ኢሳት (ኅዳር 15 ፥ 2009) በሱዳን የተከሰተን የሸቀጣሸቀጦች ዋጋ ንረት ተከትሎ በርካታ ተማሪዎች ሃሙስ በመዲናይቱ ካርቱም የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ። የሃገሪቱ የጸጥታ ሃይሎች የተቃውሞ ሰልፍን ለመበተን በወሰዱት ዕርምጃ፣ ግጭት ተቀስቅሶ ቁጥራቸው ሊታወቅ ያልቻለ ሰዎች ለእስር መዳረጋቸውን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል ። ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ ተማሪዎች የሱዳን መንግስት የሸቀጣቀጦች ዋጋ ንረት እንዲረግብ እርምጃን መውሰድ እንዳለበት መጠየቃቸውን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል። መንግስት በተለይ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በአማራ ክልል የተከሰተው ህዝባዊ ተቃውሞ ጸረሰላም ሃይሎች የፈጠሩት ነው ሲል የአማራ ክልል ምክር ቤት ገለጸ
ኢሳት (ኅዳር 14 ፥ 2008) የአማራ ክልል ምክር ቤት በክልሉ የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ የመልካም አስተዳደር ችግርና ጸረ-ሰላም ሃይሎች የፈጠሩት ችግር ነው በሚል ከተወያየ በኋላ የካቢኔ ሹም ሽር በማድረግ ተጠናቀቀ። በአቶ አንዳርጋቸው ገዱ ቀርበው በምክር ቤቱ ከጸደቁት 22 የቢሮ ሃላፊዎች 10ሩ ነባር ሃላፊዎች ሲሆኑ፣ 12 ደግሞ አዳዲሶች ናቸው። ከ12ቱ አዳዲስ የቢሮ ሃላፊዎች 6ቱ በአማራ ክልል ዩኒቨስቲዎች ሲያስተምሩ የነበሩ ሲሆኑ፣ የብዓዴን አባላት ...
Read More »በተለያዩ የሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ውጊያዎች በመካሄድ ላይ ናቸው
ኅዳር ፲፬ (አሥራ አራት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ዛሬ በአብድራፊ አንገረብ ወንዝ አካባቢ ራሳቸውን ባደራጁ የነጻነት ሃይሎች እና በገዢው ፓርቲ ወታደሮች መካከል ከፍተኛ ውጊያ ተካሂዷል። ዛሬ ሲካሄድ በዋለው ውጊያ በነጻነት ሃይሎችም ሆነ በገዢው ፓርቲ ወታደሮች ላይ ስለደረሰው ጉዳት የታወቀ ነገር የለም። በሌላ በኩል በወልቃይት ትርካንና ማይነብሪ አካባቢ በአርበኞች ግንቦት7 ወታደሮችና በመንግስት ታጣቂዎች መካከል መለስተኛ ውጊያ ...
Read More »በጂማ ዩኒቨርስቲ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ተማሪዎች ሌሊቱን ሲደበደቡ አደሩ
ኅዳር ፲፬ (አሥራ አራት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት በቲቶ ፉርጊሳ የምህንድስና ትምህርት ክፍል የሚማሩ ተማሪዎች የጀመሩትን ተከታታይ ተቃውሞ ተከትሎ፣ ወታደሮች ተማሪዎችን ከምሽቱ 2 ሰአት ላይ በማውጣት እስከ ሌሊቱ 11 ሰአት ድረስ እየደበደቡ ከፍተኛ ኢ ሰብአዊ ድርጊት ፈጽመዋል። የኮማንድ ፖስትን በመወከል ተማሪውን ዛሬ የሰበሰቡ አካላት ከፍተኛ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል። እንደ ተማሪዎቹ ገለጻ የኮማንድ ፖስት ወኪሎች ‹‹ አርፈን ...
Read More »በሃረር በርካታ ዜጎች ሲታሰሩ በባህርዳር ደግሞ ፖሊሶች በቁጥጥር ስር ዋሉ
ኅዳር ፲፬ (አሥራ አራት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመጪው ህዳር 29 ቀን 2009 ዓም ከሚከበረው የብሄር ብሄረሰቦች በአል ጋር በተገናኘ ይሁን አይሁን ባይታወቅም፣ በሃረር ከተማ ከፍተኛ ፍተሻ በመካሄድ ላይ ሲሆን፣ በፍተሻ ወቅት የክልሉን መታወቂያ ያልያዙ ሰዎች እየተያዙ ወደ እስር ቤት ተወስደዋል። ከሌሎች ክልሎች ሄደው በክልሉ ውስጥ በመስራት ላይ ያሉ በርካታ ዜጎች፣ የክልሉን መስተዳድር መታወቂያ እንዲሰጣቸው ቢጠይቁም፣ ከመጣችሁበት ክልል ...
