የካቲት ፳፬ ( ሃያ አራት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከጎንደር ብአዴን ጽ/ቤት በተገኝው መረጃ መሰረት በጎንደር ከተማ የተነሳውን ተቃውሞ ለማብረድ እና ሴቶችን ያማካለ ሰላም የማምጣት ስትራቴጅ በሚል በታቀደው መሰረት ከመንግስት በጀትና በG.F በጎንደር ከተማ በግሎባል ፈንድ ከተለገሰው ገንዘብ ተቀንሶ በብአዴን ስም የተለገሰ እና በረጅም ጊዜ ተመላሽ የሚሆን ከወለድ ነፃ የገንዘብ ድጋፍ ስራ በ1ኛ ዙር ለተመረጡ 657 ሴቶች ለእያንዳንዳቸው ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ታፍኖ የተወሰደው የሰማያዊ ፓርቲ አባል ያለበት ቦታ አልታወቀም
የካቲት ፳፬ ( ሃያ አራት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ወሎ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ የነበረው አቶ መኳንንት ካሳሁን ከሃሙስ የካቲት 16 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ ከስራ ቦታው በደኅንነቶች ታፍኖ ከተወሰደበት ጊዜ አንስቶ እስከዛሬ ያለበት አድራሻ ባለመታወቁ ወላጅ እናቱን ጨምሮ መላው ቤተሰቡ በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ መውደቃቸውን ለኢሳት ተናግረዋል። ደሴ ከተማ ውስጥ የሚኖረው አቶ መኳንንት ...
Read More »በአማራ ክልል የኮሌራ በሽታ በድጋሚ ተከሰተ፡፡
የካቲት ፳፬ ( ሃያ አራት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ዓመት ለበርካታ ዜጎች ሞት ምክንያት የነበረው የኮሌራ ወረርሽኝ በድጋሜ በባህር ዳር አካባቢ አንዳሳ ቀበሌ መከሰቱን ከጤና ጥበቃ ቢሮ የወጡ መረጃዎች አመላክተዋል፡፡ በበሽታው ከሰላሳ በላይ ሰዎች መለከፋቸውን የሚጠቁመው መረጃ ፣ ታማሚዎችን በባህርዳር ከተማ አዲስ በመሰራት ላይ ባለው ሆስፒታል ለማከም ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ታውቋል፡፡በሽታው በቀጣዩ የዝናብ ወቅት ሊቀጥል እንደሚችል የተናገሩት ...
Read More »121 ኛው የዐድዋ ድል በአል ተከበረ
የካቲት ፳፫ ( ሃያ ሦስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢትዮጵያውያን አርበኞች ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛትነት ለመያዝ ሃይላቸውን አሰባስበው የመጡትን የጣሊያን ወራሪዎች አድዋ ላይ ድል ያደረጉበት 121ኛው የነጻነት ቀን ተከብሮ ውሎአል። በዳግማዊ አፄ ሚኒልክ እና በባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱ ብጡል የተመራው ፣ ፊታውራሪ ሃብተጊዮርጊስ ዲነግዴንና ራስ አሉላ አባነጋን እና ሌሎችንም ሰመ ጥር ጅግኖችን ያሳተፈው ጦርነት የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በድል ...
Read More »ብአዴን ባህርዳር ጨርቃጨርቅ ፋብሪካን መጠቅለሉንና ዳሸን ቢራ በኪሳራ እየማቀቀ መሆኑን አስታወቀ
የካቲት ፳፫ ( ሃያ ሦስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የብአዴን የልማት ድርጅት የሆነው ጥረት ከርፖሬት ሰሞኑን በዋና ስራ አስፈፀሚው አቶ ታደሰ ካሳ በሰጠው መግለጫ ፣ ኮርፖሬቱ በአሁኑ ስዓት በርካታ ፋብሪካዎችን በመያዝ በክልሉ ቀዳሚ መሆኑን እንዲሁም ከኢጣሊያ በኢትዮጵያውያን ለደረሰው ግፍ የደም ካሳ ክፍያ ተብሎ የተገነባውን የባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካን መጠቅለላቸውን ተናግረዋል። በዳሸን ቢራ ግን ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶብናል ብለዋል። ...
