ኢሳት (የካቲት 27 ፥ 2009) በጎንደር ከተማ ከንቲባ መኖሪያ ቤት ላይ የቦንብ ጥቃት ተፈጸመ። ጥቃቱን የፈጸመው አካል ማንነት አልታወቀም። በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች በጥርጣሪ ተሰብሰብው ታስረዋል። በሰሜን ጎንደር ዞን የጎንደር ከተማ ከንቲባ የሆኑት አቶ ተቀባ ተባባል መኖሪያ ቤት ላይ ጥቃቱ የተፈጸመው ቅዳሜ ሌሊት 10 ሰዓት ላይ መሆኑን የገለጹት ምንጮች በጥቃቱ በሰው ላይ ጉዳት አለመድረሱን አመልክተዋል። ቅዳሜ ለዕሁድ አጥቢያ ከሌሊቱ 10 ሰዓት ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በከንቲባው ቤት ላይ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ በጎንደር የሚደረገው ፍተሻ ተጠናክሮ ቀጥሎአል
የካቲት ፳፯ ( ሃያ ሰባት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በጎንደር ከተማ ያለፈው ቅዳሜ ከሌሊቱ 10 ሰዓት ላይ በጎንደር ከተማ ከንቲባ አቶ ተቀባ ተባባል መኖሪያ ቤት ላይ የቦንብ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ፣ በርካታ የፌደራል ፖሊስና የመከላከያ አባላት የአካባቢውን ህዝብ ሲያዋክቡ መሰንበታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ። ጥቃቱ በግለሰቡ ላይ ያደረሰው ጉዳት ይኑር አይኑር የታወቀ ነገር ባይኖርም፣ ጥቃቱ እንደተሰማ አካባቢው በወታደሮች ታጥሮ የጥቃቱን ...
Read More »በጂንካ የሙስሊም አመራሮች ታሰሩ
የካቲት ፳፯ ( ሃያ ሰባት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ ከተማ ሦስት የሙስሊም አባቶች ካለፈው አርብ ጀምሮ እስካሁን ምክንያቱ ባልተገለጸላቸው ሁኔታ በጂንካ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው እንደሚገኙ ምንጮች ገለጹ፡፡ አባቶችን ለመያዝ በዞኑ ኮማንድ ፖስት ትዕዛዝ ቤታቸውን የፈተሸው ቡድን ከሃይማኖታዊ ስነስርዓት ውጭ በሆነ ሁኔታ መስገጃቸውን በጫማቸው በመርገጥ ፣ የህጻናት የመማሪያ ደብተሮች ሳይቀር በማገላበጥና የቤት ዕቃዎችን በመበታተን ...
Read More »በዶ/ር መረራ፣ ፕሮፌሰር ብርሃኑ፣ ኢሳትና ኦኤምኤን ላይ የተመሰረተው ክስ ለችሎት ማሰማት ተጀመረ
ኢሳት (የካቲት 24 ፥ 2009) ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሰሞኑን በዶ/ር መረራ ጉዲና፣ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እንዲሁም በኢሳትና በኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ላይ የመሰረተውን ክስ ሃሙስ ለችሎት ማሰማት ጀመረ። ባለፈው ሳምንት ፍርድ ቤት መቅረብ ያልቻሉ ዶ/ር መረራ ጉዲና በችሎት የተገኙ ሲሆን፣ የቀረበባቸውን ሽብርተኛ ቡድን መደገፍ ኣንዲሁም በማነሳሳት በዋና ወንጀል አድራጊነት ተከፋይ በመሆን የሽብር ወንጀል ክስ እንደተነበበላቸው የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ዶ/ር መረራ ...
Read More »በኦሮሚያና ሶማሌ ድንበር አካባቢዎች የተከሰተው ግጭት ወደ ተለያዩ አካባቢዎች እየተዛመተ መሆኑ ተገለጸ
ኢሳት (የካቲት 24 ፥ 2009) የኦሮሚያ ክልልን ከሶማሌ ክልል ጋር በሚያዋስኑ የድንበር አካባቢዎች በመካሄድ ላይ ያለው ግጭት ዕልባት አለማግኘቱንና ወደ ተለያዩ ቀበሌዎች በመዛመት ላይ መሆኑን ነዋሪዎች ገለጹ። በምስራቅ ሃረርጌ ጨናቅሳን ተብሎ በሚጠራ ከተማ ያሉ ነዋሪዎች የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይሎች የኦሮሚያ ክልልን ጥሰው በመግባት እየፈጸሙት ባለው ጥቃት ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ ከ100 በላይ ነዋሪዎች መገደላቸውን አስታውቀዋል። በዚሁ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ ...
