ኢሳት (ኅዳር 29 ፥ 2009) በኢትዮጵያ አጋጥሟል የተባለን የኢኮኖሚ መዳከም ተከትሎ የሃገሪቱ የዋጋ ግሽበት በተያዘው ወር ከአምስት ነጥብ ስድስት ወደሰባት በመቶ ከፍ ማለቱን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ሃሙስ አስታወቀ። የአለም ባንክ ሃገሪቱ አጋጥሟት ያለው የውጭ ንግድ ገቢ መቀነስና የውጭ ምንዛሪ ክምችት ማሽቆልቆል በኢትዮጵያ ዋጋ ግሽበት ሊያስከትል ይችላል ሲል ማሳሰቡ ይታወሳል። ባንኩ ሲሰጥ የቆየውን ትንበያ ተከትሎ የሃገሪቱ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበትን ይፋ ያደረገው ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በቢሊዮን ብር የሚቆጠር ኪሳራ የደረሰበት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ባንክ ከፍተኛ ውዝግብ ውስጥ መግባቱ ተነገረ
ኢሳት (ኅዳር 29 ፥ 2009) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ባንክ ለሃገር ውስጥና ለውጭ ባለሃብቶች መሬትን ለማቅረብ ሊያካሄድ ከነበረው ስራ ጋር በተገናኘ ያጋጠመው በቢሊዮን ብር የሚቆጠር ኪሳራ አዲስ ውዝግብ መቀስቀሱ ተግለጸ። የፌዴራልና የክልል ባለስልጣናት ለደረሰው ኪሳራ ሃላፊነቱን ማን መውሰድ እንዳለበት ለአንድ አመት ያህል ምክክርን ሲያካሄዱ ቢቆዩም ጉዳዩ ዕልባት አለማግኘቱ ታውቋል። በጋምቤላ ክልል ብቻ ከ100 የሚበልጡ የሃገር ውስጥና የውጭ ባለሃብቶች ለኢንቨስትመንት የሚሆን ሰፊ የእርሻ ...
Read More »በኢትዮጵያ የተከሰተው የዋጋ ግሽበት ከ5.6 ወደ 7 በመቶ ከፍ ማለቱን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ
ኢሳት (ኅዳር 29 ፥ 2009) በኢትዮጵያ አጋጥሟል የተባለን የኢኮኖሚ መዳከም ተከትሎ የሃገሪቱ የዋጋ ግሽበት በተያዘው ወር ከአምስት ነጥብ ስድስት ወደሰባት በመቶ ከፍ ማለቱን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ሃሙስ አስታወቀ። የአለም ባንክ ሃገሪቱ አጋጥሟት ያለው የውጭ ንግድ ገቢ መቀነስና የውጭ ምንዛሪ ክምችት ማሽቆልቆል በኢትዮጵያ ዋጋ ግሽበት ሊያስከትል ይችላል ሲል ማሳሰቡ ይታወሳል። ባንኩ ሲሰጥ የቆየውን ትንበያ ተከትሎ የሃገሪቱ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበትን ይፋ ያደረገው ...
Read More »በቢሊዮን ብር የሚቆጠር ኪሳራ የደረሰበት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ባንክ ከፍተኛ ውዝግብ ውስጥ መግባቱ ተነገረ
ኢሳት (ኅዳር 29 ፥ 2009) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ባንክ ለሃገር ውስጥና ለውጭ ባለሃብቶች መሬትን ለማቅረብ ሊያካሄድ ከነበረው ስራ ጋር በተገናኘ ያጋጠመው በቢሊዮን ብር የሚቆጠር ኪሳራ አዲስ ውዝግብ መቀስቀሱ ተግለጸ። የፌዴራልና የክልል ባለስልጣናት ለደረሰው ኪሳራ ሃላፊነቱን ማን መውሰድ እንዳለበት ለአንድ አመት ያህል ምክክርን ሲያካሄዱ ቢቆዩም ጉዳዩ ዕልባት አለማግኘቱ ታውቋል። በጋምቤላ ክልል ብቻ ከ100 የሚበልጡ የሃገር ውስጥና የውጭ ባለሃብቶች ለኢንቨስትመንት የሚሆን ሰፊ የእርሻ ...
Read More »ኢትዮጵያ በኢንተርኔት አገልግሎት ላይ የከፋ አፈናን ከሚፈጽሙ ሃገራት መካከል ግንባር ቀደም ሃገር ተብላ ተፈረጀች
ኢሳት (ኅዳር 29 ፥ 2009) ኢትዮጵያ በተያዘው 2016 የፈረንጆች አም በኢንተርኔት አገልግሎት ላይ የከፋ አፈናን ከሚፈጽሙ ሃገራት መካከል ግንባር ቀደም ሃገር ተብላ ተፈረጀች። በቴክኖሎጂው አጠቃቀምና ተደራሽነት እንዲሁም ቁጥጥር ዙሪያ አመታዊ ጥናቱን ይፋ ያደረገው ፍሪደም ሃውስ የተሰኘ ተቋም ቻይና፣ ሶሪያና ኢትዮጵያ የከፋ የተባለ አፈናን ከሚፈጽሙ ሃገራት መካከል ዋነኛ መሆናቸውን ይፋ አድርጓል። ካለፈው አመት ጀምሮ ኢንተርኔት አገልግሎት ላይ እገዳንና ቁጥጥርን ተግባራዊ አድርጋ ...
