.የኢሳት አማርኛ ዜና

በነጻነት ሃይሎች እና በህወሃት/ኢህአዴግ  ወታደሮች መካከል የሚካሄደው ውጊያ እንደቀጠለ ነው

ኅዳር ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዳባት ወረዳ ድልድይና መንደርጌ አካባቢ በህዝብ በሚደገፉ የነጻነት ሃይሎችና በህወሃት/ኢህአዴግ ወታደሮች መካከል የተጀመረው ውጊያ ዛሬም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን፣ በአገዛዙ ወታደሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ህዝብ ሙሉ በመሉ ድጋፉን እየሰጠ ባለው ጦርነት ቁጥራቸው በውል ያልተገለጸ የአገዛዙ ወታደሮች መገደላቸውንና የጦር መሳሪያዎችን መማረካቸውን ምንጮች ገልጸዋል። በርካታ ወታደሮችን የጫኑ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ...

Read More »

በፍኖተሰላም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወታደሮች ሰፈሩ

ኅዳር ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የከተማዋ ነዋሪዎች እንደገለጹት በደንብ የታጠቁ ወታደሮች ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ ወደ ከተማው የገቡ ሲሆን፣ የጃቢ ጠናን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጽ/ቤት ግቢን ካምፕ አድርገውታል። በከተማው በብዛት የሚታዩት ወታደሮች ናቸው የሚሉት ነዋሪዎች፣ እነሱ ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ በከተማው ውጥረት መጨመሩን ነዋሪዎች ገልጸዋል። ወላጆችን “ልጆቻችሁን በጊዜ ወደ ቤታችሁ አስገቡ” እያሉ መሆኑን የተናገሩት ነዋሪዎች፣ ህዝቡ መታወቂያ እንዲያሳይ ...

Read More »

የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ በስዊድን የተሳካ ስብሰባ ማካሄዱን ገለጸ

ኅዳር ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በ4 የፖለቲካ ድርጅቶች የተመሰረተው የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ትናንት እሁድ በስቶክሆልም ከተማ የተሳካ ስብሰባ ማድረጉን ገልጿል። የአርበኞች ግንቦት7 መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር መሪ አቶ ሌንጮ ለታ እንዲሁም የአፋር ህዝብ ፓርቲ መሪ ዶ/ር ኮንቴ ሙሳ በስብሰባው ላይ የተገኙ ሲሆን፣ ስብሰባው በስቶክሆልም /ስዊድን የንቅናቄው አስተባባሪ አቶ ዘለሌ ጸጋ ስላሴ ንግግር ...

Read More »

በደቡብ ኮሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የኢሳትን 6ኛ አመት አከበሩ

ኅዳር ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያኑ በሴውል ከተማ በመሰባሰብ በአሉን ያከበሩ ሲሆን፣ በበአሉ ላይ የኢሳት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ አበበ ገላው በስካይፕ ተገኝቶ ንግግር አድርጓል። ኢትዮያውያኑ ኢሳትን በቋሚነት ለመደገፍ ቃል መግባታቸውን ከስፍራው የደረሰን ዜና ያመለክታል። ተመሳሳይ የኢሳት ስድስተኛ አመት ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን በእንግድነት በተገኘበት በፍራንክፈርት ፣ ጀርመን ተከበሯል።

Read More »

በዳባት ወረዳ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ታጋዮች ከህወሃት ወታደርጎች ጋር ከፍተኛ ውጊያ ማካሄዳቸው ተገለጸ

ኢሳት (ኅዳር 17 ፥ 2009) በዳባት ወረዳ በጃኖራ ቀበሌ ልዩ ስሙ መንደርጌ ተብሎ በሚጠራ ቦታ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ታጋዮች ከህወህት ወታደሮች ጋር ከፍተኛ ወጊያ በትናንትናው ዕለት እንዳካሄዱ የአካባቢው ምንጮች ለኢሳት ገለጹ። ህወሀት በውጊያው ያሰለፋቸው ወታደሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት በመድረሱ አጋዥ ሀይል ለማስገባት እንቅስቃሴ ላይ ማደርጉ ታውቋል። ህወሃት በጭላ ማርያም እና በበንከር ልደታ በኩል ተጨማሪ ወታሮችን ለማስገባት የሞከረ ሲሆን ...