Read More »በመላ ሀገሪቱ የተከሰተውን ተቃውሞ ተከትሎ የገንዘብ እጥረት እንደገጠመው ሚኒስቴሩ አስታወቀ
የካቲት ፳፫ ( ሃያ ሦስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአገሪቱ የተከሰተውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለማስቆም ከፍተኛ ገንዘብ ወጭ በማድረጉ በዚህ አመት ለመንግስት ተቋማት የስራ ማስኬያጃ የሚውል ከፍተኛ የበጀት መዋዥቅ እንደገጠመው የገንዘብ እና የኢኮኖሚ ትብብር ሚንስትር ገለፀ፡፡ በዚህም የተነሳ በኦሮምያና በአማራ ክልሎች የመስክ ስራዎች እየተቋረጡ ነው። የሚንስትሩ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ካህሳይ ባህታ ፣ በአማራ እና ኦሮምያ ክልሎች በተካሄዱ ህዝባዊ ...
Read More »በደቡብ ኦሞ የረሃብ አድማ ከጀመሩ አራት የኅሊና እስረኞች መካከል አንደኛው ራሱን ስቶ ሆስፒታል ገባ
የካቲት ፳፫ ( ሃያ ሦስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ኦሞ ዞን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎ ተይዘው ከነበሩት 10 የኅሊና እስረኞች ውስጥ ስድስቱ ከተፈቱ ሦስት ሳምንት በኋላ ከትናንት በስቲያ ሰኞ የረሃብ አድማ መጀመራቸው ከተዘገበ በሁዋላ፣ አቶ አባስ አብዱላሂ ራሱን በመሳቱ ሆስፒታል ተወስዶ ‹የህክምና ዕርዳታ ተደርጎለት መመለሱን የዓይን እማኞች ገለጸዋል ፡፡ የአቶ አባስን በጠኔ መውደቅ ተከትሎ የታሳሪ ቤተሰቦች በፖሊስ ...
Read More »የደቡብ ክልል ወጣቶች “የደህዴን ኢህአዴግ አገዛዝ በቃን” ሲሉ ተናገሩ
የካቲት ፳፫ ( ሃያ ሦስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የደህዴን የወጣቶች ሊግ ከመላው የደቡብ ክልል ወጣቶችን አበል ከፍሎ በወልቂጤ ከተማ በማሰባሰብ፣ የክልሉን ሰላምና እና እድገት ለመስበክ ያደረገው ሙከራ አለመሳካቱን ምንጮች ገልጸዋል። “የመንግስቱ ሚዲያዎች ሁሉ ሀሰተኛ ናቸው፣ መንግስትንም ለማጥፋት የኛ እጅ በቻ በቂ ነው” በማለት አንዳንድ ወጣቶች ሲናገሩ፣ ሌሎች ደግሞ “ደህዴን ምንም አልሰራም፣ ክልሉን ወደ ኃላ ያስቀረ እና በድህነት ...
Read More »በወረዳ 6 የታዋቂውን ሊቅ የአለቃ አያሌው መኖሪያ ቤትን ጨምሮ በርካታ ቤቶች የማፍረስ ዘመቻ ተጀመረ
የካቲት ፳፫ ( ሃያ ሦስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ ከተማ በወረዳ 6 ቀበሌ 11የቤት ቁጥር 207 ተክለሃይማኖት አካባቢ የሚገኘው የታዋቂው የሃይማኖት አባት አለቃ አያሌው ታምሩ መኖሪያ ቤትን ጨምሮ በአካባቢው የሚገኙ በርካታ ቤቶች እንደሚፈርሱ ታውቋል። በጽኑ ታመው አልጋ የያዙት ባለቤታቸው እና ልጆቻቸውን ቤታቸውን በሁለት ቀናት ውስጥ እንዲያፈርሱ መመሪያ ተሰጥቷቸዋል። ከ50 ዓመታት በላይ ጎጆ ቀልሰው የኖሩበትን የሊቀ ሊቃውንት ...
Read More »121ኛው የአድዋ ድል በአል በደማቅ ሁኔታ ተከበረ
ኢሳት (የካቲት 23 ፥ 2009) ኢትዮጵያውያን ከ100 አመት በፊት ወራሪው የኢጣሊያ ጦርን በአድዋ ድል ያደረጉት 121ኛው የአድዋ ድል በአል ሃሙስ በደማቅ ሁኔታ ተከበረ። የበአሉ አከባበር በመዲናይቱ አዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው በዳግማዊ ሚኒሊክ አደባባይ አባት አርበኞች፣ እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የውጭ ሃገራት ተወካዮች በተገኙበት መከበሩ ከሃገር ቤት ከተገኘ መረጃ ለመረዳት ተችሏል። በዚሁ አመታዊ በዓል አከባበር ላይ የታደሙ ...
Read More »