ኢሳት (መስከረም 2 ፥ 2009) የዘንድሮውን የኢድ አል አድሃ በዓል ለማክበር በጎንደር ከተማ የተሰባሰቡ የሙስሊሙ ማህበረሰብ በከተማዋ ባለስልጣናት ባለኮከብ ባንዲራን ይዘው እንደወጡ የተሰጣቸውን መልዕክት ሳይቀበሉ መቅረታቸው ታውቋል። ለበዓሉ አከባበር የታደሙት የሙስሊሙ ማህበረሰብ የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ወደጎን በመተው በዕለቱ የተቃውሞ መልዕክት ነው ያሉትን ቀይ ፊኛ ወደሰማይ ሲለቁ የሚያሳይ ቪዲዮ መልዕክት ለዜና ክፍላችን ደርሷል። ቀይ ፊኛን ወደ ሰማይ መመልቀቁ ጎን ለጎን ታዳሚዎች እጃቸውን ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ጋዜጠኛ ዩሱፍ ጌታቸውን መንግስትን ይቅርታ አልጠየቅሁም አለ
ኢሳት (መስከረም 2 ፥ 2009) የህዝበ ሙስሊሙን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ሲዘግብ በአሸባሪነት ተከሶ በእስር ቤት ላይ የቆየው ጋዜጠኛ ዩሱፍ ጌታቸው መንግስትን ይቅርታ አለመጠየቁን ገለጸ። ጋዜጠኛ ዩሱፍ ሙያውን ሽፋን በማድረግ ህዝብን ለአመጽ በማነሳሳት በሚል ክስ 7 አመት ተፈርዶበት በእስር ቤት አመታትን አስቆጥሯል። ከ4 አመታት በላይ በእስር የቆየው ጋዜጠኛ ዩሱፍ ጌታቸው በመክሮ ሊፈታ ወራት ሲቀሩት ከአዲሱ ዓመት ጋር በተየያዘ በምህረት በሚል ከተለቀቁት መካከል ...
Read More »አትሌት ታምሩ ደምሴ የአትሌት ፈይሳ ሌሊሳን የተቃውሞ ድርጊት መድገሙን አለም አቀፍ መገኛኛ ብዙሃን ዘገቡ
ኢሳት (መስከረም 2 ፥ 2009) በብራዚል ሪዮ ዴ ጄኔሮ በመካሄድ ላይ ባለው የፓራ ኦሎምፒክ በ 1ሺ 500 ሜት የብር ሜዳልያን ያገኘው ኢትዮጵያዊው አትሌት ታምሩ ደምሴ በመንግስት የሚፈጸሙ ግድያዎችን በመቃወም የአትሌት ፈይሳ ሌሊሳን ድርጊት መድገሙ አለም አቀፍ መገኛና ብዙሃን ከስፍራው ዘገቡ። ሰኞ በውድድሩ ሜዳልያን ለማግኘት የበቃው አትሌቱ በአለም አቀፉ ደረጃ ተመሳሳይ መልዕክትን ካስተላለፉ አትሌቶች መካከል አራተኛው ለመሆን መብቃቱን ኢንዲፔንደንት የተሰኘ ጋዜጣ ...
Read More »ባለፈው ሳምንት በኦሮሚያ የተጀመረው ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ እንደሚገኝ ተገለጸ
ኢሳት (መስከረም 2 ፥ 2009) ባለፈው ሳምንት በተለያዩ የኦሮሚያ የክልል ከተሞች ሲካሄድ የቆየው ከቤት ያለመውጣትና የንግድ እንቅስቃሴ የማቆም አድማ ሰኞ ድረስ መቀጠሉን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። በአምቦና በዙሪያ ባሉ አካባቢዎች እንዲሁም በሻሸመኔ ከተማ ዙሪያ ሲካሄድ የቆየው አድማ ለሰባተኛ ቀን መቀጠሉን ነዋሪዎች በመግለጽ ላይ ናቸው። በተለያዩ ከተሞች አድማን እያደረጉ ያሉት ነዋሪዎች የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በንጹሃን ሰዎች ላይ የሚፈጸሙትን ድርጊት እንዲያቆሙና ...
Read More »በኢድ አል አደሃ አረፋ አከባበር ላይ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰሙ
መስከረም ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 1 ሺህ 437ኛው የኢድ አል አደሃ አረፋ በአል በመላው አገሪቱ በሰላምና በተቃውሞ ተከብሯል። በአዲስ አበባ በአሉ ያለምንም ችግር የተከበረ ሲሆን፣ በጎንደር፣ ድሬዳዋ፣ አወዳይና ሻሸሜ ህዝበ ሙስሊሙ ተቃውሞውን አሰምቷል። በጎንደር ከተማ ሙስሊሙ በአሉን ለማክበር በወጣበት ወቅት በመላው አገሪቱ እየተካሄደ ያለውን ግድያ በጽኑ የሚያወግዙ መፍክሮችን ከማሰማት በተጨማሪ ለኢትዮጵያ የነጻነት ትግል ያለውን አጋርነት እጆቹን ...
