ኢሳት (ህዳር 20 ፥ 2009) ኢትዮጵያ ከጎረቤት ደቡብ ሱዳን ጋር በምታዋስንበት የጋምቤላ ክልል ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ የጸጥታ ሃይል ማስፈሯ ተገለጠ። ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ያለፈቃድ በጋምቤላ ክልል በኩል ወደ ሃገር ገብተዋል ስለተባሉ የአውሮፕላኖች ዘገባን ያቀረበው ጄኔራል አቪየሽን መጽሄት በጋምቤላ ክልል ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ የጸጥታ ሃይል ተሰማርቶ እንደሚገኝ አመልክቷል። በቅርቡ በደቡብ ሱዳን በአዲስ መልክ የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎ ኢትዮጵያ ከሃገሪቱ ጋር በምትዋሰንበት የድንበር ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የብራዚል የእግር ኳስ አባላት ይዞ ይጓዝ የነበረ አውሮፕላን በኮሎምቢያ በመከስከሱ 76 ሰዎች ሞቱ
ኢሳት (ህዳር 20 ፥ 2009) ከ80 በላይ የብራዚል የእግር ኳስ አባላትና መንገደኞችን ይዞ ይጓዝ የነበረ አውሮፕላን በኮሎምቢያ የመከስከስ አደጋ ደርሶበት 76 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ተገለጠ። ማክሰኞ ጠዋት አደጋ ያጋጠመው የመንገደኞች አውሮፕላን መነሻውን ከብራዚል አድርጎ በቦሊቪያ በኩል ወደ ኮሎምቢያ በማቅናት ላይ እንደነበር ቢቢሲ ዘግቧል። አንድ የብራዚል የእግር ኳስ ቡድን ሙሉ አባላትን ይዞ የነበረው ይኸው አነስተኛ አውሮፕላን በሰሜናዊ ምዕራብ ኮሎምቢያ ተራራማ አካባቢ ...
Read More »በጋምቤላ ሲያለሙ የነበረውን መሬት ለመንግስት ያስረከቡ ባለሃብቶች መንግስት በጉዳዩ ላይ እልባት ባለመስጠቱ ቅሬታ አቀረቡ
ኢሳት (ህዳር 20 ፥ 2009) በጋምቤላ ክልል በስህተት የእርሻ ቦታ ተሰጥቷችኋል ተብለው በማልማት ላይ የነበሩትን የመሬት ይዞታ እንዲያስረክቡ የተደረጉ ባለሃብቶች መንግስት ለአንድ አመት ያህል ዕልባት አልሰጠንም ሲሉ ቅሬታን አቀረቡ። የግብርና ሚኒስቴር በሃገሪቱ በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ የተሰማሩ ኩባንያዎች ለአባይ ግድብ ግንባታ በሚያደርጉት ድጋፍ ዙሪያ ከቀናት በፊት በአዲስ አበባ የውይይት መድረክ ቢጠራም ተሳታፊዎቹ ለባለስልጣናት ተቃውሞ በማቅረባቸው ሳቢያ ውይይቱ ሳይሳካ መቅረቱን በሃገር ውስት ...
Read More »ወደ የመን የሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር እንዳሳሰበው ተመድ ገለጸ
ኢሳት (ህዳር 20 ፥ 2009) ጦርነት እልባት ወዳላገኘባት የመን የሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ስጋት አሳድሮበት እንደሚገኝ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን ማከሰኞ ገለጸ። አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን የሆኑት 106ሺ ስደተኞች በተያዘው የፈረንጆቹ 2016 አም ወደ የመን መሰደዳቸውን ኮሚሽኑ ያስታወቀ ሲሆን፣ ቁጥሩ ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር በ13ሺ በልጦ መገኘቱ ታውቋል። ወደ የመን ለመሰደድ ሙከራን ካደረጉ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያና የሶማሊያ ስደተኞች መካከል በትንሹ 79 ስደተኞች በተያዘው ...
Read More »ህብር ስኳር ፋብሪካ እንዲፈርስ ጥያቄ ቀረበ
ኢሳት (ኅዳር 19 ፥ 2009) ህብር ስኳር አክሲዮን ማህበር እንዲፈርስ ለፍርድ ቤት ማመልከቻ መቅረቡን በሃገር ውስጥ የሚታተሙ ጋዜጦች ዘገቡ። በማህበሩ ውስጥ ከፍተኛ ድርሽ ያላቸው ከሰባት የሚበልጡ ባለ አክሲዮኖች ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ያቀረቡት አቤቱታ እንደሚያስረዳው ፋብሪካውን ለመገንባት ከአባላት መዋጮና እና ከባንክ ገንዘብ ለማግኘት እምነት የነበረ ቢሆም ሊሳካ አልቻለም። ከአንድ መቶ ሚሊዮን ብር በላይ ከአክሲዮን ሽያጭ የሰበሰበው ህብር ስኳር ከመንግስት ...
