.የኢሳት አማርኛ ዜና

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ ዲንቃ አረፉ

ኅዳር ፴ (ሠላሳ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደርግ ስርዓት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትርነት እና ጠቅላይ ሚንስርነት ሆነው ያገለገሉት አቶ ተስፋዬ ዲንቃ ያዴሳ በተወለዱ በ77 ዓመታቸው ህዳር 29 ቀን 2009 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። በ1932 ዓ.ም በቀድሞው ሸዋ ክ/ሃገር አንቦ ከተማ ውስጥ የተወለዱት አቶ ተስፋየ ፣ የ1ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አንቦ በሚገኘው ማዕረገ ሕይወት ቀዳማዊ ኃ/ስላሴ ትምህርት ቤት፣ የ2ኛ ደረጃ ...

Read More »

በደቡብ ምዕራብ ሶማሊያ የምትገኘው የጋፍጋዱድ ከተማ በታጣቂ ሃይሎች ቁጥጥር ስር መዋሏ ተገለጸ

ኢሳት (ኅዳር 30 ፥ 2009) በቅርቡ የኢትዮጵያ ወታደሮችና የሶማሊያው ታጣቂ ሃይል አልሸባብ መጠነ ሰፊ ውጊያ ያካሄዱበትና በደቡብ ምዕራብ ሶማሊያ የሚገኘው የጎፍጋዱድ ከተማ በታጣቂ ሃይሎች ቁጥጥር ስር መዋሏ ተገለጸ። በርካታ የኢትዮጵያ ወታደሮች ከሚገኙበት የባይደዋ ከተማ በ35 ኪሜ ርቀት ላይ በሚገኘው በዚህ ስፍራ ባለፈው ወር ውጊያ ተካሄዶ የጎፍ ጋዱድ ከተማ በመንግስት እጅ ገብቶ እንደንበር ሸበሌ ሬዲዮ ዘግቧል። ይሁና ከቀናት በፊት በአካባቢው ጥቃትን ...

Read More »

በኢትዮጵያ የምግብ እጥረት ያጋጠማቸውን ህጻናት ህይወት ለመታደግ አለም አቀፍ የዕርዳታ ማሰባሰብ ስራ ተጀመረ

ኢሳት (ኅዳር 30 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ተከስቶ ባለው የድርቅ አደጋ ምክንያት የከፋ የምግብ እጥረት የሚያጋጥማቸው ህጻናት ህይወት ለመታደግ አለም አቀፍ የዕርዳታ ተቋማት የአምስት አመት ዘመቻን ጀመሩ። በመንግስትና በ11 የሰብዓዊ ዕርዳታ ድርጅቶች የሚካሄደው ይኸው ዘመቻ 1.4 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የተመደበለት ሲሆን፣ ዘመቻው በከፋ የምግብ እጥረት ምክንያት የአካል መመናመን እየደረሰባቸው ያሉ ህጻናትና የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ የሚረዳ መሆኑ ታውቋል። በአማራ ክልል 46 በመቶ ...

Read More »

የእስራዔል መንግስት በሃገሪቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ደም እንዳይለግሱ ጥሎ የቆየውን እገዳ አነሳሁ አለ

ኢሳት (ኅዳር 30 ፥ 2009) የእስራዔል መንግስት በሃገሪቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ደም እንዳይለግሱ ጥሎ የቆየውን እገዳ አነሳ። የእስራዔል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከሃገሪቱ ውጭ የተወለዱ ወይም የHIV/AIDS ስርጭት ባለባቸው ሃገራት ለአንድ አመት ያህል ቆይታ ያደረጉ ቤት-እስራዔላዊያን ደም እንዳይለግሱ ከ10 አመት በፊት እገዳ መጣሉ ይታወሳል። ይሁንና የእስራዔል መንግስት ጥሎ የነበረው እገዳ በአግባቡ ለህዝብ ይፋ ባልተደረገበት ወቅት ማሪቭ (maiariv) የተሰኘ የሃገር ጋዜጣ ከኢትዮጵያውያን ይወሰድ ...

Read More »

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በእስር ቤት አለመኖሩ ተገለጸ

ኢሳት (ኅዳር 30 ፥ 2009) በዝዋይ እስር ቤት በእስር ላይ የነበረው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በእስር ቤቱ አለመኖሩንና ያለበት ቦታ እንደማይታወቅ የጋዜጠኛውን ጉዳይ የሚከታተሉ አካላት ለኢሳት ገለጹ። የጋዜጠኛው ቤተሰቦች በበኩላቸው የማህበራዊ ድረገጾች ባሰራጩት መረጃ ዝዋይ እስር ቤት ተመስገንን ለመጠየቅ ሁለት ቀን ቢሄዱም፣ በእስር ቤቱ ተመስገን የሚባል የመንግስት እስረኛ አናውቅም የሚል ምላሽ እንደሰጧቸው አረጋግጠዋል። ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በማፈላለግ ላይ ያሉ የቤተሰቡ አባላት ...

