ሐምሌ ፩( አንድ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሃምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ በሽብር ወንጀል ክስ ተመስርቶበት ላለፉት ሁለት ዓመታት በእስር ሲንገላታ የነበረው የአረና ትግራይ ፓርቲ አባል መምህር አብረሃ ደስታ ከእስር ተፈቷል። አቶ አብርሃ ደስታ ነሀሴ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. በከፍተኛው ፍርድ ቤት ከተከሰሰበት የሽብር ወንጀል ነጻ የተባለ ቢሆንም፣ ችሎት ተዳፍረሃል ተብሎ ለተጨማሪ ጊዜያት በእስር እንዲቆይ ተደርጓል። ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የመምህራን ሽልማት ቅሬታ አስነሳ
ሐምሌ ፩( አንድ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባህርዳር ሙሉዓለም አዳራሽ ሃምሌ 30/ 08 ዓ.ም በተደረገው የምስጉን መምህራን ሽልማትአሰጣጥ ላይ የተገኙ መምህራን፣ ሽልማቱ የተሰጠው በብአዴን ፓርቲ ውስጥ አባል በመሆን አስተዋጽዎ ላበረከቱት እንጅ በሙያቸው ላገለገሉት አይደለም በማለት ቅሬታቸውን ገልጸዋል። መምህራኑ እንደተናገሩት ሽልማት የተሰጣቸው በስራቸው ታታሪ ለሆኑ መምህራን ሳይሆን በገዥው ፓርቲ ውስጥ አባል በመሆን ለተንቀሳቀሱ መምህራን ብቻ ነው። በተካሄደው የሽልማት አሰጣጥ ...
Read More »የአፍሪካ ኅብረት የሰላም አስከባሪ ጦር አሚሶም በሶማሊያ ቆይታውን አራዘመ ውሳኔውን ሂውማን ራይትስ ወች አወገዘ
ሐምሌ ፩( አንድ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሶማሊያ ዘላቂ ሰላም ያመጣል ተብሎ ወደ ሶማሊያ ያመራው የአፍሪካ ኅብረት የሰላም አስከባሪ ጦር አሚሶም በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ በአገሪቱ ሰላምና መረጋጋት ማስፈን እንዳልቻለ ተገልጿል። የኅብረቱ ጦር ከተለያዩ አገራት የተውጣጡ 22 ሽህ ሰራዊቶች ቢኖሩትም እስከ 2018 እ.ኤ.አ. በአገሪቱ ተልእኮውን አጠናቆ ለሶማሊያ ጦር አስረክቦ ይወጣል ሲባል የቆየ ቢሆንም ከአልሸባብ ተዋጊዎች በገጠሙት የተለያዩ ...
Read More »የአለም አቀፍ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ የተከሰተውን ረሃብ በቸልታ ተመልክቶታል ተባለ
ኢሳት (ሰኔ 30 ፥ 2008) በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በረሃብ እየተሰቃዩ ባሉበት በአሁኑ ወቅት፣ የአለም አቀፍ ማህበረሰብ በሌሎች ትናንሽ ጉዳዮች ላይ ማተኮሩ አግባብ አይደለም ሲሉ አንድ የተባበሩት መንግስታት መልዕከተኛ ወቀሳ አቀረቡ። የቀድሞ የአየርላንድ ፕሬዚደንት ሜሪ ሮቢንሰን ይህንን የተናገሩት ኢትዮጵያ ውስጥ ስለተከሰተው ድርቁ ማብራሪያ ከተሰጣቸው በኋላ መሆኑ ታውቋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መልዕከተኛ ሚስ ሜሪ ሮቢንሰን ለመገናኛ ብዙሃን አንደተናገሩት፣ በአሁኑ ሰዓት የአለም አቀፍ ...
Read More »የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የስኳር ፋብሪካዎች ግንባታ ችግሮችን ለመመርመር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ምክክርን ሊያካሄድ ነው ተባለ
ኢሳት (ሰኔ 30 ፥ 2008) በመንግስት ላይ ከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራ ያስከተሉትን የስኳር ፋብሪካዎች ግንባታ ጉዳይ ለመመርመር የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ፋብሪካዎቹን ለመገንባት ከተመረጡ አካላት ጋር ምክክርን ሊያካሄድ መሆኑን ገለጠ። በ77 ቢሊዮን ብር ይገነባሉ የተባሉትና ከሶስት አመት በፊት ወደ ስራ ይገባሉ ተብለው ይጠበቁ የነበሩት ፋብሪካዎች ያሉበት ደረጃ እጅግ ዝቅተኛ መሆኑን ሚኒስትሩ ለፓርላማ አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ሃላፊዎች ፋብሪካዎቹን ለመገንባት ሃላፊነት ተሰጥቶት ...
