.የኢሳት አማርኛ ዜና

በኢትዮጵያ የተከሰተውን ድርቅ ለመከላከል ተጨማሪ የእርዳታ ጥሪ ቀረበ

ታኅሣሥስ ፬ (አራት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኤሊኖ የአየር መዛባት ምክንያት በኢትዮጵያ የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ የዜጎችን ሕይወት ከርሃብ ለመታደግ 900 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወይም ከ 20 ቢሊዮን ብር ያላነሰ የገንዘብ እርዳታ እንደሚያስፈልግ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል። በምስራቅ ኢትዮጵያ በሚገኙ አካባቢዎች የኢሊኖ አየር ለውጥ በፈጠረው አሉታዊ ተጽእኖዎች ሳቢያ የጎርፍ መጥለቅለቅ፣ ተላላፊ በሽታዎች መዛመት እና ማኅበራዊ ቀውሶች ተፈጥረዋል። በድርቁ እና በተዛማጅ ...

Read More »

በታንዛኒያ የሰባት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች አስከሬን  ወንዝ ላይ ተጥሎ ተገኘ

ታኅሣሥስ ፬ (አራት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ማንነታቸውን የሚገልጽ ሕጋዊ መረጃ ያልያዙ ሰባት ኢትዮጵያዊያን በሩቩ ወንዝ ላይ አስከሬናቸው ተንሳፎ መገኘቱን የታንዛኒያ የአገር ውስጥ ሚንስትር አስታውቀዋል። ሚንስትሩ ሚውጉሉ ሚቼንባ ለአገሪቱ የቴሌቪዥን ጣቢያ እንደተናገሩት የመጀመሪያ የምርመራ ውጤት እንደሚያሳየው ሟች ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በባጋማዮ አውራጃ በሚገኝ የውሃ ዳርቻዎች ተገለው ወንዙ ውስጥ ተጥለዋል። የስድስቱ አስከሬን በውሃው ላይ ተንሳፎ ያዩት የአካባቢው ነዋሪዎች ባደረጉት ጥቆማ አስከሬናቸው ...

Read More »

አንድ ናይጀሪያዊ በቦሌ አየር ማረፊያ አደንዛዥ እፅ በሆዱ ውስጥ ደብቆ ለማለፍ ሲሞክር በቁጥጥር ስር ዋለ

ኢሳት (ታህሳስ 4 ፥ 2009) በአዲስ አበባ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ አንድ ናይጀሪያዊ ከአንድ ኪሎግራም በላይ የሚመዝን ኮኬይን የተሰኘ አደንዛዥ እፅ በሆዱ ውስጥ ደብቆ ለማለፍ ሲሞክር በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ ገለጸ። በአየር ማረፊያው ሲደርስ የሆድ ህመም አጋጥሞት ነበር የተባለውና ስሙ ያልተገለጸው ናይጀሪያዊ ወደ ሚኒሊክ ሆስፒታል ተወስዶ አደንዛዥ እጽ በቀዶ ጥገና ከሆዱ መውጣቱን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ማክሰኞ ዘግበዋል። 84 የታሸገ ኮኬይን በሆዱ ...

Read More »

ቴክሳስ ግዛት ሂውስተን ከተማ ነዋሪ ኢትዮጵውያን ኢሳትን ለመደገፍ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ባለፈው ቅዳሜ አካሄዱ

ኢሳት (ታህሳስ 4 ፥ 2009) ነዋሪነታቸው በዚሁ በአሜሪክ የቴክሳስ ግዛት ሂውስተን ከተማ የሆነ ኢትዮጵውያን ኢሳትን ለመደገፍ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በሳምንቱ መገባደጃ ቅዳሜ አካሄዱ። የኢሳትን ስድስተኛ አመት የምስረታ በአል አስመልክቶ በተካሄደው በዚሁ ስነስርዓት ኢሳትን ለመደገፍ ከተካሄደ የጨረታ ገቢ ብቻ ከ20ሺ ዶላር በላይ መገኘቱንና የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሙ የተሳካ እንደነበር አስተባባሪዎቹ ለኢሳት ገልጸዋል። የሂውስተን ከተማ የኢሳት ድጋፍ ሰጪ ኮሚቴ አስተባባሪ አቶ ሃይሌ ...

Read More »

የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ ዲንቃ የቀብር ስነስርዓት በአሜሪካ ግዛት ተፈጸመ

ኢሳት (ታህሳስ 4 ፥ 2009) የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ ዲንቃ የቀብር ስነስርዓት በአሜሪካ ግዛት ተፈጸመ። በ77 አመታቸው ማክሰኞ ህዳር 27 ቀን 2009 አም በዩኤስ አሜሪካ ቨርጂኒያ ግዛት ያረፉት የአቶ ተስፋዬ ዲንቃ የቀብር ስነስርዓት ቅዳሜ ታህሳስ 1 ቀን 2009 ዓም በፌየር ፋክስ ሜሞሪያል ፓርክ ተፈጽሟል። የቀድሞው የደርግ/ኢህድሪ መንግስት ውስጥ የንግድ፣ እንዲሁም የገንዘብና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመሆን ከሶስት በላይ ሚኒስትር መስሪያ ...