Read More »

የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ ዲንቃ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

ኢሳት (ኅዳር 30 ፥ 2009) የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ ዲንቃ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ። በደርግ ኢህድሪ መንግስት ውስጥ በከፍተኛ የሃላፊነት ቦታዎች ያገለገሉትና በመጨረሻ ለከፍተኛው የጠቅላይ ሚኒስትርነት ስፍራ የበቁት አቶ ተስፋዬ ዲንቃ ያረፉት በስደት በሚገኙበት በዩ ኤስ አሜሪካ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። የህይወት ታሪካቸው እንደሚያስረዳው የዛሬ 77 አመት በምዕራብ ኢትዮጵያ አምቦ አቅራቢያ የተወለዱት አቶ ተስፋዬ ዲንቃ፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የተከታተሉት ...

Read More »

46 ወታደሮች እስከነ ሙሉ ትጥቃቸው አርበኞች ግንቦት7ትን ተቀላቀሉ

ኅዳር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አርበኞች ግንቦት7 የኢትዮጵያ ክፍል ወኪሎች ለኢሳት እንደገለጹት ከረጅም ጊዜ ድርድር በሁዋላ 46 ወታደሮች የተለያዩ መሳሪያዎችን ይዘው ተቀላቅለዋል። ወታደሮቹ ከአርበኞች ግንቦት7 ጋር ተቀላቅለው በስልጣን ላይ ያለውን ሃይል ለመዋጋት ቃል መግባታቸውን የግንባሩ የአመራር አባል ገልጸዋል። ወታደሮቹ 9 መትረጊስ፣ 6 ስናይፐር፣ሁለት ዲሽቃና አንድ አርፒጂ መያዛቸውን አመራሩ ተናግረዋል። “ወታደሮቹ ግንባሩን የተቀላቀሉት ኤርትራ ነው ወይ ተብሎ ...

Read More »

የዶ/ር መረራ ጉዲናን መታሰር ተከትሎ በርካታ የኦሮሞ ብሄር ተወላጆች እየተያዙ ነው

ኅዳር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከአውሮፓ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ የታሰሩት የደ/ር መረራ ጉዲናን መታሰር ተከትሎ የእሳቸው ደጋፊ ይሆናሉ የተባሉ ወጣቶች እየተለቀሙ በመያዝ ላይ ናቸው። እስሩ እርሳቸው በተያዙ ማግስት የጀመረ ሲሆን፣ እስከዛሬ ድረስ በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ የኦሮምያ ወረዳዎች እንዲሁም በአምቦና አጎራባች ቀበሌዎች በርካታ ሰዎች ተይዘው ታስረዋል። በተመሳሳይ ዜና በደቡብ ወሎ ሃይቅ ከተማ በርካታ ወጣቶች በአዲሱ ወታደራዊ ...

Read More »

በአፍሪካ የቀጭኔ ዝርያዎች እየተመናመኑ በመምጣት ላይ ናቸው ተባለ

ኅዳር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በከፍተኛ ሁኔታ የሕዝብ ብዛት መጨመርን ተከትሎ በአፍሪካ አህጉር ውስጥ የሚገኙ የቀጭኔ ዝርያዎች እየተመናመኑ መጣታቸውን ዓለምአቀፍ የተፈጥሮ ጥበቃ ኅብረት International Union for the Conservation of Nature (IUCN) አስታወቀ። ድርጅቱ በጥናታዊ ሪፖርቱ እንዳመላከተው በአፍሪካ ውስጥ በእ.ኤ.አ.1985 ቁጥራቸው 155 ሽህ የነበሩ የቀጭኔ ዝርያዎች እ.ኤ.አ በ2015 ዝርያቸው ተመናምኖ ወደ 97 ሽህ ዝቅ ብሏል። ለቀጭኔ ዝርያዎች ...

Read More »

በኢትዮጵያ የሚገኘው የደቡብ ሱዳን ተማሪዎች ህብረት ሊያካሄድ የነበረውን የተማሪዎች ተወካዮች ምርጫ አራዘመ

ኢሳት (ኅዳር 29 ፥ 2009) በኢትዮጵያ የሚገኘው የደቡብ ሱዳን ተማሪዎች ህብረት በሃገሪቱ ተግባራዊ ተደርጎ በሚገኘው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንያት ሊያካሄድ የነበረውን የተማሪዎች ተወካዮች ምርጫ አራዘመ። ከ35ሺ የሚበልጡ የደቡብ ሱዳን ተማሪዎች በኢትዮጵያ የተያያዩ ዩኒቨስቲዎች የከፍተኛ ትምህርትን በመከታተል ላይ ሲሆኑ፣ የተማሪዎቹ ህብረት ከአንድ ሳምንት በኋላ አዳዲስ የተማሪዎች ተወካዮችን ለመምረጥ ፕሮግራም ይዞ እንደነበር ታውቋል። ይሁንና በኢትዮጵያ የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ህዝባዊ ስብሰባዎችን የሚከለከል ...

Read More »