የካቲት ፳፪ ( ሃያ ሁለት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው እሁድ የካቲት 19፣ 2009 ዓም አርባምንጭ ከተማ ላይ በቅዱስ ጊዮርጊስ እና በአርባምንጭ ከነማ ቡድኖች መካከል የተደረገውን የእግር ኳስ ጨዋታ ተከትሎ፣ በፖሊስና በህዝብ መካከል በተፈጠረው ግጭት 2 ህጻናትና አንድ ጎልማሳ ተገድለዋል። የአይን እማኖች እንዳሉት ቅዱስ ጊዮርጊስ አርባማንጭን 4 ለ1 እየመራ በነበረበት ወቅት፣ በመጨረሻው ሰአት ላይ አንድ የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋች ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ባለፈው ዓመት የወጣውና የባጃጅና ታክሲ አሽከርካሪዎችን ለስራ ማቆም አድማ አነሳስቶ የነበረው የትራንስፖርት ህግ ካሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ ተግባራዊ በመሆኑ በባህርዳር ከፍተኛ ችግር እንደፈጠረ ተነገረ፡፡
የካቲት ፳፪ ( ሃያ ሁለት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ዓመት በአማራ ክልል የከተማ ታክሲዎችና ባጃጆች ላይ የወጣውና ከፍተኛ ተቃውሞ በማስነሳት ከሶስት ቀን በላይ የስራማቆም አድማ በማድረግ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲታገድ ተደርጎ የነበረው ህግ ካሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ ተግባራዊ መሆን በመጀመሩ ነዋሪዎችና አሽከርካሪዎች መቸገራቸውን ተናግረዋል፡፡ ታክሲዎችና ባጃጆች ሰሞኑን በተጀመረው በአንድ ምድብ ብቻ እንዲሰሩና ወደ የትኛውም የከተማዋ አካባቢ ለግል ጉዳይም ሆነ ...
Read More »በሞዛምቢክ 36 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ተያዙ
የካቲት ፳፪ ( ሃያ ሁለት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜናዊ ሞዛምቢክ የአውራጃ አስተዳደር በህገ ወጥመንገድ ወደ ሞዛምቢክ ገብተዋል ያላቸውን 36 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን በቁጥጥር ስር ማዋሉ የአገሪቱ ፖሊስ አስታወቀ። ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች በአንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ ተደብ ቀው መያዛቸውን የፖሊስ ቃል አቀባይ ዘካርያ ናኩቴ ለአገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል። በእስር ላይ የሚገኙትን ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ወደ ትውልድ አገራቸው ለመመለስ እንደሚሞከርም አክለው ተናገረዋል። ...
Read More »ኢህአዴግ አባላቱን ሳይቀር እየሰበሰበ በማሰር ላይ ነው
የካቲት ፳፩ ( ሃያ አንድ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜን ጎንደር ዞን በመተማ ወረዳ የኢህአዴግ አባላት ሳይቀር የጦር መሳሪያ ሽጣችሁዋል በሚል እየታሰሩ ነው። በሚሊሺያ ስም ያስታጠቃቸውን አባሎቹን ሳይቀር እያሰረ የሚገኘው አገዛዙ፣ በአካባቢው የተሰማሩት ወታደሮች የነጻነት ሃይሎችን ትደግፋላችሁ በሚል በጅምላ እየቀጡዋቸው ነው። አፈናው መሮት ለትግል ጫካ የገባ አንድ ታጋይ እንደገለጸው፣ በአሁኑ ሰአት አገዛዙን በክርክር ማሳመን ስለማይቻል፣ ህዝቡ አንድ ነገር ...
Read More »በመሃል አዲስ አበባ በሁሉም ክፍለከተሞች የሚኖሩ ነባር ነዋሪዎች ከይዞታቸው እንደሚነሱ አዲሱ ፍኖተ ካርታ አመለከተ
የካቲት ፳፩ ( ሃያ አንድ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስአበባ ከተማ የሚገኙ ነባር የሚባሉ ማስፋፊያዎች ጨምሮ ፒያሳ፣4 ኪሎ፣6 ኪሎ፣ ካዛንቺስ፣ለገሀር፣ ቂርቆስ፣ በቅሎ ቤት፣ ቦሌ፣ልደታ፣ቄራ፣ ጎተራ፣ ሳሪስ እና የመሳሰሉ አካባቢዎች በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎችን አንስቶ ወደሌላ አካባቢ የማስፈር ዕቅድ በአዲሱ ፍኖተ ካርታ (ወይም ማስተር ፕላን) መካተቱ ታውቋል። በአዲሱ ካርታ መሰረት ከዚህ ቀደም ይደረግ የነበረውን ወደጎን የመስፋት መርህ በማስቀረት ወደላይ ...
