ ...
Read More »የኮንሶ ህዝብ ጥያቄ ውድቅ መደረጉን ተከትሎ በአካባቢው ውጥረት ሰፍኗል
የደቡብ ክልል የብሄረሰቦች ምክር ቤት ሰኔ 23 ቀን 2008 ዓም የኮንሶ ህዝብ የራስ አስተዳደር ጥያቄ ውድቅ መደረጉን የሚግልጽ ደብዳቤ መጻፉን ተከትሎ በአካባቢው ውጥረት መንገሱን ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። ምክር ቤቱ በደብዳቤው “ የክልሉ ህገመንግስት አንቀጽ 59 ንኡስ አንቀጽ 3 እና የብሄረሰቦች ምክር ቤትን ለማጠናከር ስልጣንና ተግባሩን ለመዘርዘር የወጣው አዋጅ ቁጥር 60/95 መሰረት አጠቃላይ የጥያቄው ይዘትና ምክንያቶችን መርምሮ በማየት የኮንሶ ህዝብ መሰረታዊና ...
Read More »በአዲስ አበባ ቤታቸው የፈረሰባቸውን ሰዎች አሳዛኝ ህይወት የሚያሳዩ ፎቶግራፎች እየወጡ ነው
በወረዳ አንድ የሁለት ፖሊሶችንና የአንድ ወረዳ አስተዳዳሪን ህይወት ጨምሮ፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ዜጎች የተገደሉትን የቤት ማፍረስ ዘመቻ ለመደበቅ መንግስት ጥረት ቢያደርግም ቤታቸው የፈረሰባቸውን ዜጎች ህይወት የሚያሳዩ ፎቶዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተለቀቁ ነው። የፌደራል ፖሊሶች አካባቢውን አጥረው ምንም ሰው ወደ ውስጥ እንዳይገባ ጥረት ሲያደርጉ ሰንብተዋል። ይህን ተከትሎም አሽከርካሪዎች በመንገድ መጨናነቅ ሲቸገሩ ሰንብቷል። ነዋሪዎች እንደሚሉት መስተዳድሩ ድርጊቱ እንዳይታወቅበት ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። ሆኖም የመስተዳድሩ ...
Read More »በገላና ወረዳ አንድ የሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪ ተደበደበ
በሁሌ ቦራ ዞን በገላና ወረዳ ሜጄ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑትና ሰማያዊ ፓርቲን በመወከል ባለፈው ግንቦት ወር ምርጫ እጩ ተወዳዳሪ የነበሩት አቶ ደስታ ቁጤ ከምሽቱ አንድ ሰአት ላይ በተፈጸመባቸው ድብደባ በእግሮቻቸው ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶአቸው በህክምና እየተረዱ ነው። ማንነታቸው ያልታወቁት ግለሰቦች ጨለማን ተገን አድርገው ግለሰቡን መደብዳበቸውንና ከዚህ ቀደም ከደህንነቶች ማስፈራሪያ ሲደርሰው እንደነበር እንደነገሯቸው የዞኑ የሰማያዊ ፓርቲ ተወካይ አቶ ጌታቸው በቀለ ለኢሳት ተናግረዋል
Read More »በአዲስ አበባ ከተማና አካባቢው ዜጎችን ከቤት ንብረታቸው የማፈናቀል ድርጊት በአስቸኳይ እንዲቆም ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ሰመጉ) ጠየቀ
ኢሳት (ሰኔ 24 ፥ 2008) በአዲስ አበባ ከተማና አካባቢው ዜጎችን ከቤት ንብረታቸው የማፈናቀል ድርጊት በአስቸኳይ እንዲቆም ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ሰመጉ) ጠየቀ። ዜጎች ለረጅም ዓመታት በይዞታነት ግብር ሲከፍሉበት ከቆዩበት ቦታ “ህገወጥ ናችሁ” ብሎ ማፈናቀል በምንም መልኩ ተቀባይነት ያለው ድርጊት አለመሆኑን ድርጅቱ ባወጣው አስቸኳይ ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል። በቦሌ ክ/ከተማ ወረገኑ የሚባል አካባቢን ጨምሮ በተለያዩ ክፍለከተሞችና በአዲስ አበባ ከተማ ዳርቻ ለረጅም ጊዜ ከኖሩበት ...