Read More »በሶማሊያ የሚገኘው የኬንያ መከላከያ ሰራዊት በትንሹ 57 ታጣቂዎችን መግደሉን አስታወቀ
ኢሳት (የካቲት 24 ፥ 2009) በሶማሊያ ተሰማርቶ የሚገኘው የኬንያ መከላከያ ሰራዊት ከአል-ሸባብ ታጣቂ ሃይል ጋር ባካሄደው ውጊያ በትንሹ 57 ታጣቂዎችን መግደሉን አስታወቀ። በታችኛው ጁባ የደቡባዊ ሶማሊያ ግዛት ተካሄዷል በተባለው በዚሁ የሁለቱ ወገኖች ፍልሚያ የጦር ሄሊኮፕተሮችን ጨምሮ የተለያዩ ከባድ መሳሪያዎች ጥቅም ላይ ውለው እንደነበር የኬንያ መከላከያ ሰራዊት ቃል አቀባይ ኮሎኔል ጆሴፍ አውቱ ለጋዜጠኞች መግለጻቸውን ዘ-ስታንዳድር የተሰኘ ጋዜጣ ዘግቧል። ሃጋን እና አፍማዶ ...
Read More »በአውሮፓ ህብረት በሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ ዙሪያ የኢትዮጵያ ጉዳይ አለመካተቱ ቅሬታ እንዳሳደረበት አንድ ተቋም ገለጸ
ኢሳት (የካቲት 24 ፥ 2009) የአውሮፓ ህብረት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውስጥ በተያዘው የፈረንጆች 2017 አም በሰብዓዊ መብቶች ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረትን እንዲያገኙ ያወጣውን አጀንዳ የኢትዮጵያ ጉዳይን አለማካተቱ ስጋት እንዳሳደረበት አንድ አለም አቀፍ ተቋም ገለጸ። መቀመጫውን በኔዘርላንድ ቤልጅየም ያደረገው Unrepresented Nations and People’s Organization የተሰኘው ይኸው ተቋም በኢትዮጵያ ያለው የሰብዓዊ መት ሁኔታ ከመቼው ጊዜ በላይ አሳሳቢ መሆኑን አመልክቷል። ይሁንና የሃገሪቱ ወቅታዊ የሰብዓዊ ...
Read More »የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ከ3ሺ በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን ተመድ ገለጸ
ኢሳት (የካቲት 24 ፥ 2009) የደቡብ ሱዳን የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች በጋምቤላ ክልል በፈጸሙት ጥቃት ከሶስት ሺ በላይ ነዋሪዎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅቱ አስታወቀ። በኦጃሎ በኦትዎል እና አጎራባቸው ባሉ ቀበሌዎች ካለፈው ወር ጀምሮ በተፈጸሙ የድንበር ዘለል ጥቃቶች የሞቱ ሰዎች መኖሩን ቢያረገግጥም ቁጥራቸው ከመግለጽ ድርጅቱ ተቆጥቧል። ከቀያቸው የተፈናቀሉ 3ሺ 714 ነዋሪዎች በአሁኑ ወቅት በአንጎይ ከተማ እንዲሁም በአለሚና ቶ’ኦ ቀበሌዎች ተጠልለው እንደሚገኙ ...
Read More »የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የፊታችን ማክሰኞ ስድስተኛ ወሩን ይይዛል
የካቲት ፳፬ ( ሃያ አራት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ በኦሮሚያ፣ አማራ እና ደቡብ ክልሎች የገጠመውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ለማስቆም የሚኒስትሮች ም/ቤት መስከረም 28 ቀን 2009 ዓ.ም ያወጣው የአስቸኳዋ ጊዜ አዋጅ የተቀመጠለትን የስድስት ወራት ጊዜ ሊጨርስ አራት ቀናት ብቻ ቢቀሩትም፣ አዋጁን ለማንሳት ፍንጭ አለመታየቱ አዋጁ ሊራዘም ይችላል የሚለውን ግምት እያጠናከረው መጥቷል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎ ሀገሪትዋ በወታደራዊ አገዛዝ ...
Read More »በሶማሊ እና በኦሮምያ ክልሎች ድንበር አካባቢ የሚታየው ውጥረት መቀጠሉን ተከትሎ ነዋሪዎች እየሸሹ ነው
የካቲት ፳፬ ( ሃያ አራት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚናገሩት የሶማሊ ልዩ ሚሊሺያ ወደ ኦሮምያ ክልል በመግባት በህዝብ ላይ በቀጥታ በመተኮስ ከፍተኛ አደጋ ያስከተለ ሲሆን፣ በምስራቅ ሃረርጌ በሚገኙ አንዳንድ አካባቢዎች የሶማሊ ክልል አርማን እያውለበለቡ መሬቱ የእነሱ እንደሆነ እየተናገሩ ነው። ከልዩ ሃይሉ የሚሰነዘረውን ጥቃት ለመቋቋም የሞከሩ የኦሮምያ ክልል ነዋሪዎች ፣ ልዩ ሃይሉ ከመከላከያ ሰራዊት አባላት ጋር በመተባበር ...
Read More »