Read More »

በ2016 ለእስር የተዳረጉ ጋዜጠኞች ቁጥር መጨመሩን ሲፒጄ አስታወቀ

ኢሳት (ታህሳስ 4 ፥ 2009) ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለየዩ የአለማችን ሃገራት በመገባደድ ላይ ባለው የ2016 የፈረንጆች አም ለእስር የተዳረጉ ጋዜጠኞች ቁጥር መጨመሩን የዘንድሮውን አመታዊ ሪፖርት ማክሰኞች ይፋ ያደረገው ኪሚቴ ቱ ፕሮቴክት ጆዎርናሊስትስ (CPJ) አስታወቀ። በአፍሪካ ካሉ ሃገራት መካከል ጋዜጠኞችን በማሰር በሶስተኛ ድረጃ ላይ የተቀመጠችውን ኢትዮጵያ በተያዘው አመት 16 ጋዜጠኞች ለእስር ዳርጋ እንደምትገኝ በጋዜጠኞች መብት መከበር ዙሪያ የሚሰራውና መቀመጫውን በዚሁ በአሜሪካ ያደረገው ...

Read More »

ለአስቸኳይ ምግብ እርዳታ ለተጋለጡ ኢትዮጵያውያን ወደ አንድ ቢሊዮን ዶላር አካባቢ እንደሚያስፈልግ ተመድ ገለጸ

ኢሳት (ታህሳስ 4 ፥ 2009) በኢትዮጵያ በአዲስ መልክ የተከሰተውን የድርቅ አደጋ ለመከላከልና በሃገሪቱ ለአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ለተጋለጡ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች ድጋፍ ለማቅረብ ወደ አንድ ቢሊዮን ዶላር አካባቢ እንደሚያስፈልግ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ማክሰኞች ይፋ አደረገ። ባለፈው አመት በስድስት ክልሎች ተከስቶ የነበረው የድርቅ አደጋ ዕልባት ሳያገኝ ከሁለት ወር በፊት አዲስ የድርቅ አደጋ መከሰቱ የሰብዓዊ ዕርዳታ ፍላጎቱ እንዲጨምር ማድረጉ ታውቋል። በፈረንጆቹ 2017 አም ...

Read More »

የወባ በሽታ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገሮች አሳሳቢ ችግር ሆኖ መቀጠሉ ተገለጸ

ኢሳት (ታህሳስ 4 ፥ 2009) ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገሮች የወባ በሽታ አሁንም ድረስ አሳሳቢ የጤና ችግር ሆኖ መቀጠሉንና ባለፈው አመት ብቻ ከ400 ሺ በላይ ሰዎች በዚሁ በሽታ መሞታቸውን የአለም ጤና ድርጅት አስታወቀ። ከ400 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ለወባ በሽታ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የሚኖሩባት ኢትዮጵያ ከበሽታው ነጻ ለመባል ስታካሄድ የቆየችው መጠነ ሰፊ ዘመቻ ሳይሳካ መቅረቱን ለመረዳት ተችሏል። ኢትዮጵያ ከዚሁ ...

Read More »

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ላይ ስጋት ማሳደሩ ተገለጸ

ኢሳት (ታህሳስ 3 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ያለው አለመረጋጋትና ተግባራዊ ተደርጎ የሚገኘው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ላይ ስጋት ማሳደሩ ተገለጸ። በተለይ አየር መንገዱ በአንጎላ እና ናይጀሪያ ሃገራት ያለው ሰፊ የጉዞ እንዲሁም የትኬት ሽያጭ ገበያ ባለፉት በርካታ ወራቶች መቀዛዝቅዝ ማሳየቱን ብሉምበርግ የተለያዩ መርጃዎችን ዋቢ በማድረግ ሰኞ ለንባብ አብቅቷል። በእነዚሁ ሁለት ሃገራት ብቻ ከትኬት ሽያጭ ከ200 ሚሊዮን ዶላር ...

Read More »

አሜሪካ አንድ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብቶች ልዑካን ቡድን ወደ አዲስ አበባ ለመላክ መወሰኗን ይፋ አደረገች

ኢሳት (ታህሳስ 3 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ባለው የሰብዓዊ መብት ሁኔታ ስጋቷን ስትገልጽ የቆየችው አሜሪካ አንድ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብቶች ልዑካን ቡድን ወደ አዲስ አበባ ለመላክ መወሰኗን ሰኞ ይፋ አደረገች። የዴሞክራሲ እና የሰብዓዊ መብቶች ረዳት ሚኒስትር ቶም ማሊኖውስኪ የሚመራ የልዑካን ቡድን ከረቡዕ ጀመሮ በአዲስ አበባ የአራት ቀን ጉብኝት እንደሚያደርግ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አመልክቷል። በኢትዮጵያ የአራት ቀን ቆይታ የሚኖራቸው ቶም ...

Read More »