ኢሳት (ሃምሌ 29 ፥ 2008) ከሃሙስ ጀምሮ አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ የሃገሪቱ ከተሞች የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት ተገቢውን አገልግሎት እየሰጠ እንዳልሆነ ታውቋል። ሃሙስ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ባለስልጣናት በክልሉ የተቃውሞ ሰላምዊ ሰልፍ ለማካሄድ በማህበራዊ ድረገጾች ቅስቀሳ እየተካሄደ ነው ሲሉ ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን መግለጻቸው ይታወሳል። የክልሉ መንግስት ለዚሁ ቅስቀሳ እውቅና እንዳልተሰጠና አዘጋጁ አካል እንደማይታወቅ ቢገለጽም ባለስልጣናቱ የሰጡትን ማሳሰቢያ ተከትሎ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ ዜጎች ወደኦሮሚያ ክልል እንዳይጓዙ ማሳሰቢያ ሰጠ
ኢሳት (ሃምሌ 29 ፥ 2008) የአሜሪካ መንግስት አዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የሃገሪቱ ኤምባሲ የሚሰሩ ሰራተኞች ወደ ኦሮሚያ ክልል እንዳይጓዙ አሳሰበ። በክልሉ ቅዳሜና እሁድ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚካሄድ በማህበራዊ ድረገጾች ቅስቀሳ እየተካሄደ መሆኑን የገለጸው የሃገሪቱ መንግስት ከኢምባሲው ሰራተኞች በተጨማሪ አሜሪካውያን በክልሉ ሊያደርጉ ባሰቡት ጉዞ ላይ አስፈላጊውን የጥንቃቄ እርምጃ እንዲወስዱ በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል። በኦሮሚያ ክልል ሊካሄድ የታቀደውን ይህንኑ የተቃውሞ ሰላማዊ ...
Read More »በኦሮሚያ ክልል የታቀደው ህዝባዊ ተቃውሞ በተያዘለት ቀንና ፕሮግራም እንደሚካሄድ ተገለጸ
ኢሳት (ሃምሌ 29 ፥ 2008) በኦሮሚያ ክልል ሊካሄድ ሊካሄድ የታቀደውን የተቃውሞ ሰልፍ በተመለከተ ተቃውሞ በተለያዩ መንገዶች በማስተባበር ላይ የሚገኙ አካላት ህዝባዊ ተቃውሞ በተያዘለት ቀንና ፕሮግራም እንደሚካሄድ ለኢሳት ገልጸዋል። ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉት እነዚሁ አካላት የተቃውሞ ሰልፍን ለማድመቅ የሚረዱ የተለያዩ ግብዓቶች መዘጋጀታቸውን እና ህዝቡ ያለውን ጥያቄ ለማሰማት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው አስረድተዋል። ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ አርብ በቴለቪዥን ባስተላለፉት መልዕክት ...
Read More »በጎንደርና ኦሮሚያ የሚካሄዱትን ተቃውሞችን ለመግታት እርምጃ እንደሚወሰድ ጠ/ሚ ሃይለማሪያም ገለጹ
ኢሳት (ሃምሌ 29 ፥ 2008) በወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ ሃዝባዊ መሰረት የሌለው ነው ሲሉ ከቀናት በፊት የገለጹት ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ፣ መንግስት ህግ የማስከበር ሃላፊነቱን ለመወጣት ህገወጥ ያለውን ድርጊት ለመግታት እርምጃን እንደሚወስድ ለሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። የጎንደር ከተማ ተቃውሞ እየተካሄደ ባለበት ወቅት መግለጫን የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ህዝቡ አሉ የሚላቸውን ችግሮች በዴሞክራሲያው መንገድ ለመፍታት የሚችልበት ሰፊ እድል ...
Read More »በጎንደር መጠነ ሰፊ ግጭት እየተካሄደ ነው
ኢሳት (ሃምሌ 29 ፥ 2008) አርብ በጎንደር ከተማና አካባቢዋ የሚኖሩ ነዋሪዎች ለሁለተኛ ጊዜ የጀመሩትን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ በከተማ መጠነ ሰፊ ግጭት በመካሄድ ላይ መሆኑን እማኞች ለኢሳት አስታወቁ። የከተማዋ ነዋሪዎች አርብ ረፋድ የወልቃይት ጠገዴ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ በጎንደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ መባሉን ተከትሎ ለተቃውሞ ፍርድ ቤት ቢሰባሰቡም ድርጊቱ ወደ ግጭት መለወጡ ታውቋል። ከተለያዩ አቅጣጫዎች ወደጎንደር ከተማ የሚያስገቡ ዋና ዋና መንገዶች ...
