.የኢሳት አማርኛ ዜና

የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት አቶ ሃብታሙ አያሌው በሃኪሞች ቦርድ ከሃገር ውጭ እንዲታከም የታዘዘን ውሳኔ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንዲያጣራ አዘዘ

ኢሳት (ነሃሴ 2 ፥ 2008) የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በጽኑ በህመም ላይ የሚገኘው አቶ ሃብታሙ አያሌው በሃኪሞች ቦርድ ከሃገር ውጭ እንዲታከም የታዘዘን ውሳኔ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መርምሮ እንዲያጣረ አዘዘ። ፍርድ ቤቱ ከዚህ ቀደም ከሃገር እንዳይወጣ እገዳ ተጥሎበት የሚገኘውን የአንድነት ፓርቲ አመራሩ አቶ ሃብታሙ አያሌው ያቀረበውን የሃኪም ማስረጃ የተሟላ አይደለም ሲል የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ የአቶ ሃብታሙ አያሌው ...

Read More »

ህወሃት መራሹ መንግስት ህዝባዊ አመጹን በሃይል ለመቆጣጠር ባደረገው ሙከራ በአንድ ሳምንት ብቻ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች  በግፍ ተገደሉ

ነሃሴ  ፪ ( ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የህወሃት አገዛዝ በቃን የሚሉ ተቃውሞዎች እየተጠናከሩ መምጣታቸውን ተከትሎ ገዢው ፓርቲ ህዝባዊ አመጹን በመሳሪያ ለመጨፍለቅ እና የስልጣን እድሜውን ለማራዘም እጅግ ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ በመውሰድ ላይ ነው። በዚህ የሃይል እርምጃ በኦሮምያና በአማራ ክልሎች ከ150 በላይ ሰዎች መገደላቸው በብዙ መቶወች የሚቆጠሩ ዜጎች መቁሰላቸው ታውቋል። በኦሮምያ በበርካታ ከተሞች ባለፈው ቅዳሜ የተካሄደውን የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ ...

Read More »

በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ ንቅናቄ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን እየዘገቡት ነው

ኢሳት (ነሃሴ 2 ፥ 2008) በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች እየተከሰተ ያለውን ህዝባዊ ንቅናቄና መንግስት እየወሰደ ያለውን የግድያ እርምጃ አለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ከፍተኛ ሽፋን ሰጡ። ቢቢሲ፣ አልጀዚራ፣ ዩናይትድ ፕሬስ ኢንተርናሽናል፣ ኢንተርናሽናል ቢዝነስ ታይምስ፣ ዶቼ ቬለ እና፣ ኤንዲ24 በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ ተቃውሞ ከዘገቡት አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ይጠቀሳሉ። ቢቢሲ ባሳለፈነው ቅዳሜና እሁድ በጎንደርና በባህርዳር ከተሞች ብዛት ያላቸው ዜጎች በመንግስት ...

Read More »

ህወሃት በጎንደር የሃይማኖት አባቶችን በማሰማራትና ታቦት በማስወጣት ህዝባዊ ንቅናቄውን ለማጨናገፍ እየሰራ ነው ተባለ

ኢሳት (ነሃሴ 2 ፥ 2008) በሰሜን ጎንደር አንዳንድ የሃይማኖት አባቶች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የአካባቢው ነዋሪዎች ጠየቁ። ሰሞኑን ከወልቃይት የማንነት ጥያቄ ጋር ተያይዞ የተቀጣጠለውን ህዝባዊ እምቢተኝነት መንግስት ባሰማራቸው የመከላከያ፣ የፖሊስና ሌሎች የጸጥታ ሃይሎች አማካኝነት በቁጥጥር ስር ማዋል ስለተሳነው የሃይማኖት ተቋማትንና የሃይማኖት አባቶችን ተጠቅሞ ህዝባዊ ንቅናቄውን ለማጨናገፍ እየሰራ መሆኑን ድርጊቱን በቅርበት የሚከታተሉ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ለኢሳት ገለጹ። እነዚህ በዳንሻ እና ሰሮቃ አካባቢ የሚኖሩ ...

Read More »

የጎንደር ህዝብ ከእንግዲህ በህወሃት /ኢህአዴግ አንገዛም አለ

ሐምሌ  ፳፱ ( ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጎንደር ከተማ ህዝብ ገንፍሎ በመውጣት በህዋሀት ኢህአዴግ ላይ ያለውን ተቃውሞ ሲያሰማ ውሎአል። ከእየቦታው የተሰባሰበው የአጋዚ ጦር በህዝቡ ላይ በቀጥታ በመተኮስ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል። በአዘዞ በአርሶአደር ታጣቂዎችና በመከላከያ ሰራዊት አባላት መካከል የተኩስ ልውውጥ ተደርጓል። የህዝቡን ትግል ለመርዳት ከወልቃይትና ከተለያዩ አካባቢዎች የተሰባሰቡ ታጣቂዎች ወደ ጎንደር መግባታቸውን ተከትሎ ወታደሮቹ ጥቃታቸውን ቀንሰዋል። በልዩ ሃይል ...

