.የኢሳት አማርኛ ዜና

በቤኒሻንጉል ቡለን ወረዳ በአማራ ተወላጆች ላይ ግፍና በደል እየተፈጸመ መሆኑ ተገለጸ

ኢሳት (ታህሳስ 18 ፥ 2009) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቡለን ወረዳ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ግፍና በደል እየተፈጸመባቸው መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ። በአካባቢው የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች እስራትና ድብደባ የሚፈጸምባቸው የጦር መሳሪያ ታዘዋውራላችሁ በሚል መሆኑን ዕማኞች ለኢሳት ተናግረዋል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና በአማራ ክልል አጎራባች ወረዳዎች በተለይም የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ ፕሮጄክቶች ባሉበት አካባቢ የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ ለስርዓቱ ስጋት መሆኑን ይነገራል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ...

Read More »

ከ100 በላይ ኢትዮጵያውያን በሶማሌ ድንበር በኩል ከሃገር ሊወጡ ሲሉ በቁጥጥር ስር ዋሉ

ኢሳት (ታህሳስ 18 ፥ 2009) በሶማሌ ክልል ድንበር አቋርጠው ከሃገር ሊወጡ የነበሩ ከ100 በላይ ኢትዮጵያውያን በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ ማክሰኞ ገለጸ። የአለም አቀፉ ስደተኞች ድርጅት (IOM) በበኩሉ የመንን ጨምሮ ከተለያዩ የምዕራብ አፍሪካ ሃገራት መውጫን አጥተው የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሃገራቸው ለመመለስ ጥረት እያደረገ መሆኑን አስታውቋል። ድርጅቱ ስደተኛ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሃገር ለመመለስ ጥረት በማድረግ ላይ እያለ ማክሰኞ ማለዳ በጭነት ተሽከርካሪዎች ተጭነው በሶማሌ ...

Read More »

አሜሪካ የሶሪያ አማጺያንን በዘመናዊ መሳሪያ ለማስታጠቅ ያያዘችው እቅድ ተቃውሞ ገጠመው

ኢሳት (ታህሳስ 18 ፥ 2009) ሩሲያ አሜሪካ የሶሪያ አማጺያን ቡድንን በዘመናዊ የጦር መሳሪያ ለማስታጠቅ የያዘችውን እቅድ ተቃወመች። የፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ አስተዳደር በቅርቡ ለሶሪያ አማጽያን ለማቅረብ የወሰነው የጦር መሳሪያ ድጋፍ በሶሪያ የሚገኙ ወታደሩን ደህንነት ስጋት ውስጥ ያካተተ ነው ስትል ሩሲያ ድርጊቱን ኮንናለች። አሜሪካ የባሽር አላሳድ መንግስት ለመጣል ለሚታገሉ ሃይሎች ጸረ አውሮፕላን ሚሳይሎችን ጨምሮ ሌሎች ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች ድጋፍ ለማድረግ በቅርቡ መወሰኗ ...

Read More »

ግብፅ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ሃይሎች ስለመደገፏ የቀረበባትን  ቅሬታ በተመለከተ ይፋዊ ምላሽ ልትሰጥ ነው

ኢሳት (ታህሳስ 17 ፥ 2009) የግብፅ መንግስት ኢትዮጵያ ላቀረበችው የተቃዋሚ ሃይሎችን ትደግፋላችሁ ቅሬታ ይፋዊ ምላሽ ለመስጠት በመዘጋጀት ላይ መሆኑ ሰኞ አስታወቀ። ለአንድ አመት ያህል በኦሮሚያ ክልል ሲካሄድ የቆየውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ግብፅ ከዚሁ አመጽ ጋር ግንኙነት አላት ሲሉ ተቃውሞን ማቅረባቸው ይታወሳል። ይህንና የግብፅ ባለስልጣናት ከኢትዮጵያ እኩል የቀረበውን ቅሬታ በማስተባበል ሃገሪቱ በሌላ ሃገር የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ እንደማትገባ ምላሽ መስጠታቸውን ...

Read More »

በአዲስ አበባ ከመሬታቸው የተፈናቀሉ አርሶ አደሮች የከተማው አስተዳደር ካሳ እንዲከፍላቸው ጠየቁ

ኢሳት (ታህሳስ 17 ፥ 2009) በአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ ለልማት ተብሎ ከእርሻ መሬታቸው የተፈናቀሉ አርሶ አደሮች የተወሰደባቸው መሬት ለአመታት ታጥሮ ያለምንም አገልግሎት በመዋሉ የከተማው አስተዳደር ኪሳራውን አስልቶ ካሳ እንዲከፍላቸው ጠየቁ። እነዚሁ ከ1988 ጀምሮ መሬታቸው ለልማት ተብሎ የተወሰደባቸው አርሶ አደሮች በመፈናቀላቸው ምክንያት ሃብትና ንብረት አልባ ሆነው ሲቀመጡ የተባለው የህዝብ ጥቅም ሳይከበር የታለመው ልማትም ሳይመጣ መሬቱ ታጥሮ ያለስራ መቀመጡ እንዳስቆጫቸው ገልጸዋል። በተወካዮቻቸው ...

