.የኢሳት አማርኛ ዜና

ቻይና በጅቡቲ ወታደራዊ ጣቢያን ለማቋቋም መወሰኗ በህንድ ላይ ስጋት አሳድሯል ተባለ

ኢሳት (ኅዳር 16 ፥ 2009) ቻይና በጎረቤት ጅቡቲ የባህር ሃይል ወታደራዊ ጣቢያን ለማቋቋም መወሰኗ በህንድ በኩል የደህንነት ስጋት ማሳደሩ ተገለጠ። የቻይና ወታደራዊ ባለስልጣናት በበኩላቸው ሃገሪቱ በጅቡቲ እየገነባች ያለው ይኸው ወታደራዊ የማዘዣ ጣቢያ ለሰላም ማስከበርና በሰብዓዊ ዕርዳታ ስራዎች እገዛን የሚያደርግ መዕከል እንደሆነ አስታውቃለች። በተያዘው ሳምንት በጅቡቲ ጉብኝትን ያደረጉ ከፍተኛ የቻይና ወታደራዊ ባለስልጣናት ሃገራቸው ቁልፍ ይዞታ ላይ ትገኛለች በምትባለው ጅቡቲ ወታደራዊ ይዞታን ...

Read More »

በሶማሊያ የተሰማራው ሰላም አስከባሪ ሃይል በአልሸባብ የተያዙ ቦታዎችን ለማስለቀቅ 40ሺ ወታደሮች ያስፈልጉኛል አለ

ኢሳት (ኅዳር 16 ፥ 2009) የኢትዮጵያ ወታደሮች ከሶማሊያ መውጣታቸውን ተከትሎ የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ልዑክ በአልሸባብ ታጣቂ ቡድን የተያዙ ቦታዎችን ነጻ ለማውጣት ተጨማሪ ከ40ሺ በላይ ወታደሮች እንደሚያስፈልጉት ገለጸ። የሰላም አስከባሪ ልዑክ በአሁኑ ሰዓት ወደ 21ሺ አካባቢ የሰላም አስከባሪ አባላት ቢኖሩትም ሁሉንም የአልሸባብ ይዞታዎችን ለመቆጣጠርና መልሶ ለመያዝ አለመቻሉን የልዑኩ ሃላፊዎች ዋቢ በማድረግ ዘ-ኢስት አፍሪካን የተሰኘ ጋዜጣ ዘግቧል። የልዑኩ ቃል አቀባይ የሆኑት ...

Read More »

በጋምቤላ የአየር ክልል ጥሰዋል ተብለው በቁጥጥር ስር የነበሩ ፓይለቶች ፈቃድ ተሰጥቷቸው እንደነበር ይፋ አደረጉ

ኢሳት (ኅዳር 16 ፥ 2009) በጋምቤላ ክልል በህገወጥ መንገድ የሃገሪቱን የአየር ክልል ጥሳችሁ ገብታችኋል ተብለው በቁጥጥር ስር የነበሩ የተለያዩ ሃገራት ፓይለቶች የመንግስት ፈቃድ ተሰጥቷቸው እንደነበር ይፋ አደረጉ። በውድድር ላይ የነበሩት እነዚሁ ከ40 የሚበልጡ ፓይለቶች የኢትዮጵያ አቪየሽን ባለስልጣን ሊያደርጉ ለነበረው የአውሮፕላን በረራ ፈቃድ ሰጥቷቸው እንደነበር መግለጻቸውን ዴይሊ ሜይል የተሰኘ የብሪታኒያ ጋዜጣ ዘግቧል። ይሁንና ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለፓይለቶቹ ቡድን ፈቃድን ከሰጠ በኋላ ...

Read More »

አቶ ጌታቸው አምባዬ በታይላንድ ባንኮክ በከፍተኛ ህክምና ላይ መሆናቸው ተገለጸ

ኢሳት (ኅዳር 16 ፥ 2009) በቅርቡ ጠ/ሚኒስትር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ባወቀሩት ካቢኔ ውስጥ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሆነው የተሾሙት አቶ ጌታቸው አምባዬ ከተሾሙበት ጊዜ ጀምሮ በስራ ገበታቸው ላይ አለመሆናቸው ታወቀ። የቅርብ ምንጮች እንደገለጹት ባለስልጣኑ በታይላንድ ባንኮክ በከፍተኛ ህክምና ላይ ይገኛሉ። ሹመቱ የተሰጣቸው በውጭ ሃገር በህክምና ላይ መሆናቸው እየታወቀ መሆኑን መረዳት ተችሏል። በቅርቡ ጥቅምት 22 ቀን 2009 ዓም በተዋቀረው ካቢኔ ውስጥ በነበሩት ...

Read More »

በአርበኞች ግንቦት7 ታጋዮችና በአገዛዙ ወታደሮች መካከል የሚካሄደው ጦርነት እንደቀጠለ ነው

ኅዳር ፲፭ (አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜን ጎንደር በአርማጭሆና ሌሎችም ቦታዎች በአርበኞች ግንቦት7 ሃይሎች እና በህወሃት/ኢህአዴግ ወታደሮች መካከል የሚካሄደው ጦርነት ዛሬም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን፣ የአርበኞች ግንቦት 7 አንድ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ መከበቡብ እንዳወቀ ራሱን ሰውቷል። ቀደም ብሎ በኢህአዴግ መከላከያ ውስጥ ሲያገለግል ቆይቶ፣ በስራዊቱ ውስጥ ያለውን ዘረኝነትና በህዝቡ ላይ የሚፈጸመውን ግፍ መቋቋም ተስኖት፣ አርበኞች ግንቦት 7ትን የተቀላቀለው ...

