ታኅሣሥ ፲፪ (አሥራ ሁለት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዘ- ኢጂፕሺያን ኢንዲፐንደንት እንደዘገበው ውይይቱ ያተኮረው በሳኡዲና በግብጽ መካከል ቅሬታ በተፈጠረበት በአሁኑ ሰዓት የሳኡዲ ባለሥልጣናት በኢትዮጵያ ያደረጉት ጉብኝት- በአባይ ላይ እየተሰራ ካለው ግድብ ጋር ስለመያያዙ ነው። የሳኡዲ ንጉስ አማካሪ ሰሞኑን በአዲስ አበባ ባደረጉት ጉብኝት ከኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር መገናኘታቸው ታውቋል። ይህ የሳኡዲ ባለስልጣናት ጉብኝት ከአባይ ግድብ ጋር ግንኙነት ይኖረው ይሆን ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በጋምቤላ ክልል ሰፋፊ የእርሻ መሬት የወሰዱ 29 ድርጅቶች የገቡበት አልታወቀም ተባለ
ኢሳት (ታህሳስ 11 ፥ 2009) በጋምቤላ ክልል በኢንቨስትመንት ስም ተመዝግበው ሰፋፊ የእርሻ መሬትን የወሰዱ 29 ድርጅቶች የገቡበት አለመታወቁን ከክልሉ መሬት አሰጣጥ ጋር ተፈጥሯል የተባለን ችግር እንዲያጠና የተቋቋመ ቡድን ይፋ አደረገ። ከአንድ አመት በላይ ጥናቱን ሲያካሄድ የቆየው ይኸው ቡድን በጋምቤላ ክልል ለኢንቨስትመንት ከተሰማሩ 623 ባለሃብቶች መካከል ለ381 ባለሃብቶች የተሰጠው ከ45ሺ ሄክታር በላይ መሬት ተደራርቦ እንደተሰጣቸው ተመልክቷል። የተደራረበ መሬት የተረከቡት እነዚሁ 381 ...
Read More »የብሪታኒያ መንግስት ለትምህርታዊ ፕሮግራሞች ሊሰጥ የነበረው የ150 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ እንደገና እንዲታጤን መወሰኑ ተገለጸ
ኢሳት (ታህሳስ 11 ፥ 2009) የብሪታኒያ መንግስት በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ስር ባሉ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ለሚተላለፉ ትምህርታዊ ፕሮግራሞች ሊሰጥ የነበረው የ150 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ እንደገና እንዲታይና እንዲጠና ወሰነ። የሃገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ለኢትዮጵያ ሊሰጥ የተወሰነው የ5.2 ሚሊዮን ፓውንድ ስተርሊንግ ድጋፍ ከታለመለት አላማ ውጭ ሊውል ይችላል ሲሉ ሰኞ ተቃውሞ ማቅረባቸውን ዴይሊ ሜይል ጋዜጣን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል። በተለያዩ ባለስልጣናት የቀረበውን ይህንኑ ተቃውሞ ...
Read More »በአዲስ አበባ ከተማ አሜሪካ ግቢ መኖሪያ ቤታቸው ለልማት የፈረሰባቸው ነዋሪዎች መንግስት ተለዋጭ ቦታ ለመስጠት የነበረውን ቃል አላከበረም ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ
ኢሳት (ታህሳስ 11 ፥ 2009) በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ አሜሪካ ግቢ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ መኖሪያ ቤታቸው ለልማት ተብሎ የፈረሰባቸው ነዋሪዎች መንግስት ተለዋጭ ቦታ ለመስጠት የነበረውን ቃል አላከበረም ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ። የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ሃላፊዎች በበኩላቸው ህጋዊ የመኖሪያ ማስረጃ እያላቸው ያልተስተናገዱ ነዋሪዎች የሉም ሲሉ ምላሽ መስጠታቸው ታውቋል። ይሁንና ቅሬታን እያቀረቡ ያሉ ነዋሪዎች ህጋዊ ይዞታ እያላቸው ምትክ ቦታ ሳይሰጣቸው ለረጅም ጊዜ ...
Read More »መስፍን ኢንጂነሪንግ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ በአዲስ አበባ አስመረቀ
ኢሳት (ታህሳስ 11 ፥ 2009) የህወሃት ንብረት የሆነው መስፍን ኢንጂነሪንግ የፔጆ መኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ በአዲስ አበባ ማስመረቁ ተነገረ። በያዝነው የፈረንጆች አመት ተመሳሳይ የፔጆ መገጣጠሚያ በትግራይ ክልል ያስመረቀው መስፍን ኢንጂነሪግን አሁን ደግሞ በአዲስ አበባ ሌላ የማስፋፊያ ፋብሪካ አስመርቋል። በአዲስ አበባ የተገነባው ይሄው የመስፍን ኢንጂነሪንግ መገጣጠሚያ ፋብሪካ በአመት እስከ 1 ሺ 200 መኪኖች እንደሚያመርት የህወሃት አገዛዝ ደጋፊ የሆነ ድረገጽ ዘግቧል። መኪና የመገጣጠም ...
