ኅዳር ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በየዓመቱ እየባሰበት የመጣው የኢትዮጵያ የዋጋ አለመረጋጋት አሁንም ተባብሶ መቀጠሉን የማእከላዊ ስታስቲክ ጽፈት ቤትን ዋቢ በማድረግ የዓለም የምግብ ድርጅት በወርሃዊ የጥናት ሪፖርቱ አመላክቷል። ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ 5.6% የነበረው የምግብ ፍጆታ በሕዳር ወር ወደ 3.4% ከፍ በማለት ጭማሪ አሳይቷል። ይህም በአገሪቱ ውስጥ የዋጋ ንረት ማስከተሉን የደንበኞች የዋጋ አመላካች Consumer Price Index ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ዶክተር አብርሃም ይሳቅ በእስራኤል መከላከያ ሰራዊት የመጀመሪያው ቤተእስራኤላዊ ኮሎኔል ሆነው ተሾሙ
ኅዳር ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በ19 ዓመታቸው ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል የተጓዙት ኮሎኔል ይስሃቅ፣ በወታደራዊ ሕክምና አገልግሎት በዶክተርነት ሲገለግሉ መቆየታቸው ጄሩሳሌም ፖስት ዘግቧል።
Read More »ኬንያ በሰላም አስከባሪ ሃይል ስር በሶማሊያ ያሰማራችውን ጦሯን እንደምታስወጣ ገለጸች
ኢሳት (ኅዳር 12 ፥ 2009) በሶማሊያ ተሰማርቶ በሚገኘው የአፍሪካ ሰላም አስከባሪ ሃይል ውስጥ ወታደሮቿን አሰማርታ የምትገኘው ኬንያ ከሃገሪቱ ለቃ እንደምትወጣ ይፋ አደረገች። ሃገሪቱ ሶማሊያ የሚገኘውን ጦሯን በማስወጣት ስትወስን ሶስተኛ ሃገር ስትሆን፣ ዩጋንዳና፣ ቡሩንዲ በቅርቡ ተመሳሳይ ውሳኔን ማስተላለፋቸው ይታወሳል። በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት አምባሳደር ፍራንሲስኮ ካታኖ፣ የኬንያ የሰላም አስከባሪ ሃይል ከአንድ አመት በኋላ ከሶማሊያ ለቆ መውጣት እንደሚጀምር ለመገናኛ ...
Read More »በደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ እየተዛመተ ያለው የድርቅ አደጋ እንዳሳሰበው ተመድ ገለጸ
ኢሳት (ኅዳር 12 ፥ 2009) በደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ አካባቢዎች የተከሰተው አዲስ የድርቅ አደጋ ወደ አጎራባች ዞኖች በመዛመት ላይ መሆኑ ስጋት እንዳሳደረበት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በድጋሚ ገለጸ። በተለይ በኦሮሚያ ክልል ስር በሚገኙ የባሌ፣ ጉጂ፣ እና ቦረና ዞኖች በአዲስ መልክ የተከሰተው የድርቅ አደጋ በአካባቢው ከፍተኛ የውሃ እጥረት እንዲከሰት በማድረግ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት አደጋ ውስጥ እንደከተቱ ድርጅቱ አስታውቋል። ከደቡባዊ ምስራቅ የሃገሪቱ አካባቢዎች ...
Read More »የኢትዮጵያ ወታደሮች ከሶማሊያ ቁልፍ ወታደራዊ ይዞታዎች ለቀው የወጡት በሎጂስቲክ ችግር ምክንያትና ለስልታዊ ዕርምጃ ነው ተባለ
ኢሳት (ኅዳር 12 ፥ 2009) በሶማሊያ የሚገኙ የኢትዮጵያ ወታደሮች ቁልፍ ከተባሉ ወታደራዊ ይዞታዎች ለቀው የወጡት በሎጂስቲክ ችግር ምክንያትና ለስልታዊ ዕርምጃ መሆኑን የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። የሚኒስትሩ ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ተወልደ ሙሉጌታ አልሸባብ የተሰኘው የሶማሊያ ታጣቂ ሃይል የኢትዮጵያ ወታደሮች ለቀው የወጡ ስፍራዎችን መያዙ ለመንግስት ስጋት የለውም ሲሉ ለሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል። የሶማሊያ ባለስልጣናት እና የተለያዩ አካላት በሃገሪቱ የሚገኙ ...
