.የኢሳት አማርኛ ዜና

በደቡብ ክልል ወደ 20 ሺ የደህዴን አባላት መባረራቸው ተገለጸ

የካቲት ፲፭ ( አሥራ አምስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢህአዴግ የክልሎችን የተሃድሶ ሪፖርት በሰማበት ስብሰባ ላይ የደቡብ ክልል መስተዳድር ፕሬዚዳንት አቶ ደሴ ዳልኬ ከ18 ሺ 250 የበታች አመራሮችን እንዲሁም 1920 ከፍተኛ፣ መካከለኛና ጀማሪ አመራሮች መባረራቸውን ተናግረዋል። በእነዚህ ሰዎች ቦታ ላይ 2 ሺ 359 አዳዲስ አመራሮች መተካታቸውን ገልጸዋል። አቶ ደሴ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ አመራሮችን አባረናል ቢሉም ፣ ያባረሯቸውና የተኳቸው ...

Read More »

የብአዴን መሪዎች የጎንደርን ህዝብ በማባበል ስራ ላይ ቢጠመዱም አልተሳካለቸውም

የካቲት ፲፭ ( አሥራ አምስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ህዝባዊ አመፁ ከተቀሰቀሰ እና አስቸኳይ አዋጅ ከታወጀ በኃላ ባሉት አራት ወራት ጊዜ ውስጥ ፣ ጠቅላይ ሚንስትሩን ጨምሮ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ ፣ የመከላከያ ሹማምንት ፣ የክልል ፕሬዝዳንቶች ፣ ምክትል ፕሬዝዳንቶችና ሌሎችም የኢህአዴግ አመራሮች በጎንደር እየተገኙ እራሳቸውን እየሰደቡ፣ ችግሮችን ለመፍታት ሲምሉ እና ሲገዘቱ ቆይተዋል። ለምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን አራተኛ መድረክ፣ ...

Read More »

ሰላማዊ ሰልፍ በማድረጋቸው የታሰሩ 63 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ለኢህአዴግ መንግስት ተላልፈው ተሰጡ

የካቲት ፲፭ ( አሥራ አምስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባሳለፍነው ሳምንት ሱዳን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ በመገኘት በሰላማዊ መንገድ ሕጋዊ መብቶቻቸውን የጠየቁ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ላይ በኤንባሲው ፈቃጅነት በሱዳን የጻጥታ ኃይሎች ድብደባ፣ የጅምላ እስራት፣ አካላዊ ጥቃቶች መፈጸሙ እና አንድ ስደተኛም በስለት ተወግተው መገደላቸው ይታወቃል:: በሱዳን የፀጥታ ሃይሎች ተይዘው በተጨናነቀ በእስር ቤት ታጉረው የተለያዩ ሰቆቃ ሲፈፀምባቸው ከነበሩት ስደተኞች ...

Read More »

ገዥው ፓርቲ በፈጠረው ጫና ላለፉት አስር ቀናት ተቋርጦ የነበረው የኢሳት ቴሌቪዥን ስርጪት ዳግም ተጀመረ።

የካቲት ፲፭ ( አሥራ አምስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ገዥው ፓርቲ የኢትዮጵያ ሕዝብ አማራጭ ሀሳቦችን እንዳይሰማ ካለው ሥጋት በመነሳት እንደተለመደው ሁሉ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ በማፍሠስ የኢሳት ቴሌቪዥን ከአየር ላይ እንዲወርድ አድርጎ ቢሰነብትም ኢሳት ባደረገው ከፍተኛ ጥረት ዳግም ወደ አየር ተመልሷል። ቀደም ሲል ኢሳትን ሲከታትተሉ የነበሩ አድማጮች የዲሽ ሰሀን አቅጣጫ መቀየር ሳያስፈልጋቸው በፍሪኩዌንሲ Tel Star 12 Frequency 12738 Horizontal ...

Read More »

የኢትዮጵያ የመረጃ ደህንነትና መረብ ኤጀንሲ የኢንተርኔት ቴክኖሎጂ ቁሳቁሶችን አስኮ ከተባለ ኩባንያ ለመግዛት የ1.3 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ፈጸመ

ኢሳት (የካቲት 15 ፥ 2009) መቀመጫውን በአውሮፓ ፖላንድ ያደረገ አንድ አለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ለኢትዮጵያ የመረጃ ደህንነትና መረብ ኤጀንሲ የተለያዩ የኢንተርኔት የቴክኖሎጂ ቁሳቁሶችን ለማቅረብ የ1.3 ሚሊዮን ዶላር (ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ) ስምምነት ፈጸመ። አስኮ (ASSECO) ግሩፕ የሚል መጠሪያ ያለው ይኸው ኩባንያ የረቀቁ የቴክኖሎጂ ሶፍትዌሮችን በማምረት ለተለያዩ ድርጅቶችና አገራት የሚያቀርብ እንደሆነ ኩባንያው በድረገጹ ላይ ካሰፈረው መረጃ ለመረዳት ተችሏል። የኢትዮጵያ መረጃና ደህንነት ...