Read More »በባህር ዳር ከተማ በተካሄደው ህዝባዊ እምቢተኝነት የተቃውሞ ሰልፍ በወጡ ወጣቶች ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ እንዳስከፋቸው የወጣቶቹ ቤተሰቦች ተናገሩ፡፡
መስከረም ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከባህር ዳር ከተማ በመንገድ ላይ ሲዘዋወሩ የተያዙትን እነዚህ ወጣቶች ከባህር ዳር ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘው የወንዳጣ እስር ቤት ታጉረው ከሰነበቱ በኋላ፣ የስርዓቱ ቃል አቀባይ በሆኑ ና አብረው የታሰሩ በመሰሉ ከሃዲዎች ተገኘ በተባለው መረጃ ብቻ ተመርጠው ወደ ብር ሸለቆ ወታደራዊ የጦር ካምፕ ማሰልጠኛ ተወስደው በከፍተኛ ስቃይ ላይ መሆናቸውን ከስፍራው በሚወጡ መረጃዎች መረዳታቸውን ...
Read More »በኢትዮጵያ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ሰላማዊ ምላሽ ካላገኘ ከፍተኛ ቀውስ ሊያስከትል ይችላል ተባለ
ኢሳት (ጳጉሜ 4 ፥ 2008) በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች በመካሄድ ላይ ያለው ህዝባዊ ተቃውሞ ለአፍሪካ ህብረትና ለተለያዩ አለም አቀፍ አካላት ልዩ ትኩረት እየሆነ መምጣቱንና ተቃውሞ ሰላማዊ ምላሽ ካላገኘ በመላው ሃገሪቱ ተቃውሞ ሊቀሰቅስ እንደሚችል የቱርክ የዜና አገልግሎት አርብ ዘገበ። መቀመጫውን በአዲስ አበባ ያደረገው የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ባልተለመደ መልኩ በሃገሪቱ ስላለው የጸጥታ ሁኔታ ስጋቱን እየገለጸ እንደሆነ ያወሳው አናዱሉ የዜና አውታር፣ ተቃውሞው አሁንም ድረስ ...
Read More »በጀርመን በርሊን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ
ኢሳት (ጳጉሜ 4 ፥ 2008) ነዋሪነታቸው በጀርመን በርሊን ከተማና አካባቢዋ የሆነ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ መንግስት በንጹሃን ሰዎች ላይ የሚፈጸመውን ግድያና አፈና በመቃወም አርብ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ። በበርሊን ከተማ በሚገኘው የሃገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፊት ለፊት ተሰባስበ የነበሩት ኢትዮጵያውያን የተለያዩ መፈክሮች በማስተጋባት የጀርመንንና ሌሎች ሃገራት መንግስታት በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ጉዳይ ልዩ ትኩረትን እኝዲሰጡ ጠይቀዋል። በዚሁ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የተለያዩ አላማ ያላቸው ...
Read More »በዛምቢያ ሲጓጓዙ በነበሩ ኢትዮጵያውያን ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ2 ሰዎች ህይወት ጠፋ
ኢሳት (ጳጉሜ 4 ፥ 2008) በዛምቢያ ድንበር በህገወጥ መንገድ ሲጓጓዙ ነበሩ የተባሉ 14 ስደተኞች ኢትዮጵያውያን ላይ የትራፊክ አደጋ ደርሶ ሁለት ኢትዮጵያውያን መሞታቸውን የሃገሪቱ ባለስልጣናት አርብ ገለጡ። የዛምቢያ ፖሊስ በበኩሉ በተለያዩ ጊዜያው ወደ ዛምቢያ የሚሰደዱና ሃገሪቱ አቋርጠው የሚጓዙ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ እንዳሳሰበው መገልጹን የዛምቢያ መገኛኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በሃገሪቱ የድንበር አካባቢ ደርሶ ነበር ከተባለው የትራፊክ አደጋ የተረፉ 12 ስደተኛ ኢትዮጵያውያን ...
Read More »በኦሮሚያ ክልል ከቤት ያለመውጣት አድማ ተጠናክሮ ቀጥሏል
ኢሳት (ጳጉሜ 4 ፥ 2008) በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች ከቀናት በፊት የተጀመረው ከቤት ያለመውጣት የስራ ማቆም አድማ አርብ ድረስ መቀጠሉን የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች አስታወቁ። የአዲስ አበባ ኮሚሽን በበኩሉ የፊታችን እሁድ የሚከበረውን የአዲስ አመት በአል ዝግጅት በሰላም ለማክበር ሲባል በከተማዋና በዙሪያው ባሉ አካባቢዎች የጸጥታ ቁጥጥሩ ተጠናክሮ መቀጠሉን አርብ ለሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል። በኦሮሚያ ክልል እንዲሁም በሌሎች የሃገሪቱ ክፍሎች የሚካሄዱ ...
Read More »