ኢሳት (መስከረም 20 ፥ 2009) የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ከነገ በስቲያ እሁድ በበሾፍቱ ከተማ ለሚከበረው የእሬቻ በዓል ልዩ ሃይል ተመድቦ የጸጥታ ቁጥጥር በመደረግ ላይ መሆኑን አርብ አስታወቀ። የከተማዋ ነዋሪዎች የፌዴራልና የክልል የጸጥታ አባላት ከመቼውም ጊዜ በላይ በመሰማራት ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ በተለያዩ ስፍራዎች ፍተሻ በመካሄድ ላይ መሆናቸውን ረቡዕ ለኢሳት መግለጻቸው ይታወሳል። የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አርብ ባወጣው መግለጫ በከተማ የበዓሉ አከባበር በሰላም እንዲስተናገድ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ፖሊስ የተመድ ሰራተኞች የእሬቻን በዓልን ለመከታተል ወደ ቢሾፍቱ እንዳይጓዙ አሳሰበ
ኢሳት (መስከረም 20 ፥ 2009) የፊታችን ዕሁድ በደብረ ዘይት (ቢሾፍቱ) ከተማ የሚከበረውን የእሬቻ በዓል አከባባር ምክንያት በማድረግ የተባበሩት መንግስታት የደህንነትና የጸጥታ መምሪያ ሰራተኞች ወደ ከተማዋ እንዳይጓዙ አሳሰበ። መምሪያው ለሰራተኞቹ ባሰራጨው ማሳሰቢያ ተለይቶ የታወቀ የደህንነት ስጋት ባይኖርም፣ የድርጅቱ ሰራተኞች ቅዳሜ እኩለ ቀን ጀምሮ እስከ ሰኞ ድረስ የግል ጉዞን ጨምሮ ከማንኛውም እንቅስቃሴ እንዲታቀቡ ጠይቋል። በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል ህዝባዊ ተቃውሞዎች ሲካሄዱ መሰንበታቸውን ያወሳው ...
Read More »በቤኒሻንጉል ጊዛን ወደ 300 የሚጠጉ ነዋሪዎች ለደህንነታቸው ሲሉ ጫካ መግባታቸው ተነገረ
ኢሳት (መስከረም 20 ፥ 2009) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጊዛን ተብሎ በሚጠራ አካባቢ የተቀሰቀሰውን ግጭት እልባት አለማግኘቱን ተከትሎ ወደ 300 የሚጠጉ ነዋሪዎች ለደህንነታቸው ሲሉ ጫካ መግባታቸውን እማኞች አርብ ለኢሳት ገለጡ። በነዋሪዎችና ከትግራይ ክልል መጥተው ሰፍረዋል በተባሉ 1ሺ አካባቢ ሰዎች መካከል የተፈጠረው ግጭት በትንሹ ስምንት ከሚሆኑ የመንግስት የጸጥታ አባላት ግድያ ምክንያት መሆኑን ሃሙስ መዘገባችን ይታወሳል። ድርጊቱ እልባት ሳያገኝ ለሶስተኛ ቀን መቀጠሉን የተናገሩት ...
Read More »በጎንደርና ባህርዳር ከተሞች የንግድ ቤቶች መታሸጋቸው ተቃውሞ አስነሳ
ኢሳት (መስከረም 20 ፥ 2009) በቅርቡ በጎንደርና ባህር ዳር ከተሞች በስራ ማቆም አድማ ተሳትፋችኋል የተባሉ የንግድ ድርጅቶችን ለማሸግ በንግድ ቢሮ እየተካሄደ ያለው የማሸግ ዕርምጃ ነዋሪዎችን ማስቆጣቱ ታወቀ። በተለይ ከአንድ ሳምንት በፊት ለሶስተኛ ጊዜ የስራ ማቆም አድማ ውስጥ በቆየችው የጎንደር ከተማ በርካታ ሱቆች እየታሸጉ መሆናቸውን እማኞች ማስረጃዎችን በማስደገፍ ለኢሳት አስረድተዋል። ይሁንና የከተማው የንግድ ቢሮ የንግድ ድርጅቶቹን ለማሸግ እየወሰደ ያለው እርምጃ በነዋሪዎች ...
Read More »የጎንደር ዩኒቨርስቲ መምህራንና ሰራተኞች ተቃውሞ ማሰማታቸውን ተከትሎ ስብሰባው ተበተነ
መስከረም ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የጎንደር ዩኒቨርስቲ መምህራንንና ሰራተኞች ዛሬ በሳይንስ አምባ አዳራሽ ላይ ስብሰባ የተካሄደ ቢሆንም፣ መምህራኑ በጩኸት እና በፉጨት ተቃውሞ በማሰማታቸው እንዲበተን ተደርጓል። ስብሰባውን የመሩት የቀድሞው የትምህርት ሚ/ር ዶ/ር ስንታየሁ ወልደሚካኤል ሲሆኑ ፣ ንግግር ሲጀምሩ የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ በጩኸት አቋርጧቸዋል። ስብሰባው መቀጠል እንደማይቻል የተረዱት ሰብሳቢዎቹ በእረፍት አሳበው ከ20 ደቂቃዎች በሁዋላ ስብሰባውን በትነውታል። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ደሳለኝ ...