Read More »

በኢትዮጵያና ሶማሊያ በድርቅ ምክንያት ህይወታቸው አደጋ ላይ የተጋለጠ ሰዎችን ህይወት ለመታደግ አለም አቀፍ ጥሪ ቀረበ

ኢሳት (የካቲት 15 ፥ 2009) የተባበሩት መንግስታት የእርዳታ ድርጅቶች በኢትዮጵያና ጎረቤት ሶማሊያ በድርቅ ምክንያት ህይወታቸው አደጋ ላይ የተጋለጠ ሰዎችን ህይወት ለመታደግ የአለም አቀፍ ማህበረሰብ አፋጣኝ ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪን አቀረቡ። መቀመጫቸውን በስዊዘርላንድ ጄኔቫ ከተማ ያደረጉ የድርጅቱ የሰብዓዊ ዕርዳታ አስተባባሪዎች በሁለቱ ሃገራት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የሞት እና የጤና አደጋ ውስጥ መሆናቸውን እንደገለጹ ሮይተርስ ዘግቧል። ባለፈው ሳምንት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል ...

Read More »

ወደ ታንዛኒያ የሚገቡ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ቁጥር ስጋት እየሆነ መምጣቱን የታንዛኒያ የኢሚግሬሽን ባለስልጣናት አስታወቁ

ኢሳት (የካቲት 15 ፥ 2009) የታንዛኒያ የኢሚግሬሽን ባለስልጣናት ወደ ሃገሪቱ በህገወጥ መንገድ የሚገቡ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ስጋት እየሆነ መምጣቱን ረቡዕ አስታወቁ። በዚሁ ድርጊት ተሳትፈዋል የተባሉ 13 ኢትዮጵያውያን ሰኞ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የገለጹ ሲሆን፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወደ ታንዛኒያ የሚገቡ ኢትዮጵያውያን ቁጥር እየጨመረ በመሄድ ላይ መሆኑን አክለው ገልጸዋል። ከአንድ ወር በፊት በተመሳሳይ ሁኔታ ወደ ሃገሪቱ ገብተዋል የተባሉ 83 ስደተኛ ኢትዮጵያውያን በቁጥጥር ስር ...

Read More »

ብሪታኒያ ለአፍሪካ አገራት የምትሰጠው የገንዘብ ድጋፍ ከአውሮፓ ህብረት ለመውጣት ለሚደረግ እቅድ ማስፈጸሚያነት እንዲውል ጥያቄ ቀረበ

ኢሳት (የካቲት 14 ፥ 2009) የብሪታኒያ መንግስት ኢትዮጵያን ጨምሮ ለተወሰኑ የአፍሪካ ሃገራት የሚሰጠውን አመታዊ የገንዘብ ድጋፍ ከአውሮፓ ህብረት ለመውጣት እያካሄደ ላለው እቅድ ማስፈጸሚያ እንዲያውለው የሃገሪቱ ሚኒስትሮች ጥያቄን አቅረቡ። ለአፍሪካ የሚሰጠው ድጋፍ እንዲታጠፍ ጥያቄን እያቀረቡ ያሉ የብሪታኒያ ሚኒስትሮች ሃገራቸው ድጋፍን በምስራቅ አውሮፓ ከሚገኙት ፖላንድ፣ ሃንጋሪ እና የባልቲክ ሃገራት (ኢስቶኒያ፣ ላቲቪያና፣ ሊቶኒያ) ድጋፍ እንዲውል ጥያቄን አቅርበዋል። የብሪታኒያ መንግስት በየአመቱ 12 ቢሊዮን ፓውንድ ...

Read More »

በሞጆ የሚገኙ የጨርቃጨርቅ ፋብሪካዎች በኤሌክትሪክ መቋረጥ ሳቢያ ከቅዳሜ ጀምሮ ምርት ማቆማቸው ተገለጸ

ኢሳት (የካቲት 14 ፥ 2009) በሞጆ የሚገኙ የጨርቃጨርቅና ሌሎች ፋብሪካዎች በኤሌክትሪክ መቋረጥ ሳቢያ ከቅዳሜ ጀምሮ ምርት ማቆማቸው ታወቀ። የሞጆ ቆዳ ማምረቻ፣ ጆርጅ ጫማ የተሰኘና ምርቶቹን ለውጭ ሃገር ገበያ የሚያቀርብ ፋብሪካ፣ የኢትዮ-ጃፓን የጨርቃ-ጨርቅ ፋብሪካዎች፣ አዲስ ሞጆ የምግብ ዘይት ኮምፕሌክስና የሞጆ ደረቅ ወደብ ምርት ካቆሙ ፋብሪካዎች መካከል ዋና ዋናዎቹ መሆናቸው ተመልክቷል። ፋብሪካዎቹ ምርት በማቆማቸው ምክንያት የምርት መስተጓጎልና በትዕዛዝ መድረስ የነበረባቸው ምርቶች ሊደርሱ ...

Read More »

የፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት የቀብር ስነ-ስርዓት በአዲስ አበባ መንበረ-ጸባዖት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ተፈጸመ

ኢሳት (የካቲት 14 ፥ 2009) ከቀናት በፊት ከዚህ አለም በሞት የተለዩት የፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት የቀብር ስነ-ስርዓት ማክሰኞ በአዲስ አበባ መንበረ-ጸባዖት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ተፈጸመ። በኢትዮጵያ ታሪክ ለረጅም አመታት ጥናትና ምርምር በማካሄድ የሚታወቁት ፕሮፌሰር ፓንክረስት ከአራት ቀናት በፊት በ90 አመታቸው በሞት መለየታቸው ይታወሳል። ፕሬዚደንት ሙላቱ ተሾመን ጨምሮ የፕሮፌሰር ፓንክረስት ቤተሰቦች ወዳጆችና የስራ ባልደርቦች እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በቀብር ስነስርዓቱ መታደማቸውን ከሃገር ...

Read More »