Read More »በቂሊንጦ እስር ቤት በእሳት ቃጠሎ እና በጥይት ለተገደሉ ታራሚዎች ሞት 38 እስረኞች ተጠያቂ ሆኑ
ኅዳር ፲፬ (አሥራ አራት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ዓመት ነሃሴ 28 ቀን 2008 ዓ.ም ሆን ተብሎ የእሳት ቃጠሎ እንዲነሳ በማድረግ ከእሳቱ ለመሸሽ ሲያመልጡ የነበሩ ታራሚዎች በእሳት ቃጠሎ እና በግፍ በጥይት ተደብድበው መገደላቸው የሚታዉቅ ሲሆን ለዜጎች ሞት ምክንያት ናቸው የተባሉ 38 እስረኞች በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ዛክስ ተመስርቶባቸዋል። እስረኞቹ ሆን ብለው እሳት እንዲነሳ ያደረጉት በድብቅ ...
Read More »አልሸባብን ለማስወጣት ተጨማሪ 4 ሺ ወታደሮች ያስፈልጋሉ ተባለ
ኅዳር ፲፬ (አሥራ አራት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተባበበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ሰላም አስከባሪ አሚሶም ስር የተሰማራው ጦር፣ በአሁኑ ወቅት አልሸባብ ከተቆጣጠራቸው የሶማሊያ ግዛቶች ለማስወጣት ተጨማሪ 4 ሺህ ወታደሮች ማሰማራት እንደሚያስፈልጉት አስታውቋል። ጁባ ሸለቆ፣ ሂራን፣ በቆል እና አንዳንድ የተወሰኑ የድንበር ከተሞች በአልሸባብ ቁጥጥር ስር ውለዋል። የኅብረቱ ጦር ቃል አቃባይ የሆኑት ኮሎኔል ጆሴፍ ጊበርት እንዳሉት አሁን ካሉ 21 ሽህ ...
Read More »በአርማጭሆ ሳንጃ ወረዳ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ቀጥሏል
ጎንደር ከተማ የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ወታደራዊ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ቀጥሏል። በአርማጭሆ ሳንጃ ወረዳ ረቡዕ ዕለት አንድ የጭነት መኪና በተወሰደበት ዕርምጃ መቃጠሉንም የአይን ዕማኞች ገልጸዋል። በተበታተነ መልኩ ሲካሄዱ የነበሩ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች በአንድ ዕዝ በተቀናጀ መንገድ እንዲካሄዱ ስምምነት ላይ መደረሱንም በበረሃ የሚገኙት ታጣቂዎች ከኢሳት ጋር ባካሄዱት ቃለ-ምልልስ ገልጸዋል። በሰሜን ኢትዮጵያ በአማራ ክልል በተለይም በሰሜን ጎንደር በየአካባቢው ተደራጅተው በጎበዝ ...
Read More »አንድ እንግሊዛዊ አብራሪ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ከገባ በኋላ የገባበት አለመታወቁ ተነገረ
ኢሳት (ኅዳር 14 ፥ 2009) እድሜ ጠገብ በሆኑ አውሮፕላኖች በሚደረገ ውድድር ላይ ተሳታፊ የነበረ አንድ የብሪታኒያ ፓይለት ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ከገባ በኋላ የገባበት አለመታወቁን የውድድሩ አዘጋጆች ረቡዕ አስታወቁ። የ72 አመቱ ሞሪስ ኪርክ የአፍሪካ ጉዞን በሚሸፍነው ውድድሩ ከጎረቤት ሱዳን ወደ ኢትዮጵያ የጋምቤላ ክልል በመጓዝ ላይ እያለ ግንኙነቱ ተቋርጦ ያለበት ሁኔታ አለመታወቁን ዴይሌ ሜይል ጋዜጣ ዘግቧል። የ72 አመቱ ፓይለት በውድድሩ እያለ እንደ ...
Read More »38 እስረኞች በቂሊንጦ እስር ቤት እሳት በማስነሳት ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው
ኢሳት (ኅዳር 14 ፥ 2009) በቅርቡ በቂሊንጦ እስር ቤት የደረሰን የእሳት አደጋ እንዲነሳ አድርገዋል የተባሉ 38 እስረኞች ክስ ተመሰረተባቸው። ከሳሽ አቃቢ ህግ 38ቱ ተከሳሾች ከጥር ወር 2008 ዓም ጀምሮ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ግንቦት ሰባትና፣ በአልሸባብ የሽብር ቡድን ተልዕኮ ለመፈጸም በእስር ቤቱ በተለያዩ ወንጀሎች በእርማት ላይ ያሉ እስረኞችን በድብቅ በመመልመል አመጽ ለመፍጠር መረጃን ሲለዋወጡ ነበር ሲል በክሱ አመልክቷል። ይሁንና ተከሳሾቹ ...
Read More »