Read More »በአቶ ሃብታሙ አያሌው ላይ በፍርድ ቤት የተጣለበት እገዳ እንዲነሳ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጥሪ አቀረበ
ኢሳት (ሰኔ 24 ፥ 2008) በፍርድ ቤት ከኢትዮጵያ እንዳይወጣ እገዳ ተጥሎበት የሚገኘውና በጽኑ ህመም ላይ የሚገኘው የአንድነት ፓርት አመራር አቶ ሃብታሙ አያሌው የተጣለበት እገዳ እንዲነሳለት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጥሪውን አቅረበ። የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ለጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ በላከው የጽሁፍ መልዕክት አቶ ሃብታሙ ከሰብዓዊ መብት አንጻር እገዳው በአስቸኳይ ሊነሳለት የሚገባ እንደሆነ አመልክቷል። በእስር ቤት ቆያታው የተለያዩ ስቃዮች በአቶ ሃብታሙ አያሌው ...
Read More »በአወዳይ በተነሳው ተቃውሞ ህጻናትን ጨምሮ በትንሹ 4 ሰዎች ተገደሉ
ሰኔ ፳፬ ( ሃያ አራት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በምስራቅ ሃረርጌ በአወዳይ ከተማ የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የወረዳው አስተዳዳሪ በከፈተው ተኩስ ሁለት ህጻናት እና አንድ ጎልማሳ ተገድለዋል። ነዋሪዎች ማምሻውን ለኢሳት እንደገለጹት ከሆነ የሟቾች ቁጥር 7 ድርሷል። ኢብራሂም ሙሜ የሚባል ባለ ጸጉር ቤት እና አህመድ አልዬ የሚባል ባለሞባይል ቤት አሊ መሰራ ህንጻ እና አዋሽ ባንክ መሃል የሚገኘው ቤታቸው ...
Read More »ከቤት ማፍረስ ጋር በተያያዘ የሚገደሉ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ ነው
ሰኔ ፳፬ ( ሃያ አራት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ ወረዳ አንድ አካባቢ በህገወጥ መንገድ ተሰርተዋል የተባሉ ቤቶችን ለማፍረስ የተጀመረው ዘመቻ እንደቀጠለ ባለበት በዚህ ወቅት፣ በምሽት እየታደኑ የሚገደሉ ሰዎች ቁጥር መጨመሩንም የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። ነዋሪዎች እንደሚሉት ትናንት ምሽት ፌደራል ፖሊሶች አንድ ቄስ ገድለዋል። እስካሁን ለማረጋጋጥ ባንችልም ሌላም አንድ ቄስ ክፉኛ ተጎድተው በሞትና በህይወት መካከል እንደነበሩ ነዋሪዎች ...
Read More »በባህርዳር ከተማ ትልቁ የገበያ ስፍራ የተነሳው ቃጠሎን ተከትሎ ህዝቡ ጣቱን በመስተዳድሩ ላይ እየቀሰረ ነው
ሰኔ ፳፬ ( ሃያ አራት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰኔ 22 ከሌሊቱ በ6፡00ሰዓት በባህርዳር ከተማ ትልቁ ገበያ በተነሳው የእሳት ቃጠሎ የጎማ መደብሮች፣የቤት ዕቃ መሸጫዎች የባልትና ውጤት አቅራቢዎችና በርካታ የጌጣጌጥ መሸጫ ሱቆች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል፡፡ የአካበቢው ህብረተሰብ የአሁኑ ቃጠሎ ከአሁን በፊት በተደጋጋሚ የገበያ ቦታዎችን አስለቅቆ ለባለሃብቱ ለመስጠት ሲደረግ የነበረው ሴራ አንድ አካል ነው ይላሉ ፡፡ ከአመታት በፊት በደሮ ...
Read More »