መጋቢት ፩ (አንድ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዶ/ር መረራ ጉዲና የዋስትና መብት መከልከላቸውን አስመልክቶ እየተፈጸመባቸው ያለውን የመብት ጥሰቶች የኢትዮጵያ ሕዝብ እዲያውቅላቸው ከእስር ቤት ደብዳቤ ልከዋል። የተከሰስኩት ምንም ዓይነት ሕገወጥ ወንጀል ፈጸሜ ሳይሆን ለዘመናት ለአገሬና ለህዝብበመታገሌ መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ ይወቅልኝ ብለዋል። ከእነ ጀነራል መንግስቱ ነዋይ እና ጄኔራል ታደሰ ብሩ ዘመን ጀምሮ ከአንድ ትውልድ በላይ ገዳዮችና ሟቾች፣ ታሳሪዎች እና አሳሪዎች፣ በበዙበት ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የአዲስ አበባ ታክሲ አሸከርካሪዎች ፍትህ አጣን ይላሉ
መጋቢት ፩ (አንድ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ህዳር ወር የስራ ማቆም አድማ መተው የነበሩት የአዲስ አበባ ታክሲ አሽከርካሪዎች፣ ከአድማው በሁዋላ ችግራቸው እንደሚፈታላቸው ተነግሯቸው የነበረ ቢሆንም፣ አሁንም በችግር እየተሰቃዩ መሆኑን ገልጸዋል። “መድረሻ አጥተናል፣ መቆሚያችንን ለሰላም ባስ ለሚባለው ለቀን ወጥተናል። የሰቀቀን ኑሮ ነው የምንኖረው” የሚሉት አሽክርካሪዎች ዳኝነት ጠፍቷል በማለት ምሬታቸውን ገልጸዋል። ኢህአዴግ የጥፋት ሪከርድ ምዝገባ ተወግዷል ቢልም የገንዘብ ቅጣቱ ጨምሮ ...
Read More »አርበኞች ግንቦት 7 በሰሜን ጎንደር ጥቃት ፈጽሞ እስረኞችን አስለቀቀ
ኢሳት (መጋቢት 1 ፥ 2009) የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሃይሎች በሰሜን ጎንደር ወገራ ወረዳ ችንፋዝ በገና ሲራሬ ከተማ ሰርገው በመግባት በፈጸሙት ጥቃት እስረኞችን አስለቀቁ። ታጋዮቹ ትናንት የካቲት 30: 2009 አም ምሽት ከ4 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋት በከተማ ባሉ የመንግስት ታጣቂዎች ላይ በፈጸሙት ጥቃት የህወሃት/ኢህአዴግ ወታደሮች ገድለዋል። የተወሰኑ የከተማዋ ታጣቂዎች ለአርበኞች ግንቦት ሰባት ታጋዮች ድጋፍ በመስጠት በህወሃት ኢህአዴግ ወታድሮች ላይ ጥቃት ፈጽመዋል። ከፊሎችም ...
Read More »አሜሪካ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ያላትን ግንኙነት ታቋርጥ ሲሉ የአሜሪካ ምክር ቤት አባላት ጠየቁ
ኢሳት (መጋቢት 1 ፥ 2009) ዩ ኤስ አሜሪካ ከጨቋኙ የኢትዮጵያ መንግስት ጋር ግንኙነቷን ታቋርጥ ሲሉ የአሜሪካ ምክር ቤት አባል ኮንግረስ ማን ክሪስ ስሚዝ ጥሪ ሲያቀርቡ ሌላው የምክር ቤት አባል ኮንግረስ ማን ዳና ሮራባከር ዩ ኤስ አሜሪካ አናሳዎችን ብቻ ከሚወክለው የኢትዮጵያ መንግስት ጋር የነበራት ግንኙነት ስህተት መሆኑን ተቀብላ ለሁለቱ ሃገራት ጥቅም የኢትዮጵያን ህዝብ መሰረት ያደረገ ግንኙነት እንድታደርግ ጥሪ አቅርበዋል። በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ...
Read More »ዶ/ር መረራ ጉዲና የጠየቁት የዋስትና መብት ጥያቄ ውድቅ ተደረገ
ኢሳት (መጋቢት 1 ፥ 2009) ዶ/ር መረራ ጉዲና የተመሰረተባቸው ክስ እስከ ሞት የሚደርስ ቅጣት ሊያሰጥ የሚችል ነው በማለት ፍርድ ቤት ያቀረቡትን የዋስትና መብት ጥያቄ አርብ ውድቅ አደረገ። የፌዴራሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዶ/ር መረራ ለፍርድ ቤት ያቀረቡትን የዋስትና መብት ጥያቄ በመቃወም ሃሙስ ለፍርድ ቤቱ ባለሁለት ገፅ የተቃውሞ ጥያቄ አቅርቦ እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል። አርብ በዚሁ ጉዳይ ላይ ብይን ለመስጠት የተሰየመው ችሎት የኦሮሞ ...