Read More »የጎንደርን ህዝባዊ እምቢተኝነት በአጎራባች አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች እንዲቀላቀሉ ጥሪ ቀረበ
ኢሳት (ሃምሌ 29 ፥ 2008) በጎንደር ህዝብና በመከላከያ ሰራዊት እየተደረገ ያለውን ውጊያ ተከትሎ በአጎራባች አካባቢዎች ያሉ የሚኖሩ ዜጎች ትግሉን እንዲቀላቀሉ ጥሪ ቀረበ። ይህ ዜና እየተጠናከረበት ባለበት ሰዓት በጎንደር ከተማና አካባቢው ከፍተኛ የተኩስ ድምፅ እየተሰማ ሲሆን፣ ህዝቡ ወደ አደባባይ በመውጣት መንገድ መዝጋቱ ታውቋል። ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመከለክተው እስካሁን ድረስ በትንሹ አንድ ሰው መሞቱ ተረጋግጧል። ሌሎች በርካታ ሰዎች ቆስለው ሆስፒታል መግባታቸውንም ለማወቅ ...
Read More »በጎንደር ውጊያ እየተደረገ ነው
ኢሳት (ሃምሌ 29 ፥ 2008) በአዘዞ ከፍተኛ ውጊያ እየተደረገ መሆኑ ተነገረ። 24ኛው ክፍለ ጦር ማዘዣ አካባቢ በህዝቡና በመከላከያ እየተደረገ ያለው ውጊያ ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ ተፋፍሞ መቀጠሉ ለኢሳት የደረሰው መረጃ አመልክቷል። መከላከያ ሰራዊት ከባድ መሳሪያ እየተጠቀመ መሆኑንም ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። መከላከያ ሰራዊቱ በሻለቃ ዶሽቃ ታግዞ ህዝቡ ላይ እየተኮሰ ሲሆን፣ የታጠቀ የጎንደረ አርሶ አደር ከመከካከያ ሰራዊት ጋር የሚያደርገው የተኩስ ...
Read More »የጎንደሩን ህዝባዊ ትዕይንት ያስተባበሩ አካላት በአማራና በኦሮሚያ ለሚደረጉ ሰላማዊ ተቃውሞች ድጋፍ ሰጡ
ኢሳት (ሃምሌ 28 ፥ 2008) በሳምንቱ መጨረሻ በኦሮሚያ ክልል እንዲሁም በአማራ አንዳንድ አካባቢዎች ለታቀደው ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ የጎንደሩን ህዝባዊ ትዕይንት ያስተባበሩ አካላት ድጋፍ ሰጡ። መላው የጎንደር አማራ ኢትዮጵያውያን በሚል ስያሜ የተሰባሰበውና ዕሁድ ሃምሌ 24 ፥ 2008 በጎንደር ከተማ የተካሄደውን ደማቅ ህዝባዊ ትዕይንት ያስተባበሩት ወገኖች ልምዳቸውን ከማካፈል ባሻገር አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም በሁሉም መንገድ ከጎናቸው እንደሚቆሙ ማረጋገጫ ሰጥተዋል። “በእነዚህ ለሰው ልጅ ...
Read More »በእስራዔል የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መንግስት በወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ ላይ እየወሰደ ያለውን እርምጃ በመቃወም ሰልፍ ወጡ
ኢሳት (ሃምሌ 28 ፥ 2008) ነዋሪነታቸው በእስራዔል እየሩሳሌም ከተማ የሆነ ኢትዮጵያውያን መንግስት በወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ ላይ እየወሰደ ያለውን እርምጃ በመቃወም ሃሙስ በከተማዋ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ። ለአመታት የቆየው የማንነት ጥያቄ አፈና ሲካሄድበት መቆየቱን የተናገሩት ሰልፈኞች ወልቃይትና አማራ የማይነጣጠሉ መሆናቸውን ሲገልጹ አርፍደዋል። የተለያዩ መፈክሮችን ሲያሰሙ የነበሩት ሰልፈኞች በአጠቃላይ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በማውገዝ እየተካሄደ ላለው ህዝባዊ ንቅናቄ አጋርነታቸውን እንዳሳዩ ...
Read More »በታንዛኒያ የሚገኙ 500 ኢትዮጵያውያንን ወደ አገራቸው ለመመለስ አለም አቀፍ ድጋፍ ተጠየቀ
ኢሳት (ሃምሌ 28 ፥ 2008) የታንዛኒያ መንግስት በህገወጥ መንገድ ወደ ሃገሪቱ ገብተዋል ተብለው ለእስር የተዳረጉ 500 ስደተኛ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሃገራቸው ለመመለስ አለም አቀፍ የገንዘብ ድጋፍን ጠየቀ። የሃገሪቱ የስደተኛና ኢሚግሬሽን መምሪያ በየጊዜው ወደ ሃገሪቱ የሚገቡ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ቁጥር ከመቼውም ጊዜ በላይ በመጨመር ላይ መሆኑ እንደገለጸ ዘሲትዝን የተሰኘ የታንዛኒያ ጋዚኤጣ ሃሙስ ዘግቧል። በተለያዩ ጊዜያት ወደ ታንዛኒያ በህገወጥ መንገድ ገብታችኋል ተብለው በቁጥጥር ስር ...
Read More »