Read More »

የብረታብረት ኢንጂነሪንግ ሰራተኞች ተቃውሞ እያሰሙ ነው

ሐምሌ  ፳፱ ( ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) አስተዳደር ያለሰራተኞቹ ፈቃድ ለአባይ ግድብ በሚል የአንድ ወር ደሞዛቸውን  ከነሐሴ ጀምሮ እንደሚቆርጥ ማስታወቁን ተከትሎ ሰራተኞቹ ተቃውሞውአቸውን የገለጹ ሲሆን፣ የሰራተኛው ተቃውሞ ያስፈራው አስተዳደሩ ውሳኔውን ለሚቀጥለው ወር መተላለፉን አስታውቋል። ሰራተኞች ውሳኔውን አንቀበለም በማለታቸው ደሞዛቸው የታገደ ሲሆን በዚህም ምክንያት  ለከፍተኛ ችግር ተዳርገው ይገኛሉ፡፡ ሰራተኞቹ  እኛ የምናዋጣው ከምናገኘው ጋር ተመጣጣኝ ...

Read More »

በፎገራ ወረዳ የሚገኙ ስምንት ቀበሌዎች በጎርፍ አደጋ ተጠቁ፡፡

ሐምሌ  ፳፱ ( ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ጎንደር በ2 ቢሊዮን 400 ሚሊዮን ብር በመገንባት ላይ ያለው ርብ ግድብ ከመፍረሱ ጋር ተያይዞ ከ17 በላይ ሰዎች መሞታቸው እንዲሁም ከ60 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ጉዳት ከደረሰባቸው በሁዋላ፣ የግድቡ ውሃ በፎገራ ወረዳ የሚገኙ ስምንት ቀበሌዎችን ማጥለቅለቁ ታውቋል፡፡በአካባቢው የሚገኙ ነዋሪዎች ወደ መንገድ ዳርና ወደተራራ ቦታዎች በመሄድ ለመስፈር ሙከራ እያደረጉ ነው። ግድቡ በ4 ...

Read More »

ሶስት የኢሲኤ (ECA) ሰራተኞች ታሰሩ

ኢሳት (ሃምሌ 29 ፥ 2008) አዲስ አበባ በሚገኘው የተባበሩት  መንግስታት ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ ቦምብ እና መሳሪያ ተገኝቷል በሚል ሶስት የድርጅቱ ሰራተኞች የሆኑ ኢትዮጵያውያን በቁጥጥር ስር ዋሉ። ዋና ሃላፊው ሚስተር ካርሎስ ሎፔዝ  የድርጅቱን ሰራተኞች ባልተጣራ ጉዳይ አሳልፈው መስጠታቸው በሰራተኞች ዘንድ እያነጋገረ መምጣቱንም መረዳት ተችሏል። አዲስ አበባ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታተ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ጽ/ቤት ግቢ ወስጥ ተገኘ ከተባለው መሳሪያ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ...

Read More »

ባህርዳር የሚገኘው የአቶ ካሳ ተክለብርሃን ቤት በድንጋይ እየተደበደበ ነው ተባለ

ኢሳት (ሃምሌ 29 ፥ 2008) የወልቃይት የማንነት ጥያቄ ጊዜው ያለፈበትና ምላሽ ያገኘ መሬቱም የትግራይ ነው በማለት መግለጫ የሰጡት የአቶ ካሳ ተክለብርሃን ቤት በድንጋይ እየተደበደበ ነው። የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት፣ ባህርዳር ከተማ የሚገኘው የአቶ ካሳ ተክለብርሃን ባለሁለት ፎቅ መኖሪያ ቤት መደብደብ የጀመረው አርብ ምሽት ሲሆን፣ ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ በድንጋይ እየተደበደበ ይገኛል። ተቃውሞው በከተማዋ እየሰፋ መገኘቱንም መረዳት ተችሏል። የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትርና ...

Read More »

በእነብርሃኑ ተክለ ያሬድ መዝገብ ክስ የተመሰረተባቸው 4 ተከሳሾች እስራት ተበየነባቸው

ኢሳት (ሃምሌ 29 ፥ 2008) ባለፈው አመት ወደ ኤርትራ በመጓዝ የግንቦት ሰባት ሃይልን ለመቀላቀል ሙከራ ሲያደርጉ በድንበር ላይ ተይዘዋል ተብለው የሽብርተኛ ወንጀል ክስ የተመሰረተባቸው አራት ተከሳሾች ከአራት እስከ አምስት አመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ተቀጡ። ተከሳሽ ብርሃኑ ተክለ ያሬድ የግንቦት ሰባት አባል በመሆንንና አባላትን በመመልከል አድርጎታል በተባለው ክስ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአምስት አመት ጽኑ እስራት ተወስኖበታል። በተመሳሳይ ክስ ስር የነበሩትና ...

Read More »