Read More »የኢትዮጵያ ብር የመግዛት አቅሙ አሽቆለቆለ
ኢሳት (መጋቢት 1 ፥ 2009) የኢትዮጵያ የመገበያያ ገንዘብ የሆነው ብር ባለፉት 12 ወራቶች ብቻ የመግዛት አቅሙ ከአምስት በመቶ በላይ ማሽቆልቆሉን አለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት አስታወቁ። የብር የመግዛት አቅም እየቀነሰ መምጣት በህብረተሰቡ ላይ ከሚያደርሰው የኢኮኖሚ ተፅዕኖ በተጨማሪ የሃገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገትና የዋጋ ግሽበት እየተፈታተነ እንደሚገኝም የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ገልጸዋል። መንግስት አጋጥሞት ያለውን የፋይናንስ እና የውጭ ምንዛሪ ክምችት እጥረት የብር የመግዛት አቅም እየቀነሰ ...
Read More »ጃፓን በደቡብ ሱዳን አሰማርታ የምትገኘውን የሰላም አስከባሪ ሃይል ለማስወጣት ወሰነች
ኢሳት (መጋቢት 1 ፥ 2009) የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ በደቡብ ሱዳን ተሰማርተው የሚገኙ የጃፓን የሰላም አከባሪ ሃይሎች ከአንድ ወር በኋላ ጠቅልለው እንደሚወጡ መግልጻቸውን ቢቢሲ የጃፓኑን ዜና አገልግሎት (ኪዮዳን) ዋቢ በማድረግ ዘግቧል። ደቡብ ሱዳን ወደ አዲስ መንግስት ግንባታ በመሸጋገሯ ጃፓን በተለያዩ ዘርፎች ስትሰጥ ከቆየችው ድጋፍ ለመውጣት ወስናለች ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል። የጃፓን ባለስልጣናት የተወሰደው ዕርምጃ እያሽቆለቆለ ከመጣው የደቡብ ሱዳን የጸጥታ ...
Read More »የመምህራን የግምገማ ሪፖርት በኢሳት መተላለፉ በኢህአዴግ ውስጥ ከፍተኛ ቁጣ ፈጥሯል።መምህራኑ ዳግም ትሃድሶ እንዲያደርጉ የታዘዙበት ሰነድም እጃችን ገብቷል
የካቲት ፴ (ሠላሳ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቅርቡ የሁለተኛ ደረጃ መምህራን አስደንጋጭ የተሃድሶ ግምገማ ሪፖርት በኢሳት መተላለፉን ተከትሎ ድንጋጤ ውስጥ የገባው ኢህአዴግ፣ አሁን ደግሞ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንና ተማሪዎች ዳግም ትሃድሶ እንዲያካሂዱ ቀጭን ትእዛዝ ተላልፏል። ዩኒቨርስቲዎችም ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ትሃድሷቸውን እንዲወጡ በታዘዙት መሰረት፣ ትምህርት ዘግተው የተሃድሶ ውይይታቸውን እያደረጉ ነው። ትምህርት ሚኒስቴር በ25/06/2009 ዓም “ አስቸኳይ ዳግም ተሃድሶ መምህራን እና ...
Read More »የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ድርድሩ እንደማይሳካ እየገለጹ ነው።
የካቲት ፴ (ሠላሳ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮምያ፣ አማራና ደቡብ አካባቢዎች የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ በአገር ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ጋር እነጋገራለሁ ያለው ኢህአዴግ፣ ለእውነተኛ ድርድር ከልቡ ያልተዘጋጀ በመሆኑ ድርድሩ እንደማይሳካ፣ በምርጫ 97 ወቅት “ከኢህአዴግ ጋር መስራት ይቻላል” ብለው ከቅንጅት ወጥተው ለ5 ዓመታት የፓርላማ አባል ሆነው ያገለገሉት አቶ አብዱረህማን አህመዲን ተናግረዋል። ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ በየነም ድርድሩን አጣጥለውታል። ስለድርድሩ ጠቀሜታ እንዲናገሩ ...
Read More »የወልቃይት ጉዳይ የአማራ ክልልንም ሆነ ብአዴንን አያገባውም ሲሉ ም/ል ፕሬዚዳንቱ ተናገሩ
የካቲት ፴ (ሠላሳ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ንጉሱ ጥላሁን ከክልሉ ጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ ሲሰጡ፣ “ስለወልቃይት ጉዳይ የሚያገባው የትግራይ ክልልና የፌዴሬሽን ምክር ቤት እንጅ የአማራ ክልል አይደለም” ብለዋል። “ በወልቃይት፣ በራያ እና ሌሎችም አካባቢዎች፣የትግራይ ክልል ከአማራ ክልል መሬት እየወሰደ ነው፣ ዳሸን ተራራና ላሊበላ ሳይቀር የእኔ ነው እያለ ነው፤ በየጊዜውም በትግራይ መገናኛ ብዙሃን የታጠቁ ሰዎች ...
Read More »