.የኢሳት አማርኛ ዜና

በአሰቦት ከ30 በላይ ሰዎች ታሰሩ

ኢሳት ((ሃምሌ 12 ፥ 2008) በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሃረርጌ ዞን በሚገኘው አሰቦት ከተማ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በአንድ ነዋሪ ላይ በፈጸሙት ድብደባ ተቃውሞን ቀስቅሶ በትንሹ 30 ሰዎች መታሰራቸውንና ድርጊቱ በአካባቢው ውጥረት ማንገሱን እማኞች ለኢሳት አስታወቁ። የከተማዋ ነዋሪዎች በከተማው ከንቲባ ላይ ያላቸውን ተቃውሞና ቅሬታ ማክሰኞ መግለጽ በጀመሩበት ጊዜ የጸጥታ ሃይሎች አንድ ነዋሪን በጠመንጃ ስለት (ሳንጃ) ጭንቅላቱን እንደወጉትና ድርጊቱን ተጨማሪ ተቃውሞ መቀስቀሱን እማኞች ...

Read More »

በምዕራብ ሸዋ ጀልዱ ወረዳ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው

ኢሳት ((ሃምሌ 12 ፥ 2008) በምዕራብ ሸዋ ዞን ጀልዱ ወረዳ በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ማክሰኞ ለሁለተኛ ቀን መቀጠሉ ታወቀ። የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ተቃውሞውን ለማሰማት አደባባይ በወጡ ነዋሪዎች ላይ በወሰዱት የተኩስ ዕርምጃ በትንሹ አምስት ሰዎች መጎዳታቸውን እማኞች ለኢሳት መግለጻቸው ይታወሳል። ይኸው ተቃውሞ ማክሰኞ ለሁለተኛ ቀን የቀጠለ ሲሆን፣ ቁጥራቸው በትክክል ሊታወቅ ያልቻለ ነዋሪዎች ለእስር መዳረጋቸውን ከሃገር ቤት ከተገኘ መረጃ ለመረዳት ተችሏል።

Read More »

የኮሌራ ወረርሽኝ በአዲስ አበባ በከፍተኛ ፍጥነት እየተዛመተ ነው ተባለ

ኢሳት ((ሃምሌ 12 ፥ 2008) በአዲስ አበባ ከተማ ለስድስት ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው የኮሌራ ወረርሽኝ በሽታ ስርጭቱ በተለያዩ የመዲናይቱ አካባቢዎች በመዛመት ላይ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ማክሰኞ አስታወቀ። የበሽታው ስርጭት መባባስን ተከትሎ በየክፍለ ከተማው ተቋቁመው የነበሩ ጊዜያዊ የህክምና መስጫ ተቋማት በእጥፍ እንዲያድጉ ተደርጎ 26 መድረሳቸው ታውቋል። በመጣል ላይ ያለው ዝናብ እስከ ነሃሴ ወር ድረስ ቀጣይ በመሆኑ የበሽታው ስርጭት እየጨመረ ሊሄድ ...

Read More »

ኮ/ል ደመቀ ዘውዱን ፍርድ ቤት ለማቅረብ የሚደረገው እንቅስቃሴ ከህዝቡ ጋር የተደረሰውን ስምምነት የሚጥስ ነው ተባለ

ሐምሌ  ፲፪ ( አሥራ ሁለት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኮሚቴ አባላቱ ለኢሳት እንደገለጹት የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱንም ሆነ በአጠቃላይ የታሰሩትን የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ አቅራቢ የኮሚቴ አባላትን ጉዳይ የሚከታተሉ የአገር ሽማግሌዎች ፣ ኮሎኔሉ ወደ ትግራይ ተላልፈው እንደማይሰጡ እንዲሁም ሁኔታዎች ሲረጋጉ ኮሎኔሉና ሌሎችም የኮሚቴ አባላት ለሽማግሌዎች ተመልሰው እንደሚሰጡ ስምምነት ላይ ተደርሶ ነበር። ኮሎኔሉ ራሳቸው ሽማግሌዎች በተስማሙት መሰረት ስምምነቱ ...

Read More »

በተለያዩ የኦሮምያ አካባቢዎች የሚካሄዱ ህዝባዊ አመጾች እንደቀጠሉ ናቸው

ሐምሌ  ፲፪ ( አሥራ ሁለት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በምእራብ ሸዋ ጀልዱ ወረዳ በጃዊ ቦኒ ከተማ ከፍተኛ ህዝባዊ አመጽ በመካሄድ ላይ ሲሆን፣ ከተለያዩ የገጠር አካባቢዎች የተሰባሰቡ ነዋሪዎች መንገዶችን በመዝጋት እና ገዢውን ፓርቲ የሚያወግዙ መፈክሮችን በማሰማት ተቃውሞ እያደረጉ ነው። እስካሁን ባለው መረጃ 5 ሰዎች ቆስለዋል። በምእራብ ሃረርጌ አሰቦት ወረዳም እንዲሁ ከፍተኛ ህዝባዊ አመጽ ተቀጣጥሎአል። ትናንት የጊንጪ ጀልዱ ግንደበረት መንገድ ...