Read More »በተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ላይ የቀረበው ክስ ፖለቲካዊ ነው ሲል ሂውማን ራይትስ ወች አስታወቀ
የካቲት ፳፩ ( ሃያ አንድ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሶስት ወራት በፊት በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ከአውሮፓ ኅብረት ፓርላማ አባላት ጋር ለመወያየት ወደ ቤልጅየም በመሄድ በኅብረቱ ፓርላማ በመገኘት ንግግር አድርገው ሲመለሱ የታሰሩት የ60 ዓመቱ ዶ/ር መረራ ጉዲና እና ሌሎች የተቃዋሚ ድርጅት አባላት ላይ የቀረቡባቸው ክሶች ሕጋዊነት የሌላቸው ፖለቲካዊ ክሶች ናቸው ሲል የሂውማን ራይትስ ወች የምስራቅ አፍሪካ ዋና አጥኚ ፊሊክስ ...
Read More »በዶ/ር መረራ ላይ የተሰረተው ክስ ፖለቲካዊ ተልዕኮ ያለው ነው ሲል ሂውማን ራይስት ዎች ስጋቱን ገለጸ
ኢሳት (የካቲት 21 ፥ 2009) በዶ/ር መረራ ጉዲና ላይ ሰሞኑን የተመሰረተው ክስ ከህግ ይልቅ ፖለቲካዊ ተልዕኮ ያለው ነው ሲል ሂውማን ራይትስ ዎች ማክሰኞ ስጋቱን ገለጸ። የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አመራሩን ጨምሮ ሁሉም የፖለቲካ ዕስረኞች እንዲለቀቁ ጥሪውን ለኢትዮጵያ መንግስት ያቀረበ ሲሆን መንግስት ከህዝብ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽን ከመስጠት ይልቅ እየወሰደ ያለው እስራት እና ወከባ መፍትሄን እንደማያስገኝ በተመራማሪው ፊሊክስ ...
Read More »በኦሮሚያና ሶማሌ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች በተቀሰቀሰ ግጭት ከ400 በላይ ዜጎች መገደላቸው ተገለጸ
ኢሳት (የካቲት 21 ፥ 2009) የኦሮሚያ ክልልን ከሶማሌ ክልል ጋር በሚያዋስኑ አካባቢዎች የተቀሰቀሰው ግጭት ዕልባት አለማግኘቱንና በሁለቱ ወገኖች ከ400 በላይ ሰዎች መሞታቸውን የአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብቶች ሊግ ገለጸ። ካለፉት ስድስት ወራት ጀምሮ በፌዴራል መንግስት ድጋፍ ይደረግላቸዋል የተባሉ የሶማሌ ክልል ልዩ የፖሊስ አባላት 15 በሚሆኑ የኦሮሚያ ክልል ወረዳዎች መጠነ ሰፊ ጥቃት በመውሰድ ላይ መሆናቸውን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው ...
Read More »የአባይ ግድብ የሃይል ማመንጫ አቅሙ እንዲያድግ ተደርጓል መባሉ በግብፅ በኩል ስጋት አሳድሯል ተባለ
ኢሳት (የካቲት 21 ፥ 2009) በመገንባት ላይ ያለው የአባይ ግድብ የሃይል ማመንጫ አቅሙ በ450 ሜጋ ዋት እንዲያድግ ተደርጓል መባሉ በግብፅ በኩል ስጋት ማሳደሩን የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ማከሰኞ ዘገቡ። ሰሞኑን የኮሚኒኬሽን ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶር ደብረጽዮን ገብረሚካዔል በግድቡ ላይ በተደረገ ማሻሻያ 6ሺ ሜጋዋት የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ያቀርባል ተብሎ የነበረው ግድቡ ወደ 6450 ሜጋዋት ከፍ ማለቱን መግለጻቸው ይታወሳል። ይሁንና የግብፅ የውሃ ምህንድስና ...
Read More »ለህዝብና ቤቶች ቆጠራ ከተመደበው ሶስት ቢሊዮን ብር አንድ ቢሊዮኑ ለ180 ሺ ዘመናዊ ዲጂታል ታብሌቶች መግዣ ሊውል ነው
ኢሳት (የካቲት 21 ፥ 2009) በቀጣዩ አመት በኢትዮጵያ ሊካሄድ ለታቀደው የህዝብና ቤቶች ቆጠራ ከተመደበው ሶስት ቢሊዮን ብር መካከል አንድ ቢሊዮን ብር ለ180ሺ ዘመናዊ ዲጂታል ታብሌቶች (የእጅ ኮምፒውተሮች) መግዣ ተመደበ። ለቆጠራው ከሚያስፈልገው ገንዘብ ውስጥ አብዛኛው በአለም አቀፍ ተቋማት ድጋፍ የሚሸፍን መሆኑን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ሃላፊዎች መግለጻቸውን አዲስ ፎርቹን የተሰኘ የቢዝነስ ጋዜጣ ዘግቧል። ኤጀንሲው የዘመናዊ ኮምፒውተሮቹን በአንድ ቢሊዮን ብር ለመግዛት ባወጣው ጨረታ ...
Read More »