ኢሳት (ሃምሌ 5 ፥ 2008) በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች ከሚገኙ 35ሺ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል ወደ 21ሺ የሚጠጉት የውሃ አገልግሎት የሌላቸው መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይፋ አደረገ። በተለይ በድርቅ በተጎዱ ክልሎች ውስጥ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች የውሃ አገልግሎት የማያገኙ በመሆኑ ትምህርታቸውን የሚያቋርጡ ተማሪዎች እየጨመረ እንደሚሄድ ምክንያት መሆኑ ታውቋል። ድርጅቱ ከተለያዩ አለም-አቀፍ ተቋማት ጋር በመተባበር ትምህርት ቤቶቹ የውሃ አገልግሎት እንዲያገኙ ጥረትን ቢያደርጉም ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በአዲስ አበባ በተከሰተው አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት በሽታ 6 ሰዎች ሞቱ
ኢሳት (ሃምሌ 5 ፥ 2008) በቅርቡ በአዲስ አበባ ከተማ መሰራጨት በጀመረው የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት (ኮሌራ) በሽታ እስካሁን ድረስ በትንሹ ስድስት ሰዎች ሞቱ። በሁሉም ክፍለ-ከተሞች በመሰራጨት ላይ ባለው በዚሁ ወረርሽን እስከ 2ሺ የሚደርሱ ነዋሪዎች በበሽታው መያዛቸውንና በሽታውን ለመቆጣጠር እየተደረገ ያለው ጥረት አልባት አለማምጣቱን በሃገር ውስጥ ያሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በበሽታው የተያዙ በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች በተለያዩ ጊዜያት የኮሌራ በሽታ መከላከያ ጣቢያዎች ህክምና ...
Read More »በሰሜን ጎንደር መንግስት ከታጣቂ ሃይሎች ጋር እየተታኮሰ እንደሆነ ገለጸ
ኢሳት (ሃምሌ 5 ፥ 2008) መቀመጫቸውን በኤርትራ ካደረጉ ሃይሎች ጋር ግንኙነት ኣላቸው የተባሉ ታጣቂዎች በሰሜን ጎንደርና ትግራይ ክልሎች ከመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ጋር የተኩስ ልውውጥ በማድረግ ላይ መሆናቸውን መንግስት ማክሰኞ ምሽት ገልጸ። ታጣቂዎች ሴቶችንና ህጻናትን ከለላ በማድረግ ከመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ጋር ተኩስ በመክፈትና ቦንብ በመወርወር ጉዳት አድርሰዋል ሲል የብሄራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎትና የፌዴራል ፖሊስ የጋራ የጸረ-ሽብር ግብረሃይል አስታውቋል። ግብረ ሃይሉ በታጣቂ ...
Read More »የወልቃይት ጥያቄ የሚመሩ የኮሚቴ አባላትን ለመያዝ በተወሰደው ዕርምጃ የሰላማዊ ሰው ህይወት ጠፋ
ኢሳት (ሃምሌ 5 ፥ 2008) የወልቃይት የማንነት ጥያቄን የሚመሩ የኮሜቴ አባላትን ለማሰር በተወስደ እርምጃ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ከፍተኛ ግጭት አስከተለ። ሰላማዊ ሰዎችም የተገደሉ ሲሆን፣ ከህዝብ ወገን በተወሰደ አጸፋ የጸጥታ ሃይሎች መገደላቸውም ታውቋል። የኮሚቴ አባል የሆኑት ኮሎኔል ደመቀ ዘውዴ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ተከበዋል። መንግስት በዕለቱ ማምሻውን በሰጠው መግለጫ ሶስት የልዩ ሃይል ፖሊሶች ሲገደሉ፣ 5 መቁሰላቸው አስታውቋል። አንድ ሰላማዊ ሰው መገደሉንም ...
Read More »ጎንደር በተኩስ እየተናጠች ነው
ኢሳት (ሃምሌ 5 ፥ 2008) በጎንደር ከተማ የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ቁጣ የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ኤፈርት ንብረት የሆነው ሰላም ባስን ጨምሮ የንግድ ተቋማት መቃጠላቸው ተሰምቷል። ኮሎኔል ደመቀ ዘውዴ እጅ አልሰጥም በማለት መታኮሳቸው የታወቀ ሲሆን፣ ከጎንደር ከተማና አካባቢም በርካታ ነዋሪዎች ዕርሳቸውን ለመታደግ ተንቀሳቅሰዋል። በከተማዋ ሙሉ በሙሉ የንግድ እንቅስቃሴ ሆነ ስራ የቆመ ሲሆን፣ ኮ/ል ደመቀ ዘውዴን ለመታደግ የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆች በ6 አውቶቡሶች ወደጎንደር ...
