ኢሳት (ህዳር 8 ፥ 2009) በባህርዳር ከተማ የጊዮን ሆቴልን ያለጨረታ ተከራይተው ለ20 አመታት ሲጠቀሙበት የነበሩት አቶ ወልዱ ወልደአረጋይ በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ቢታዘዙም የትግራይ ክልል አሳልፌ አልሰጥም ማለቱ ተነገረ። የአቶ መለስ ዜናዊ ዘመድ እንደሆኑ የሚታወቁት አቶ ወልዱ ወልደ አረጋይ ከ1987 ዓም ጀምሮ ለ 20 አመታት የመንግስት የነበረው የባህርዳር ጊዮን ሆቴል ያለጨረታ ተከራይተው ሲገለገሉ ቆይተዋል። ይሁንና አቶ መለስ ከሞቱ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በየመን የሚገኙ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ለከፋ የሰብዓዊ ቀውስ ተጋልጠዋል ተባለ
ኢሳት (ህዳር 8 ፥ 2009) በየመን በስደት ላይ የሚገኙ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ለከፋ የሰብዓዊ ቀውስና በሃገሪቱ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ተጋላጭ መሆናቸው ስጋት እንዳሳደረበት የአለም አቀፍ የሰደተኞች ድርጅት (IOM) አስታወቀ። ሰሞኑን በሳውዲ አረቢያ የሚመራው ጥምር ሃይል ለተወሰነ ጊዜ የሚፈጸመውን የአየር ጥቃት ማቆሙን ተከትሎ ድርጅቱ መውጫን አጥተው የሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያንን ከሃገሪቱ ለማስወጣት ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጿል። ይሁንና የስደተኞቹ ቁጥር ከፍተኛ መሆኑንና ...
Read More »የኢትዮጵያ መንግስት ለእስር የዳረጋቸውን ሁሉንም ጋዜጠኞች በአስቸኳይ እንዲፈታ ሲፒጄ ጥሪ አቀረበ
ኢሳት (ህዳር 8 ፥ 2009) የአለም አቀፍ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (ሲፒጄ) ኮሚቴ ቱ ፕሮቴክት ጆዎርናሊስትስ የኢትዮጵያ መንግስት ለእስር የዳረጋቸውን ሁሉም ጋዜጠኞች በአስቸኳይ እንዲፈታ ሃሙስ ጥሪውን አቀረበ። በሃገሪቱ የተፈጠረውን አለመረጋጋት ተከትሎ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ከመቼውም ጊዜ በላይ ወከባ እየተፈጸመባቸው መሆኑን ድርጅቱት ለመንግስት ባቀረበው የጸሁፍ መልዕክት አመልክቷል። ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ብቻ አንድ ጋዜጠኛን ጨምሮ ሁለት ጦማሪያን ለእስር መዳረጋቸውን ያወሳው ሲፒጄ ሌላ ...
Read More »በቅርቡ የተከሰተው የድርቅ አደጋ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የአርብቶ አደር ማህበረሰቦችን ህይወት አደጋ ላይ መጣሉን ተመድ ገለጸ
ኢሳት (ህዳር 8 ፥ 2009) በደቡብ ምስራቅ የኢትዮጵያ አካባቢ በቅርቡ የተከሰተው አዲስ የድርቅ አደጋ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የአርብቶ አደር ማህበረሰቦች ህይወትን አደጋ ላይ እንደጣለ ተመድ ገለጸ። በአካባቢው የተከሰተውን ይህንኑ አዲስ የድርቅ አደጋ ተከትሎ በቤት እንስሳት ላይ አሉታዊ ጉዳት መከሰት መጀመሩን ያስታወቀው ድርጅቱ በኦሮሚያ ክልል 10 በመቶ የሚሆኑ የአርብቶ አደሩ እንስሳቶች አስቸኳይ የምግብ አቅርቦት እንደሚፈልጉ በድርቁ ዙሪያ ባወጣው መግለጫ አስፍሯል። ይኸው የድርቅ ...
Read More »የአፍሪካ ሃገራት ከአለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አባልነት ለመውጣት እያካሄዱ ያለው ዘመቻ ተወገዘ
ኢሳት (ህዳር 8 ፥ 2009) የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የአፍሪካ ሃገራት ከአለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አባልነት ለመውጣት እያካሄዱ ያለውን ዘመቻ አወገዘ። የአህጉሪቱ ሃገራት ከአባልነት ለመውጣት እየወሰዱ ያለው እርምጃ ከተጠያቂነት በማምለጥ የተያዘ ስልት ነው ሲሉ የኮሚሽኑ ሃላፊ ዘይድ ራድ አል ሁሴን ለአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን መግለጻቸውን ቢቢሲ ሃሙስ ዘግቧል። ኢትዮጵያን ጨምሮ የምስራቅ አፍሪካ ሃገራት በተለያዩ ጊዜያት በአዲስ አበባ በመሰብሰብ ...