Read More »ስዊድን በኢትዮጵያ በእስር ላይ የሚገኙ የዶ/ር ፍቅሩ ማሩ የጤና ሁኔታ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱ ገለጸች
ኢሳት (ኅዳር 19 ፥ 2009) ስዊድን በኢትዮጵያ በእስር ላይ የሚገኙ ዜጋዋ የጤና ሁኔታ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱ ስጋት እንዳሳደረባት ገለጸች። የስዊድን ዜግነት ያላቸውና የልብ ቀዶ ህክምና አገልግሎት ላይ ለመስራት ከጥቂት አመታት በፊት ወደ ኢትዮጵያ ገብተው የነበሩት ዶክተር ፍቅሩ ማሩ ከሶስት አመት በፊት ከሙስና ወንጀል ጋር በተያያዘ ለእስር መዳረጋቸው ይታወሳል። በፌዴራል አቃቤ ህግ የተመሰረተባቸውን ክስ ሲከታተል የነበረው ፍርድ ቤት ባለፈው ወር የህክምና ...
Read More »የሱዳን ህዝቦች የነጻነት ንቅናቄ ኢትዮጵያ፣ ኬንያና አሜሪካ ከተደረሰው ስምምነት ውጭ እየሄዱ ነው በማለት ድርጊቱን አወገዘ
ኢሳት (ኅዳር 19 ፥ 2009) የሱዳን ህዝቦች የነጻነት ንቅናቄ ኢትዮጵያ፣ ኬንያና አሜሪካ የሱዳን ህዝቦች ነጻነት ንቅንናቄ አማጺ ቡድን መሪ ሪክ ማቻር ከሰላም ስምምነት እንዲወጡ አድርገዋል ሲል ድርጊቱን አወገዘ። ባለፈው ሳምንት ማቻር ወደ ኢትዮጵያ ከገቡ በኋላ ወደ መነሻቸው ደቡብ አፍሪካ እንዲመለሱ መደረጉን አስመልክቶ መግለጫን ያወጣው ንቅናቄ ሶስቱ ሃገራት ሪክ ማቻርን ከተደረሰው የሰላም ስምምነት ውጭ ሊያደርጓቸው እንቅስቃሴን እያደረጉ እንደሆነ ገልጸዋል። ኢትዮጵያን ጨምሮ ...
Read More »በዩጋንዳ በተቀሰቀሰው ግጭት ከ55 ሰዎች በላይ ተገደሉ
ኢሳት (ኅዳር 19 ፥ 2009) በዩጋንዳ መንግስትና በታጣቂዎች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት በትንሹ 55 ሰዎች መገደላቸውንና በድርጊቱ በሃገሪቱ ውጥረት ማንገሱ ተገለጠ። የዩጋንዳ ፖሊስ በበኩሉ ቅዳሜ የተከሰተውን ይህንኑ ግጭት ተከትሎ ከድርጊቱ ግንኙነት ያላቸው የጎሳ ንጉስ ለእስር መዳረጉን የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የርዌንዙሩሩ ጎሳ ንጉስ ቻርለስ ዊስሊ ምምቤሬ ለሁለት ቀን ዘልቆ ከነበረው ግጭት ጋር ግንኙነት እንደሌላቸው አስተባብለዋል። በዩጋንዳ የጸጥታ ሃይሎችና ንጉሱን ይደግፋሉ በሚባሉ ...
Read More »የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚደንት ጃኮብ ዙማ ከስልጣናቸው እንዲነሱ ተጠየቁ
ኢሳት (ኅዳር 19 ፥ 2009) የሙስና ክስ እየቀረበባቸው የሚገኙት የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚደንት ጃኮብ ዙማ ከስልጣናቸው እንዲነሱ ሶስት የካቢኔ ሚኒስትሮቻቸው ጠየቁ። የሃገሪቱ ገዢው የአፍሪካ ብሄራዊ ምክር ቤት እያካሄደ ባለው አስቸኳይ ስብሰባ ላይ የታደሙት ሶስቱ ሚኒስትሮች ዙማ በገዛ ፈቃዳቸው ስልጣናቸውን እንዲለቁ በይፋ መጠየቃቸውን የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የሃገሪቱ የጤና ጥበቃ፣ ቱሪዝምና የስራ ሚኒስሮች ለፕሬዚደንቱ ጥያቄን ያቀረቡ ሶስቱ ሚኒስትሮች ሲሆኑ፣ ጃኮብ ዙማ በስልጣን ...
Read More »በጌዲዮ ዞን ለተፈጠረው ጉዳት ተጠያቂው ህወሃት/ኢህአዴግ ነው ሲሉ በውጭ የሚኖሩ የጌዲዮ ተወላጅ ማህበረሰብ አባላት ገለጹ
ኢሳት (ኅዳር 19 ፥ 2009) በጌዲዮ ዞን ለተፈጠረው ግጭትና ለደረሰው ከፍተኛ ጉዳት ተጠያቂው የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት ነው ሲል በውጭ የሚኖሩ የጌድዮ ተወላጆች ኮሚኒቲ አስታወቀ። በውጭ ሃገር የሚኖሩ የጌዲዮ ተወላጆች የሚያስተባረው ማህበር በሰዎች ላይ ለደረሰው ሞት እንዲሁም ለደረሰብ ንብረት ውድመት ሃዘኑን በመግለጽ በአካባቢው ከሚኖሩ የሌላ አካባቢ ተወላጆች ኢትዮጵያውያን ጋር የጌዲዮ ህዝብ ችግር የለበትም ሲልም አመልክቷል። ከወር በፊት በጌዲዮ ዞን የተፈጠረውን ችግርና የተከተለውን ...
Read More »