Read More »በኦሮሚያ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ አሁንም ዜጎች በመንግስት ሃይሎች እየተገደሉ ነው
ኢሳት (ሃምሌ 4 ፥ 2008) ከወራት በፊት ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን መስፋፋት ጋር በተገናኘ በኦሮሚያ ክልል የተቃውሞ መነሻ በነበረችዉ ጊንጪ ከተማ ዳግም ተቃውሞ ተቀስቅሶ በትንሹ አንድ የ9ኛ ክፍል ተማሪ ተገደለ። ሰሞኑን የከተማዋ ነዋሪዎች በፅጥታ ሀይሎች ቀጥሎ ያለን የሀይል ድርጊት በመቃወም ወደ አደባባይ በወጡ በጊንጪ ከተማ ሰፍረዉ የሚገኙ የፌደራል የፅጥታ ሀይሎች በነዋሪዉ ላይ ተኩስ መክፈታቸዉን እማኞች ለኢሳት ገልፅዋል። የፅጥታ ሀይሎች በወሰዱት ...
Read More »የኢትዮጵያ መንግስት ማህበራዊ መገኛኛ ብዙሃን ድረ-ገጾችን መዝጋቱን አስታወቀ
ኢሳት (ሃምሌ 4 ፥ 2008) ሰኞ በመላዉ ኢትዮጵያ መሰጠት የጀመረዉን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ምክንያት በማደረግ መንግስት የማህበራዊ ድረ-ገፆችን ዘጋ። ከቀናት በፊት ብሔራዊ ፈተናዉ ለሁለተኛ ጊዜ አፈትልኮ ስለመዉጣቱ ሲገለፅ ቢቆይም የትምህርት ሚኒስትር የተሰራጨዉን መረጃ በማስተባበል የማህበራዊ ድረ-ገፅችን በመዝጋት የተወሰደዉ እርምጃ ተፈታኞች ፈተናዉን ተረጋግተዉ እንዲወስዱ ነዉ ሲል ገልጿል። በአብዛኛዉ ህዝብ ዘንድ የሚታወቁት የፌስቡክ ፣ ትዊተር ፣ ቫይብር እና ሌሎች አገልግሎቶች ...
Read More »አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መከላከያ ምስክር ሆነው እንዲቀርቡ ፍ/ቤት አዘዘ
ኢሳት (ሃምሌ 4 ፥ 2008) የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት አቶ አንዳርጋቸዉ ፅጌ የቀረበባቸዉን የሽብርተኛ ወንጀል ክስ ለመከላከል ምስክር ሆነዉ እንዲቀርቡላቸዉ ጥያቄ ላቀረቡ አምስት የፓርቲ አመራሮች በመከላከያ ምስክርነት ፍ/ቤት እንዲቀርቡ አዘዘ። ሰበር ችሎቱ የመጨረሻ ዉሳኔውን ሰሞኑን ከማስተላለፉ በፊት የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከወራት በፊት አቶ አንዳርጋቸዉ ለተከሳሾቹ መከላከያ ምስክር ሆነዉ መቅረብ አይችሉም ሲል ትዕዛዝ ማስተላለፉ ይታወሳል። ይሁንና ተከሳሾቹ በታችኛዉ ...
Read More »ግብጽ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ 143 ስደተኞችን በቁጥጥር ስር አዋለች
ኢሳት (ሃምሌ 4 ፥ 2008) የግብፅ መንግስት በህግ-ወጥ መንገድ የዉሃ ግዛት በመጠቀም ወደ አዉሮፓ ለመጓዝ ሙከራን አድርገዋል የተባሉ ኢትዮጵያንን ጨምሮ 143 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን አስታወቀ። በ24 ሰዓታት ዉስጥ ለሁለተኛ ጊዜ በፀጥታ ሀይሎች በተወሰደዉ በዚሁ ዘመቻ 322 ስድተኞች በቁጥጥር ስር ሊውሉ መቻላቸዉን አል-አህራም የተሰኘ ጋዜጣ የግብፅ የባህር ሀይል ሃላፊዎችን ዋቢ በማድረግ ሰኞ ዘግቧል። የሀገሪቱ የባህር ሀይል ሀላፊ የሆኑት ብርጋዴል ጄኔራል ...
Read More »አልሻባብ በፈጸመው ጥቃት በትንሹ 10 ወታደሮች ተገደሉ
ኢሳት (ሃምሌ 4 ፥ 2008) የሱማሌ ታጣቂ ሀይል አል-ሸባብ በደቡባዊ ምዕራብ የሞቃዲሾ አካባቢ በአንድ የሶማሊያ የጦር ማዘዣ ጣቢያ ላይ በፈፅመዉ ጥቃት በትንሹ 10 ወታደሮች ተገደሉ። ታጣቂ ቡድኑ በተሽከርካሪ ላይ በተጠመደዉ ቦንብ አድርሶታል በተባለዉ በዚሁ ጥቃት ቁጥራቸዉ ያልታወቁ ወታደሮች ጉዳት የደረሰባቸዉ ሲሆን ለሰዓታት የቆየ የተክስ ልውውጥ መካሄዱን ሮተርስ የአይን እማኞችን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል። ሰኞ ጠዋት በታችኛዉ የሸበሌ ግዛት በሚገኘዉ የላንታ ቡሮ ...
Read More »