Read More »አንድ የስውዲን የፓርላማ አባል አገራቸው በኢትዮጵያ ላይ የምትከተለውን ፖሊሲ እንድትምረመር ጠየቁ
መስከረም ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ስዊድንን በማስተዳደር ላይ ያለው የክርስቲያን ዲሞክራት ፓርቲ አባል የሆኑት ሚ/ር አንደርስ ኦስተንበርግ ስዊድን ለኢትዮጵያ በምትሰጠው እርዳታ እንዲሁም በአሪቱ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲገነባ እያደረገች ያለውን ጥረት በተመለከተ ለውጭ ልማትና እርዳታ ሚኒስትር ጥያቄ አቅርበዋል። ሚኒስትሯ በኢትዮጵያ የሚካሄደው ነገር እንደሚያሳስባት ብትገልጽም፣ እኔ ግን አገሪቱ አስቸኳይ እርምጃ እንድትወስድ ጠይቄያለሁ ብለዋል። በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ሁኔታ በቅርብ እንደሚከታተሉ ለኢሳት ...
Read More »በጢስ አባይ አንድ የፖሊስ አባል እስረኛ ይዞ ሲሄድ ተገደለ
መስከረም ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በምዕራብ ጎጃም ዞን በጢስ አባይ ከተማ አንድ ፖሊስ በእስር ላይ የነበረን ወጣት በህዝብ ትራንስፖርት ወደ ባህርዳር በመውሰድ ላይ እያለ ሁለት ወጣቶች ወደ አውቶቢሱ በመግባት ከከተማዋ ወጣ እንዳሉ ፣ ፖሊሱን በጩቤ በመውጋት ገድለው እስረኛውን እና የፖሊሱን የጦር መሳሪያ ይዘው ማምለጣቸውን የአይን እማኞች ተናግረዋል። ጥቃቱን ያደረሱትን ሰዎች ለመያዝ በርካታ ወታደሮች ወደ አካባቢው ተሰማርተው ...
Read More »በማንችሰትር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ የሚፈጸመው ግድያና አፈና እንዲቆም ጠየቁ
መስከረም ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በእንግሊዝ ማንችስተር ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ ያደረጉ ኢትዮጵያውያን የተለያዩ የተቃውሞ መፈክሮችን በማሰማት እንዲሁም በእስር ላይ የሚገኙ ፖለቲከኞችን፣ ጋዜጠኞችንና በግፍ የተገደሉ ዜጎችን ፎቶግራፎች በመያዝ አገዛዙ በአገር ውስጥ የሚፈጸመውን ግድያና አፈና አውግዘዋል።ከአስተባባሪዎች መካከል አንዱ የሆነው አቶ ይድነቃቸው ረዳ እንደተናገረው ቀደም ብለው ለተለያዩ የፓርላማ አባላት፣ እንዲሁም ተጽኖ ፈጣሪ ሰዎች ዘንድ መልእክት መተላለፉን ገልጸዋል። የተቃውሞ ሰልፉ ...
Read More »በደብረዘይት (ቢሾፍቱ) የሚከበረውን የእሬቻ በዓልን አስመልክቶ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት መሰማራቱ ተገለጸ
ኢሳት (መስከረም 19 ፥ 2009) የፊታችን ዕሁድ በደብረዘይት (ቢሾፍቱ) ከተማ ለሚከበረው አመታዊው የእሬቻ በዓል አከባባር በሚል ቁጥር ከፍተኛ የሆነ የፌዴራል የክልል የጸጥታ ሃሎች በከተማዋ መሰማራታቸውን እማኞች ለኢሳት ገለጹ። የበዓሉ አከባበር ዝግጅትን ተከትሎ ወደ ከተማ በሚገቡ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥብቅ ፍተሻ በመደረግ ላይ መሆኑም ታውቋል። በኦሮሚያ ክልል ከወራት በፊት የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ በቢሾፍቱ ከተማ ዙሪያዋ ባሉ የገጠር ወረዳዎች ህዝባዊ ትዕይንቶች ሲካሄዱ የንበረ ...
Read More »የመልቀቂያ ወረቀት ያቀረቡ በርካታ ወታደሮች በመለስ አጽም እየተባሉ እንዲቆዩ እየተለመኑ ነው
መስከረም ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመላው አገሪቱ የሚታየውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የ7 አመታት የከንትራት ጊዜያቸውን የጨረሱ ወታደሮች መልቀቂያ በብዛት እያስገቡ ቢሆንም፣ አዛዦቹ የቀድሞውን ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ፎቶ እግራቸው ስር በማንጠፍ “ የመለስን ፎቶ ተራምደኸው እለፍ፣ በመለስ አጽም ይዘንሃል” እየተባሉ ኮንትራታቸውን እንደሚያራዝሙ የመከላከያ ምንጮች ገለጹ” በአሁኑ ሰአት መከላከያው ከፍተኛ ችግር ውስጥ መግባቱን የሚገልጹት ምንጮች፣ ወታደሮች በአማራ ...
Read More »