Read More »

ወታደራዊ እዙ ( ኮማንድ ፖስት) በአዳማ ተቃውሞ ገጠመው

ኅዳር ፲፭ (አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ሳምንት ከሰኞ እስከ ዓርብ ኢህአዴግና የከተማው መስተዳድር በአዳማ ከተማ ከኢህአዴግ አባላትና ደጋፊ የከተማው ነዋሪዎች ጋር ስለ ወታደራዊ እዙ ተግባርና ኃላፊነት፣ ስለተደረገው ሹም ሽር እንዲሁም የክልሉንና የከተማዋን ልማትና ጸጥታ ሁኔታ በሚመለከት በተደረገው ስብሰባ ላይ ያልተጠበቀ ተቃውሞ ተነስቷል። በዚህ መድረክ የተሳተፉት የኢህአዴግ አባላትና ደጋፊዎች ቢሆኑም የከተማዋ የኮማንድ ፖስት ኃላፊ ማንነት እንደተገለጸ ...

Read More »

በባህር ዳር ከተማ በአንዳንድ አካባቢዎች የሚደረጉት ፍተሻዎች የህብረተሰቡን ኑሮ እያወኩ መሆኑን ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

ኅዳር ፲፭ (አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰሞኑን በባህርዳር ከተማ በተለያዩ ቦታዎች በሚደረጉ ፍተሻዎች ነዋሪው እየታወከ መሆኑን  በባህርዳር የጣናና ሽምብጥ ክፍለከተማ ነዋሪዎች ለኢሳት ተናገሩ፡፡ በውድቅት ሌሊት የመንግስት ወታደሮችና ታጣቂዎች በወደ ግለሰቦች ቤት በመግባት ‹‹ፍተሻ እናካሂዳለን!!›› በማለት ከሌሊት እስከ ንጋት ድረስ ሲያንገላቷቸው ያድራሉ፡፡በተለይ በጣና ክፍለ ከተማ ቀጠጢና በተባለ መንደር የሚገኙ ነዋሪዎች እንደተናገሩት፣ ከንጋቱ አስራ አንድ ሰዓት ወደ ሆቴል ...

Read More »

የኢትዮጵያና የኬንያ የጸጥታና ደህንነት ባለስልጣናት በሞምባሳ ውይይት እያካሄዱ ነው

ኢሳት (ኅዳር 15 ፥ 2009) በቅርቡ በኢትዮጵያና በኬንያ ድንበር አካባቢ የተካሄደን ግጭት ተከትሎ የሁለቱ ሃገራት ተወካዮች በኬንያ ሞምባሳ ከተማ የጸጥታና ደህንነት ውይይት በማካሄድ ላይ መሆናቸው ተገለጸ። ኢትዮጵያ የኦሮሞ ነጻነት ግንባት (ኦነግ) ታጣቂዎችን ለመያዝ በሚል በተደጋጋሚ የኬንያን ድንበር እየጣሰች መግባቷ በኢትዮጵያና ኬንያ መካከል ዲፕሎማሲያዊ አለመግባባት መፍጠሩን የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።  ባለፈው ወር የኬንያ ድንበር ጥሰው የገቡ የኢትዮጵያ ወታደሮች ስድስት የኬንያ ፖሊሶችን ...

Read More »

በአውሮፕላን ውድድር ላይ የነበሩና ከኢትዮጵያ እንዳይወጡ የተደረጉ የውጭ ዜጎች እንዲለቀቁ ውይይት እየተደረገ ነው ተባለ

ኢሳት (ኅዳር 15 ፥ 2009) የአሜሪካና የብሪታኒያ ባለስልጣናት ከኢትዮጵያ እንዳይወጡ የተደረጉና በአውሮፕላን ውድድር ላይ የነበሩ የተለያዩ ሃገራት ዜጎች እንዲለቀቁ ውይይት በማድረግ ላይ መሆናቸውን ሃሙስ አስታወቁ። የተለያዩ ሃገራት ዜግነት ያላቸው እነዚሁ ቁጥራቸው ያልተገለጸ ፓይለቶች አፍሪካን በሚሸፍን  የአውሮፕላን ውድድር ላይ የነበሩ አዘጋጆች ለመገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል። የውድድሩ አዘጋጆች ረቡዕ አንድ ብሪታኒያዊ ፓይለት ከሱዳን ወደ ጋምቤላ ክልል በመጓዝ ላይ እንዳለ ደብዛው መጥፋቱን አስታውቆ እንደነበር ...

Read More »

ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ለህገወጥ የሰዎች ዝውውር አደጋ በመጋለጥ ላይ  ናቸው ተባለ

ኢሳት (ኅዳር 15 ፥ 2009) የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድገት መቀዝቀዝ ማሳየቱን ተከትሎ በርካታ የሃገሪቱ ሴቶች ለህገወጥ የሰዎች ዝውውር አደጋ በመጋለጥ ላይ መሆናቸውን ሮይተርስ የተለያዩ አካላትን ዋቢ በማድረግ ሃሙስ ዘግበ። በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ችግር ዙሪያ ጥናትን የሚያካሄደው ዎክ ፍሪ የተሰኘ ተቋም በበኩሉ ከ400ሺ የሚበልጡ ኢትዮጵያውያን የባርነት አይነት ህይወት ውስጥ እንደሚገኙ በ2016 ረፖርቱ አስፍሯል። በኢትዮጵያ የሚኖሩ አብዛኞቹ ሴቶች በረሃብ፣ በህመም፣ በድህነትና ተያያዥ በሆኑ ...

Read More »