Read More »የአርበኞች ግንቦት7 ሃይል ከህወሃት/ኢህአዴግ ወታደሮች ጋር በቀብትያ ሁመራ እና አጎራባች ቀበሌዎች እየተዋጋ ነው
ኅዳር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአርበኞች ግንቦት7 የሰሜን ጎንደር አስተባባሪ እንደገለጹት፣ አባሎቻቸው በሰሜን ጎንደር በተለያዩ አካባቢዎች ለወራት ሲደራጁና ሲያደራጁ ከቆዩ በሁዋላ፣ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ወታደራዊ ጥቃት በመፈጸም ላይ ናቸው። በተለይ ከትናንት ጀምሮ በቃፍታ ሁመራ እና በአከር አካባቢ ከፍተኛ ውጊያ እያካሄደ መሆኑንም ተናግረዋል። አደንድን በሚባል አካባቢ ባለፈው ሳምንት በተደረገው ጦርነት 48 የአገዛዙ ወታደሮች መገደላቸውን የገለጹት አስተባባሪው፣ ከትናንት ...
Read More »በአባይ ግድብ አካባቢ ያለው የስራ እንቅስቃሴ መዳከሙን ጋዜጠኞች ገለጹ ።
ኅዳር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ‹‹ በአባይ ግድብ ላይ ያለው እንቅስቃሴ ቆሟል የሚል ወሬ በስፋት እየተወራ ነውና ወሬውን አክሽፉ!” ተብለው ለጉብኝት የተላኩት ጋዜጠኞች ምንም አይነት የስራ እንቅስቃሴ ባለማየታቸው የሚወራው ትክክል መሆኑን አረጋጋጥው መመለሳቸውን ለኢሳት ገለጹ። ሰሞኑን ወደ አባይ ግድብ የተላከው የ መንግስት ጋዜጠኞች ቡድን ለጉብኝት በቆየበት አንድ ቀን፤ ምንም አይነት ስራ ሲሰራ አለመመልከቱን ገልጿል፡፡ ‹‹ ለአንድም ...
Read More »በሶማሊያ ክልል በኮሌራ ወረሽኝ 35 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ
ኅዳር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በምስራቅ ኢትዮጵያ ኦጋዴን አካባቢዎች በኮሌራ በሽታ 35 ሰዎች መሞታቸውንና ድርቁን ተከትሎ ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊ ቀውስ እየተፈጠረ መሆኑን የኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅት አስታወቀ። በድርቁ ምክንያት እንስሳት እየሞቱ ነው። የምግብ እጥረት ተጠቂ የሆኑት የኦጋዴን ነዋሪዎች አፋጣኝ እርዳታ ካላገኙ አደጋው የከፋ ቀውስ ሊያስከትል ይችላል ተብሎ ተሰግቷል። ለጋሽ የረድኤት ድርጅቶች ለነዋሪዎቹ የሚያደርጉትን ሰብዓዊ እገዛዎች እንዳያሰራጩ ...
Read More »በኢንተርኔት አፈና ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆነች ።
ኅዳር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በዜጎቻቸው ላይ አፈና በማድረግ የመረጃ እቀባ ከሚያደርጉ አገራት ውስጥ ቻይና፣ ሶሪያ እና ኢራንን በመከተል ኢትዮጵያ በዓለም አራተኛ፣ በአፍሪካ ደግሞ በአንደኝኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን ፍሪደም ሃውስ አስታውቋል። በኢንተርኔት ስርጭት ሁዋላ ቀር የሆነችው ኢትዮጵያ በኢንተርኔት ተጠቃሚ ዜጎቿ ላይ በምታደርገው እቀባዎችና አፈናዎች ግን ቀዳሚ ሆናለች ብሎአል። አንድ ዓመት ያስቆጠረውን የኢትዮጵያን ሕዝባዊ አመጽ ተከትሎ በመላው ...
Read More »በውጭ ሃገራት በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና በመንግስት መካከል ሊካሄድ የታቀደ ስብሰባ መሰረዙ ተገለጸ
ኢሳት (ህዳር 7 ፥ 2009) በውጭ ሃገራት በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና በመንግስት መካከል ባሉ የተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ረቡዕ በአዲስ አበባ ከተማ ሊካሄድ የነበረ ስብሰባ ባልታወቀ ምክንያት መሰረዙ ተገለጸ። በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተቋቋመው የዳያስፖራ ማህበር ጽ/ቤት ከ1ሺ በላይ ሰዎች ይታደሙበታል ተብሎ የተጠበቀው የውይይት መድረክ ግልጽ ባልሆነ ምክንያት ሊካሄድ አለመቻሉንና ስብሰባው ለሌላ ጊዜ ይካሄዳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ለሃገር ውስጥ መገናኛ ተቋማት አስታውቋል። በተመሳሳይ ሁኔታ ...
Read More »