Read More »

በምስራቅ ሸዋ የመኪና ግጭት አደጋ በመከሰቱ የሰው ህይወት ጠፋ

ኢሳት (ታህሳስ 17 ፥ 2009) በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ሸዋ ዞን ቦራ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ 14 ሰዎች መሞታቸውን ፖሊስ ሰኞ አስታወቀ። 14 ሰዎችን አሳፍሮ ከባቱ ከተማ ወደ አዲስ አበባ ይጓዝ የነበረ የህዝብ ማመለሻ ተሽከርካሪ ቦራ ወረዳ ሶሪ ዴሊሳ ቀበሌ ሲደርስ ከቢሾፍቱ ወደ ባቱ ከተማ ከሚጓዝ ሲኖ ትራክ የጭነት ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ አደጋው መድረሱን የፖሊስ መረጃን ዋቢ በማድረግ በሃገር ውስጥ ያሉ ...

Read More »

የሩሲያ ወታደራዊ አውሮፕላን በጥቁር ባህር ላይ ተከሰከሰ

ኢሳት (ታህሳስ 17 ፥ 2009) ንብረትነቱ የሩሲያ የሆነ ወታደራዊ አውሮፕላን ዕሁድ በጥቁር ባህር ላይ ተከሰከሰ። የገቡበት ያልታወቀ ከ90 በላይ ሰዎችን ለማግኘት ዘመቻ በመካሄድ ላይ መሆኑን ሩሲያ አስታወቀች። ይኸው ወደ ሶሪያ በማቅናት ላይ የነበረው አውሮፕላን ወታደሮችን፣ ሙዚቀኞችን፣ እንዲሁም ጋዜጠኞችና የበረራ ባለሙያዎችን ይዞ በማቅናት ላይ እንዳለ ሶቺ ተብላ ከምትጠራ የባህር ዳር አቅራቢያ ከተማ መከስከሱን የሩሲያ ባለስልጣናት ለመገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል። የሃገሪቱ ወታደራዊ ባለስልጣናት ...

Read More »

በባህርዳር እና በዙሪያዋ ወረዳዎች ተይዘው ከታሰሩት መካከል በሺዎች የሚቆጠሩት ፍድር ቤት ሳይቀርቡ ለወራት መታሰራቸው ታወቀ

ታኅሣሥ ፲፯ (አሥራ ሠባት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከነሃሴ ፣ 2008 ዓም ጀምሮ በባህርዳር ዙሪያ በሚገኙ ወረዳዎች ማለትም በባህርዳር ዙሪያ፣ ጎንጂ ቆለላ፣ ይልማና ዴንሳ፣ ሜጫ፣ አቸፈር፣ ባህርዳርና ደራ ወረዳዎች ተይዘው ከታሰሩ ከ4 ሺ በላይ ወጣቶች መካከል 1 ሺ 500 የሚሆኑት እስካሁን ድረስ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ በባህርዳር ወህኒ ቤት ታስረው ለስቃይ እየተዳረጉ ነው። እስረኞቹ በከፍተኛ የውሃ እና ህክምና ችግር እየተሰቃዩ ...

Read More »

በአፋር ክልል የተተከለው ራዳር መነሳቱ ታወቀ

ታኅሣሥ ፲፯ (አሥራ ሠባት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቅርቡ በተለያዩ አገሪቱ ክፍሎች ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ወጥቶባቸው ከተተከሉት ራዳሮች መካከል በአፋር ክልል ዱብቲ አካባቢ የተተከለው ራዳር ሳምንት ባልሞላው ጊዜ ውስጥ እንዲነቀል ተደርጓል። እርምጃው ለምን እንደተወሰደ ባይታወቅም፣ ዘገባው በኢሳት ከተላለፈ በሁዋላ እንዲነሳ መደረጉ ምናልባትም ከመረጃው ከመውጣት ጋር የተያያዘ ሳይሆን እንደማይቀር ይገመታል። ከፍተኛ ገንዘብ ወጪ በማድረግ ገዢው ፓርቲ የተለያዩ የርቀት መቆጣጠሪያ ...

Read More »

የፉጋ ማህበረሰብ እየተባሉ የሚጠሩት ለመጥፋት ተቃርበዋል ተባለ

ታኅሣሥ ፲፯ (አሥራ ሠባት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ክልል በአላባ ልዩ ዞን የሚገኝው የፉጋ ማህበረሰብ ከፍተኛ ለሆነ መገለል እና መድሎ ተጋላጭ በመሆኑ እና ምንም አይነት ፤ የትምህርት ፣ የጤና ተደራሽነት በማጣቱ ወደ ማህበረሰባዊ በቀል እና ጥላቻ የወለደው አመፅ ሊያመሩ እንደሚችሉ የፌደሬሽን ምክርቤት አስታወቀ፡፡ ምክር ቤቱ ባስጠናው ጥናት  ኢህአዴግ እስካሁን ድረስ አገዛዙን ከተቆጣጠረበት ጊዜ አንስቶ ማህበረሰቡ “የተካደ የተናቀ እና ...

Read More »