Read More »

በሰሜን ጎንደር ከፍተኛ ጦርነት ሲካሄድ ዋለ

ኅዳር ፲፮ (አሥራ ስድስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ጎንደር ታች አርማጭሆ  ሳንጃ እና በጠገዴ ወረዳ ግጨው እንዲሁም ልዩ ስሙ ሃመረ በተባለ ቦታ ላይ የነጻነት ሃይሎች እና በገዢው ፓርቲ ወታደሮች መካከል ሲካሄድ በዋለው ጦርነት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የህወሃት /ኢህአዴግ ወታደሮች መገደላቸው ታውቛል። ከሁመራ ወደ ቀራቀር በሚወሰደው መንገድ ላይ ቁስቋም ማሪያም አካባቢ በሚገኝ ዳገት ላይ፣ በወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ አባል ...

Read More »

የጎንደር ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተደብድበው ታሰሩ

ኅዳር ፲፮ (አሥራ ስድስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጎንደር ዩኒቨርሲቲ  የእንስሳት ህክምና (ቬተርናሪ ሳይንስ) ፋካልቲ የሚማሩ ተማሪዎች የምንማረው ትምህርት ስራ የማ  ያሲዘንና የስራ እድል የማይፈጥር ነው በማለታቸው ብቻ   ወታደሮች  ፣ የፌደራል ፖሊስ ፣ የፀረ -ሽምቅ አባላትና መደበኛ ፖሊሶች ወደ ግቢው በመግባት ተማሪዎችን ደብድበዋል። ከ100 በላይ ተማሪዎች ታፍነው በ2 አውቶብሶች ተጭነው  ወደ ሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ የተወሰዱ ሲሆን፣ ወታደሮች በአራቱም መአዘኖች  ...

Read More »

በሶማሊያ በተፈጠረው የእርስ በርስ ጦርነት እና ድርቅ ምክንያት ዜጎች ወደ ዶሎ አዶ እየተፈናቀሉ ነው

ኅዳር ፲፮ (አሥራ ስድስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሶማሊያ ያገረሸውን የእርስበርስ ጦርነት እና ድርቅ ሸሽተው ከሶማሊያ የተሰደዱ ተፈናቃዮች በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ አሳዋኝ ወደምትገኘው ዶሎአዶ ከተማ እየፈለሱ መሆኑን ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን አስታውቋል። ግጭቱን ሸሽተው ለመጡ ተፈናቃዮች በዶሎ ጤና ጣቢያ የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ሲሆን  ሕጻናት እና አዛውንት ለ ከፍተኛ ስቃይ መዳረጋቸውን ተገልጿል።

Read More »

በሰሜን ኢትዮጵያ የተጀመረው ውጊያ እንደቀጠለ ነው ፥ ከሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ህልፈት ጋር በተያያዘ ኢሳት በሰበር ዜናው ለተያያዘው ምስል ይቅርታ ጠየቀ

ኢሳት (ኅዳር 16 ፥ 2008) ከአርበኞች ግንቦት 7 የጦር አዛዦች አንዱ በሆነው በሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ህልፈት የለውጥ ደጋፊዎች ሃዘንና ቁጭታቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው። በሌላም በኩል በሰሜን ኢትዮጵያ የተጀመረው ውጊያ አሁንም መቀጠሉን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል። ከሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ህልፈት ጋር በተያያዘ ኢሳት በሰበር ዜናው ለተያያዘው ምስል ዝግጅት ክፍሉ የሟቹ ቤተሰቦቹንና ተመልካቾቹን ይቅርታ ጠየቀ። የቀድሞ የደርግ መንግስት ለመጣል በተደረገው ትግል በብዓዴን/ኢህአዴግ ትግል ...

Read More »

ቱርክ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ስደተኞችን ወደ አውሮፓ እንዲገቡ ልታደርግ ትችላለች ተባለ

ኢሳት (ኅዳር 16 ፥ 2009) ቱርክ ለአውሮፓ ህብረት አባልነት ለመደራደር የተገባላት ቃል ተግባራዊ አለመደረጉን ተከትሎ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ስደተኞችን ወደ አውሮፓ እንዲገቡ ልታደርግ እንደምትችል አሳስባለች። ባለፈው አመት የሶሪያ ስደተኞች ቱርክን በመጠቀም ወደ ተለያዩ የአውሮፓ ሃገራት ሲገቡ የነበረ ሲሆን፣ ህብረቱ ቱርክ ሰደተኞቹን በሃገሩ እንድታቆይ የጥቅማ-ጥቅም ቃል ገብቶ እንደነበር ይታወሳል። ቱርክ የሃገሩ ዜጎች ያለ ቪዛ ወደ አውሮፓ እንዲገቡና ሃገሪቱ የአውሮፓ ህብረት አባል ...

Read More »