Read More »በጃዊ የነጻነት ታጋዮች ከአርሶአደሮች ጋር በማበር በመንግስት ወታደሮች ላይ ያደረሱትን ጥቃት ተከትሎ አካባቢው አሁንም በውጥረት ላይ ነው
ታኅሣሥ ፲፩ (አሥራ አንድ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚገለጹት ታህሳስ 5 እና 6 በነበረው ሁለተኛ ዙር ተቃውሞ አገዛዙ ሁለት ታንኮችን አስገብቶ የነበረ ቢሆንም፣ ከህዝብ የተሰነዘረበትን ጥቃት መቀነስ ሳይችል ቀርቷል። አርሶአደሮችና ታጋዮች ተቃውሞውን ተከትሎ እነሱን ለማጥቃት የሄደውን አንድ ታንክ እንዳቃጠሉ እየተናገሩ ቢሆንም፣ ኢሳት ከራሱ ምንጮች እስካሁን ለማረጋገጥ አልቻለም። የአካባቢው ዘጋቢያችን እና ከዋና ከተማው ራቅ ብሎ በሚገኘው የጃዊ የሸንኮራ ...
Read More »በኦሮምያ በተለያዩ ቀበሌዎች በተደረጉት ስብሰባዎች የቀበሌ አመራሮች ተቃውሞአቸውን ገለጹ
ታኅሣሥ ፲፩ (አሥራ አንድ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው እሁድ በተጠናቀቀው “ ጥልቅ ተሃድሶ” በሚል አጀንዳ ለ5 ተከታታይ ቀናት በተደረገው ስብሰባ ላይ የቀበሌ አመራሮች ግምገማው ትክክል ያልሆነና የህዝቡን ብሶት ግምት ውስጥ ያላስገባ ነው ብለዋል። እናንተ ህዝባችንን ትገላላችሁ፣ እኛ ደግሞ አንድ ሰው እስከሚቀር ፣ ህዝባችን ጥያቄውን መጠየቁን አያቆምም። ጥልቅ ተሃድሶ የሚባል ከሆነ ዋናውን ችግር ትታችሁ ትንንሽ ጉዳይ ላይ ማተኮራችሁ ትክክል ...
Read More »የኦጋዴን ነጻነት ግንባር ከአገዛዙ ወታደሮች ጋር “እየተዋጋሁ ነው” አለ
ታኅሣሥ ፲፩ (አሥራ አንድ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ግንባሩ፣ ባለፈው ሃሙስ በኦጋዴን ቃብሪዳህር ወረዳ ዲሞዲሊ መንደር ውስጥ የህወሃት ኢህአዴግ ታጣቂዎች በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ እንደተለመደው የጅምላ ግድያ፣ አስገድዶ መድፈርና እስራት መፈጸማቸውን ተከትሎ ግንባሩ ከተጠቂዎቹ ጎን በመቆም አጸፋዊ ምላሽ መውሰዱን አስታውቋል። በሁለቱ ቡድኖች መሃከል በተደረገው የተኩስ ልውውጥ 6 የህወሃት ኢህአዴግ ወታደሮች ተገለው፣ 8 መቁሰላቸውን የግንባሩ ወታደራዊ ክንፍ አስታውቋል። በኦጋዴን ግዛት ውስጥ ...
Read More »ባንዲራ በመሥራታቸው በላሊበላ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ግርማ ቅባቴ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ
ታኅሣሥ ፲፩ (አሥራ አንድ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለ11 አመታት በፖሊስነት ያገለገሉት አቶ ግርማ ፣ ከ1987 ዓም ወዲህ ስራቸውን በመልቀቅ በዲዛይነር ስራ ላይ ተሰማርተው ቆይተዋል። አቶ ግርማ የኢትዮጵያን ባንዲራ በተለያዩ ዲዛይኖች እየሰሩ መሸጣቸውና ወደ ውጪ መላካቸው ወንጀል ሆኖ ተቆጥሮባቸዋል። ባለፉት ወራት የተከሰተውን ህዝባዊ አመጽ ተከትሎ የታሰሩት አቶ ግርማ፤ ፍርድ ቤት እስከቀረቡበት እስከዛሬ ማክሰኞ ድረስ “እኔ ነኝ ያሳሰርኳቸው” የሚል አካል ...
Read More »የብሪታንያ መንግስት ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚሰራጩ የሙዚቃና ትምህርታዊ ፕሮግራሞች ያጸደቀው 5 ሚሊዮን ፖውንድ ተቃውሞ ገጠመው
ኢሳት (ታህሳስ 10 ፥ 2009) የብሪታንያ መንግስት በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተቋማት ለሚካሄዱ/ለሚሰራጩ የሙዚቃና ትምህርታዊ ፕሮግራሞች ድጋፍ ያጸደቀው 5 ሚሊዮን ፖውንድ በሃገሪቱ ባለስልጣናት ዘንድ ተቃውሞን ቀሰቀሰ። የሃገሪቱ መንግስት በመንግስት መገናኛ ብዙሃን ተቋማቱ “የኛ” በሚሰኙ አባላት ዘንድ የሚተላለፉ ፕሮግራሞች የማህበራዊ ጉዳዮች የሚዳሰሱ ናቸው በማለት ከጥቂት አመታት በፊት ድጋፍ መስጠት መጀመሩን ዴይሊ ሜይል የተሰኘ የብሪታኒያ ጋዜጣ ዘግቧል። ይህንኑ የሙዚቃና ድራማዊ ፕሮግራሞ ለቀጣዩ ሁለት ...
Read More »