Read More »አቶ ኦባንግ ሜቶ በዜጎች ላይ የሚፈጸመውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት አስመልክቶ ለዶ/ር ቴዎድሮስ ደብዳቤ ጻፉ
ኢሳት (ሰኔ 30 ፥ 2008) ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ ያጋራ ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ ኦባንግ ሜቶ በአዲስ አበባ እየፈረሱ ባሉ ቤቶች ስለተፈናቀሉ ከ20ሺ በላይ ዜጎች እና በአንድነት ፓርቲ አመራር ሃብታሙ አያሌው ላይ የሚፈጸመውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት አስመልክተው ለዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ግልጽ ደብዳቤ ጻፉ። በሰኔ ወር ውስጥ በላፍቶ ክፍለ ከተማ ቀርሳ፣ ኮንቶማ ማንጎ ወረገኑ እና ሃናማሪያም ተብለው ከሚጠሩ መንደሮች ከህጻናት ጀምሮ እድሚያቸው 93 ዓመት ...
Read More »የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት አቶ ሃብታሙ አያሌው የውጭ አገር ህክምና ጥያቄን በተመለከተ ውሳኔ ለመስጠት የተሟላ መረጃ አልቀረበልኝም አለ
ኢሳት (ሰኔ 30 ፥ 2008) የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፅኑ ህመም ላይ የሚገኙት አቶ ሃብታሙ አያሌው ከሃገር ውጭ እንዲታከሙ የቀረበለትን ጥያቄ የተሟላ አይደለም ሲል ሃሙስ ምላሽ ሰጠ። ከቀናት በፊት በጉዳዩ ላይ ውሳኔን ይሰጣል ተብሎ የነበረው ፍርድ ቤት የቀረበለት ማስረጃ በቦርድ የተደገፈ አይደለም ሲል ማስረጃውን አስተካክሎ እንዲቀርብለት ምላሽን መስጠቱን ጉዳዩን እየተከታተሉ የሚገኙት የአቶ ሃብታሙ ቤተሰቦች ለኢሳት አስታውቀዋል። ከሁለት ሳምንት በፊት ጀምሮ ...
Read More »ሁለት ቤተክርስቲያኖችን ለማፍረስ የተደረገው ሙከራ የህዝብ ቁጣ ቀስቅሷል
ባለፈው ሳምንት በአዲስ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቀጣና 01 መንደር 06 በተለምዶ አጠራር ቀርሳና ኮንቶማ በሚባለው አካባቢ የሚገኙ ሁለት ቤተክርስቲያኖችን ለማፍረስ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ህዝቡ እየተቃወመ ነው። ባለፈው ሳምንት ኡራኤል ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ ሙከራ ሲደረግ ህዝቡ ባስነሳው ተቃውሞ ቤተክርስቲያኑ እስካሁን ሳይፈርስ ቆይቷል። ከሶስት ቀናት በሁዋላ ደግሞ የቤተክርስቲያኑ ቄስ በፌደራል ፖሊስ ተገድለዋል። አፍራሽ ግብረሃይሎች የጸበል ቦታውን ካፈረሱ በሁዋላ ፣ ሙሉውን ቤተከርስቲያን ለማፍረስ ...
Read More »ኢትዮጵያን በመጎብኘት ላይ ያሉት የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ናትኒያሁ መንግስታቸው በሽህዎች የሚቆጥሩ ኢትዮጵያውያን ይሁዲዎችን እስራኤል ሀገር ወደሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ለመውሰድ እንደሚፈልግ ገለጹ።
እንደ ቢቢሲ ዘገባ አያቶቻቸውና አባቶቻቸው አይሁዳውያን እንደሆኑ የሚያምኑ በትንሹ 9ሺህ ያህል ኢትዮጵያውያን ወደ እስራኤል ለመጓዝ ለዓመታት እየጠበቁ ይገኛሉ። ናትኒያሁ ከኢትዮጵያው አቻቸው ጋር በሰጡት መግለጫ የአይሁድ ኢትዮጵያኑ ጉዞ በቅርቡ እንደሚከናወን ገልጸዋል። ይሁንና መቼ እንደሚሆን ትክክለኛውን የጊዜ ሰሌዳ አልተጠቀሱም። “አይሁድ ኢትዮጵያውያንን ወደ እስራኤል የመመለሱን ጉዳይ እየሰራንበት ነው፤ያን ለማድረግ ቁርጠኝነቱ አለን። በቤተሰብ መቀላቀል ሂደቱ የሚያስፈልጉትን ነገሮች ሁሉ እያሟላን ነው። ይህ የሚሆነው ለወደፊት አይደለም።በወቅቱ ...
Read More »የተመድ የምግብና የእርሻ ክፍል በጎርፍ ለተጎዱት ዜጎች ተጨማሪ ገንዘብ ጠየቀ
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምግብ እና የእርሻ ክፍል በቅርቡ በተከሰተው ረሃብ የተጎዱ ዜጎች ሳያገግሙ በድጋሜ በጎርፍ በመጠቃታቸው ለመስከረም ወር ተጨማሪ የ3 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ጠይቋል። ድርጅቱ የኢትዮጵያን የጎርፍ አደጋ መከላከል ግብረሃይልን ጠቅሶ እንደዘገበው በጎርፉ ምክንያት 690 ሺ ተፈናቅለዋል። 55 ሺ ሄክታር መሬትም በጎርፍ መጥለቅለቁን ድርጅቱ አስታውቋል። በድርቁ የተጎዱ ዜጎች ወደ ነበሩበት ቦታ ለመመለስ በትንሹ ሁለት አመት ያስፈልጋቸዋል። ድርጅቱ የውሃ አቅርቦትን ለመጨመር ...
Read More »