Read More »አትላስ አፍሪካን ኢንዱስትሪስ ከኢትዮጵያ ለቆ መውጣቱ ተገለጸ
ኢሳት (ኅዳር 12 ፥ 2009) በቅርቡ የኢትዮጵያ መንግስት ከሁለት ሚሊዮን ዶላር በላይ የኢንቨስትመንት ገንዘብ ያለ አግባብ አግዶብኛል በማለት ቅሬታን ያቀረበ አንድ አለም አቀፍ ኩባንያ ከኢትዮጵያ ለቆ መውጣቱን ይፋ አደረገ። አትላስ አፍሪካን ኢንዱስትሪስ የተሰኘው ይኸው ኩባንያ ለራያ ቢራ አፍሪካ የቢራ ምርት ማሸጊያ ጠርሙሶችን ለማምረት ስምምነት አድርጎ የሽርክና ስራ ሲሰራ መቆየቱን አውስቷል። ይሁንና ኩባንያው የሽክርና ስራው በጀመረ በጥቂት ጊዜ ውስጥ የኢትዮጵያ ገቢዎች ...
Read More »አርበኞች ግንቦት7 በአዲ ጎሹ ፣ ቃፍታ ሁመራ አካባቢዎች ውጊያ ማካሄዱን አስታወቀ
ኅዳር ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከድርጅቱ ወታደራዊ ክፍል የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ባለፉት ሳምንታት የድርጅቱ ታጣቂዎች በቃፍታ ሁመራ፣ አዲ ጎሹና አርማጭሆ አካባቢዎች ከህወሃት/ኢህአዴግ ቃኝ ወታደሮች ጋር ተከታታይ የተኩስ ልውውጦችን አድርገዋል።በተኩስ ለውውጡ ከመንግስት በኩል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወታደሮች ሙት እና ቁስለኛ ቢሆንም፣ ከነጻነት ሃይሎች በኩል የደረሰውን ጉዳት ለማወቅ ድርጅቱ ምርመራ እያደረ መሆኑን ገልጿል። “የንቅናቄው ሃይሎች አንዳንድ ቦታዎችን ...
Read More »በደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ ከተማ የተጠራው ስብሰባ ሳይሳካ ቀረ
ኅዳር ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ኦሞ ዞን በጂንካ ከተማ የኢህአዴግ አባልና ደጋፊ የመንግሥት ሠራተኞችን ለይተው ‹‹በወቅታዊ ጉዳዮች›› ላይ ለማወያየት የተጠራው ስብሰባ ሠራተኛው በስብሰባው ላይ ለመገኘት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ሳይሳካ መቅረቱን የከተማው ሠረተኞች ገልጸዋል፡፡ ዛሬ ሰኞ ህዳር 12/2009 ዓ.ም ሁሉም የመንግሥት ሠራተኛ ወደ ሥራ ገበታው ሲገባ የቢሮ ኃላፊዎች የኢህአዴግ አባላትና ደጋፊዎች የሆኑትን ሠራተኞች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ...
Read More »በኢትዮጵያ ያለው ድርቅ እየተባባሰ ቢመጣም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እርዳታ ለማከፋፈል ሳንካ ፈጥሯል ተባለ
ኅዳር ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ቀውስ አጥኚ ቡድን ከ ኢትዮጵያ አደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኮሚሽን ጋር በመተባበር የድርቅ አደጋ ያንዣበባቸውን አካባቢዎች ለይተው አውጥተዋል። በደቡባዊ ምስራቅ ኢትዮጵያ አካባቢ አርብቶ አደሮች ለረሃብ አደጋ ተጋላጭ ሆነዋል። ለጉዳተኞቹ እርዳታዎችን ለማሰራጨት አስቸኳይ አዋጁን ተከትሎ የፀጥታ ችግሮች መኖራቸው እና መንገዶች ዝግ መደረጋቸው የሰዎችን ሕይወት ለመታደክ ከፍተኛ ሳንካ ፈጥሯል። ...
Read More »የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን ተከትሎ የታፈሱት ወጣቶች ይፋዊ ባልሆኑ እስር ቤቶች ታስረዋል
ኅዳር ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን ተከትሎ ከተለያዩ የሃገሪቱ ስፍራዎች ታፍሰው የታሰሩት እስረኞች ገሚሶቹ በአዋሽ አርባ፣ በኦሮሚያ ፖሊስና በቀድሞው ህጻናት አምባ አሁን አላጌ የግብርና ኮሌጅ በመባል በሚጠራው ስፍራ እንደሆነ ታውቋል። መንግስት አዋጁን ለማስከበር በሚል ከ20ሺ እስከ 30ሺ ይደርሳል ተብሎ የሚገመቱ ታሳሪዎችን ቤተሰብና ዘመድ ሊያውቀው በማይችልበት ስፍራ ወስዶ ማሰሩ በታሳሪዎቹ ላይ የስነ ልቦና ጫና ...
Read More »