Read More »

ዓለም የኢትዮጵያን ርሃብ ችላ ሊለው አይገባም ሲል ሻለቃ ሃይሌ ገብረስላሴ ጥሪውን አቀረበ

ሐምሌ  ፲፪ ( አሥራ ሁለት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች በምግብ እጦት ችግር ምክንያት አሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ። ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብና ግብረሰናይ ድርጅቶች በጋራ በመተባበር አፋጣኝ የምግብ እርዳታ ሊያቀርብላቸው ይገባል ሲል የኦሎምፒክ ባለድሉ ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ተማጽኖውን አሰማ። ባለፉት ሃምሳ ዓመታት ውስጥ ተከስቶ የማያውቀው የኢትዮጵያ ድርቅ ተጠቂ የሆኑና አፋጣኝ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች 10.2 ...

Read More »

አቶ ሃብታሙ አያሌው ከሕክምና ቦርድ ማረጋገጫ ቢያገኝም ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሳይሰጥ ቀረ

ሐምሌ  ፲፪ ( አሥራ ሁለት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በከፍተኛ ሕመም የሚሰቃየው አቶ ሀብታሙ አያሌው ወደ ውጭ አገር ሄዶ ለመታከም የሚያስችለውን ተጨማሪ የሕክምና መረጃ ቦርድ እንዲያቀርብ በፍርድ ቤት ትእዛዝ ከተሰጠ በሁዋላ፣  የሕክምና ቦርድ አባላት የፈረሙበትና ታማሚው በግድ ወደ ውጭ ወጥቶ መታከም እንዳለበት የሚያረጋገጥ ማስረጃውን ይዞ ቢቀርብም የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች አልተሰየሙም በሚል ምክንያት ቀጠሮዎችን በማጓተት ፍርድ ቤቱ ...

Read More »

የጸጥታ አካላት በጎንደር ህዝብ ላይ የሚያደርሱትን ግድያና አፈና በመቃወም በዋሽንግተን ዲሲ ሰልፍ ተደረገ

ኢሳት (ሃምሌ 11 ፥ 2008) ባለፈው ሳምንት በጎንደር ከተማና አካባቢዋ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ሰላማዊ ጥያቄን ባቀረቡ ነዋሪዎች ላይ የወሰዱትን ግድያና እስራት በመቃወም ነዋሪነታቸው በዚህ በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማና አካባቢዋ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ሰኞ በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ኣካሄዱ። የተለያዩ መፈክሮችን ሲያስተጋቡ ያረፈዱት ሰልፈኞች መንግስት የማንነት ጥያቄን እያቀረቡ ባሉ አካላት ላይ እየወሰደ ያለው እርምጃ የሚወገዝና ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ገልጸዋል። ...

Read More »

በጎንደር የተቀሰቀሰው ግጭት ወደሌሎች አካባቢዎች እየተዛመተ እንደሆነ ተነገረ

ኢሳት (ሃምሌ 11 ፥ 2008) የወልቃይት የማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በጎንደር በተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ የተገደሉት የመንግስት ታጣቂዎች 11 መሆናቸውን የብሄራዊ መረጃና ፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ። የተገደሉ ሰላማዊ ሰዎች ደግሞ 5 መሆናቸውንም አስታውቋል። ግጭቱ ከጎንደር ባሻገር በሌሎች አካባቢዎች መዛመቱንና ግጭት መከተሉንም አረጋግጧል። የብሄራዊ መረጃና ፌዴራል ፖሊስ የጸረ-ሽብር ግብረ ሃይል እሁድ ዕለት ባወጣው መግለጫ ተጠርጣሪ የተባሉ ግለሰቦችን ለመያዝ የመንግስት ሃይሎች በተንቀሳቀሱበት ወቅት በተከፈተባቸው ...

Read More »

ኢትዮጵያ በየጊዜው የምትበደረው ገንዘብ ዕዳ የመክፈል አቅሟን እያዳከመ ነው ተባለ

ኢሳት (ሃምሌ 11 ፥ 2008) የኢትዮጵያ መንግስት ከተለያዩ የልማት ድርጅቶች ሲወስድ የቆየው አለም አቀፍና የሃገር ውስጥ ብድር ዕዳ የአገሪቱን እዳ የመክፈል አቅም እንደሚጎዳ አንድ አለም አቀፍ ተቋም አሳሰበ። ይኸው የመንግስት የውጭ ዕዳ የመሸከም አቅም እንዲገመገም በመንግስት ተቀጥሮ የነበረውና ፈች የሚል ስያሜ ያለው ኩባንያ የመንግስት የልማት ድርጅቶች እዳ እያሻቀበ መሆኑንና በድርጊቱ በብሄራዊ ደረጃ ስጋት እየሆነ መምጣቱን ይፋ አድርጓል። ኢትዮ-ቴሌኮምን ጨምሮ የኢትዮጵያ ...

Read More »