Read More »የአውሮፓ ሃገራት ዜጎቻቸው ወደ ሰሜን ጎንደር እንዳይጓዙ አዲስ ማሳሰቢያን አወጡ
ኢሳት (ኅዳር 29 ፥ 2009) በሰሜን ጎንደር የተለያዩ አካባቢዎች በመንግስትና በአርበኞች ግንቦት ሰባት ሃይሎች መካከል የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎ የአውሮፓ ሃገራት ዜጎቻቸው ወደ ስፍራው እንዳይጓዙ አዲስ ማሳሰቢያን አወጡ። ተደጋጋሚ የጉዞ ማሳሰቢያን ሲያወጡ የነበሩት የጀርመንና የቤልጅየም መንግስታት በኢትዮጵያ ያለው ህዝባዊ ተቃውሞ መሻሻልን ቢያሳይም በአማራ ክልል ስር በሚገኙ ሶስት ዞኖች የጸጥታ ስጋት መኖሩን ይፋ አድርገዋል። ለዜጎቻቸው አዲስ የጉዞ ማሳሰቢያን ያሰራጩት ሁለቱ የአውሮፓ ሃገራት ...
Read More »በጃኖራ የሚደረገው ውጊያ ዛሬም ቀጥሎ ውሎአል
ኅዳር ፳፰ (ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በዳባት ወረዳ በጃኖራ ቀበሌ ልዩ ስሙ መንደርጌ በተባለው ቦታ ካለፉት 2 ሳምንታት ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው ጦርነት ዛሬም እንደቀጠለ ሲሆን፣ በጦርነቱ ላይ የሚሳተፉ ተዋጊዮች እንደሚሉት በአገዛዙ ወታደሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ ነው። በአቶ መሳፍንት ተስፉ የሚመራው የነጻነት ሃይሎች ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከ50 በላይ ወታደሮችን መግደሉን የሚገልጹት ተዋጊዮቹ፣ በትናንቱ ጦርነትም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ...
Read More »የጃዊ ስኳር ፋብሪካ የሸንኮራ አገዳ ለሁለተኛ ጊዜ በእሳት ተቃጠለ
ኅዳር ፳፰ (ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) በመገንባት ላይ ያለው እና ከመጠናቀቂያ ጊዜው ለአንድ አመት ያክል የዘገየው የስኳር ፋብሪካ ንብረት የሆነ 60 ሄክታር የሸንኮራ አገዳ ሙሉ በሙሉ በእሳት ጋይቷል። ድርጊቱን ማን እንደፈጸመው በስም ያልጠቀሱዋቸው አካላት እያጣሩት ነው ሲሉ፣ የጠቀሱት የፋብሪካው ሃላፊ አቶ ባይነሳኝ፣ ጥናቱ ሳያልቅ መንስኤውን ይፋ ማድረግ አይቻልም ይላሉ። ሌሎች ወገኖች ደግሞ ድርጊቱ ...
Read More »በሳኡዲ አረቢያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤንባሲ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ስብሰባ ሊያደርግ ነው
ኅዳር ፳፰ (ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የብሔር ብሔረሰቦችን ቀን ለማክበር በሚል ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚቆይ ስብሰባ ከህዳር 29 እስከ ታህሳስ 1 ቀን 2009 ዓም ይካሄዳል። ጥሪውን ያስተላለፈው በአገሪቱ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤንባሲ ሲሆን፣ ዘመዶቻቸው በግፍ የተገደሉባቸውም ሆኑ አገዛዙን የሚቃወሙት ሁሉ በኢምባሲው ተገኝተው ተቃውሞአቸውን እንዲያሰሙ በአገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጥሪ አቅርበዋል።
Read More »አሜሪካውያን ወደኢትዮጵያ እንዳይጓዙ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማሳሰቢያ አወጣ
ኢሳት (ኅዳር 28 ፥ 2009) የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሃገሪቱ ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ ከመጓዝ እንዲቆጠቡ በድጋሚ ማሳሰቢያን አወጣ። ባለፈው አመት በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ ፖለቲካዊ ውጥረትና አለመረጋጋት ማስፈኑን ያስታወቀው የአሜሪካ መንግስት፣ አሜሪካዊያን ችግሩ ዕልባት ወደአላገኘባት ኢትዮጵያ ቢጓዙ የደህንነት ስጋት ሊያጋጥማቸው እንደሚችል አሳስቧል። ዜጎቹ ወደ ሃገሪቱ ከመጓዝ እንዲቆጠቡ ያሳሰበው የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ በኢንተርኔት አገልግሎት ላይ ተጥሎ ያለው ...
Read More »