.የኢሳት አማርኛ ዜና

አንድ የእንግሊዝ ኩባንያ ከአፋር ክልል የፖታሽ ማዕድን ለማምረት ፈቃድ ተሰጠው

ኢሳት (መጋቢት 5 ፥2009) መቀመጫውን በብሪታኒያ ያደረገ አንድ የፖታሽ የማዕድን አምራች ኩባንያ በአፋር ክልል ለቀጣዮቹ 20 አመታት የማዕድን ሃብቱን ለማምረት የሚያስችለው ፈቃድ በኢትዮጵያ መንግስት እንደተሰጠው ማክሰኞ ይፋ አደረገ። በሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔን እንዲያገኝ ተደርጓል በተባለው በዚሁ ልዩ ፈቃድ ሲርከም (Circum) የተሰኘው ኩባንያ በብቸኝነት በአፋር ክልል በዳናክል አካባቢ ከአራት እስከ ዘጠኝ ቢሊዮን ቶን የሚጠጋ ፖታሽ ማዕድን ማምረት እንዲያችለው ማይኒንግ ዊክሊይ የተሰኘ ...

Read More »

በአዲስ አበባ የቆሻሻ መጣያ ሰፈር በደረሰው አደጋ የሟቾች ቁጥር እያሻቀበ ነው

መጋቢት ፬ (አራት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኮልፌ ቀራንዩ ወረዳ 01 በተለምዶ ቆሸ ሰፈር ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ በተፈጠረው የቆሻሻ ክምር መደርመስ የሟቾች ቁጥር ከ50 በላይ የደረሰ ሲሆን፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አሁንም እንደጠፉ መሆናቸውን ያነጋገርናቸው ሰዎች ገልጸዋል። አብዛኞቹ ሟቾች ሴቶችና ህጻናት ሲሆን፣ አስከሬን የመፈለጉ ስራ ቀጥሏል። አስከሬን ሲያወጡ የነበሩ ወጣቶች እንደገለጹት ቁራን ሲቀሩ የነበሩ ህጻናት እንዲሁም፣ ከወለደች 3 ቀናት የሆናት ...

Read More »

ኦህዴድ ከሶማሊ ድንበር ጋር በሚዋሰኑ ወረዳዎች ላይ ለተፈጸመው ጥቃት የሶማሊ ክልልን ተጠያቂ አደረገ

መጋቢት ፬ (አራት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኦሮምያ የኮሚኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ በጻፉት ጽሁፍ በምስራቅ ሃረርጌ ዞን ስር ባሉ ቁምቢ፣ጭናክሰን፣ ሚደጋ ቶላ፣ጉርሱም፣መዩ ሙሉቄ እና ባቢሌ ወረዳዎች፤ በምዕራብ ሀረርጌ ዞን የሚገኘዉ የጉምቢ ቦርዶዴ ወረዳ፣ በባሌ ዞን የሚገኙት ዳዌ ሰረር፣ሰዌና፣ መደ ወላቡ እና ራይቱ ወረዳዎች፣በጉጂ ዞን ጉሚ ኢደሎና ሊበን ወረዳዎች በቦረና ዞን የሚገኘዉ ሞያሌ ወረዳ ላይ ጥቃት መፈጸሙን አውስተው፣ ...

Read More »

የህውሃት የበላይነት አለ ያሉ በብአዴን አመራር ስብሰባ ላይ በልዩነት የወጡ አመራሮች ከኃላፊነት ተነሱ

መጋቢት ፬ (አራት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በክልሉ የብአዴን ውይይት እና የካቢኔ አመራር ስብሰባ ላይ “ የህወሃት የበላይነት አለ” በማለት በልዩነት የወጡ የክልል አመራሮች ከስልጣን ተባረዋል። የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ም/ኃላፊ አቶ ቹቹ እና የክልሉ ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ የሻምበል በውይይቱ ላይ “ ህወሃት አገሪቱን በበላይነት እየመራት ነው፣ ሌሎች ፓርቲዎች ያላቸው ኃላፊነት በእጅጉ የወረደ ነው” የሚል ሃሳብ በማንሳት ...

Read More »

በአዲስ አበባ በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የተከሰተው አደጋ በአካባቢው በመገንባት ላይ ባለ በባዮ-ጋዝ ፕሮጄክት ምክንያት መሆኑ ተገለጸ 

ኢሳት (መጋቢት 4 ፥ 2009) በአዲስ አበባ በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ለ65 ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው አደጋ በአካባቢው በመገንባት ላይ ያለ የባዮጋዝ ፕሮጄክት ምክንያት መሆኑን ነዋሪዎች ገለጹ። በከተማዋ አስተዳደር በመካሄድ ላይ ላለው ለዚሁ ግንባታ መሬቱን ለማስተካከል ሲከናወኑ የቆዩ ስራዎች በቆሻሻ ክምሩ ላይ ጭነት ማሳደሩንና ለአደጋው መንስዔ መሆኑን ሮይተርስ ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ ሰኞ ዘግቧል። አቶ ብርሃኑ ደግፌ የተባሉ የአካባቢው ነዋሪና ...

Read More »

በጎንደር ከተማ በእግር ኳስ ደጋፊዎችና በጸጥታ ሃይሎች መካከል ግጭት ተነስቶ ጨዋታው ተቋርጦ ነበር ተባለ

ኢሳት (መጋቢት 4 ፥ 2009) እሁድ በጎንደር ከተማ በኢትዮጵያ ቡናና በፋሲል ከነማ መካከል የተካሄደ የእግር ኳስ ጨዋታ በደጋፊዎችና በጸጥታ ሃይሎች መካከል ግጭት በማስነሳት ጨዋታው ለጥቂት ጊዜያት እንዲቋረጥ ማድረጉን እማኞች ለኢሳት አስታወቁ። የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታው በጎንደር ከተማ ስታዲየም በመካሄድ ላይ እንዳለ የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች የተለያዩ መፈክሮችን ማሰማት በጀመሩ ጊዜ በድርጊቱ ቅሬታ የተሰማቸው የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ዕርምጃ ለመውሰድ ሙከራ አድርገው እንደነበር ታውቋል። ...

Read More »

የብሪታኒያ መንግስት ለኢትዮጵያና ሌሎች አገራት ሲሰጥ የቆየው የገንዘብ ድጋፍ ብክነት አሳይቷል ተባለ

ኢሳት (መጋቢት 4 ፥ 2009) የብሪታኒያ መንግስት ለኢትዮጵያና ሁለት የአፍሪካ ሃገራት ለአማራጭ የሃይል አቅርቦት ፕሮጄክቶች ሲሰጥ የቆየው በመቶ ሚሊዮን ፓውንድ ስተርሊንግ የሚቆጠር የገንዘብ ድጋፍ “ብክነት” አስከትሏል የሚል ጥያቄን አስነሳ። ሃገሪቱ ለዚሁ ፕሮጄክት ከስምንት አመት በፊት ወደ ሁለት ቢሊዮን ፓውንድ የሚጠጋ ገንዘብ ብትመድብም በኢትዮጵያ፣ ኬንያ እንዲሁም በማሊ የሃይል አማራጭን ተግባራዊ ለማደረግ የተከናወኑ ስራዎች ከፍተኛ የገንዘብ ብክነት ታይቶባቸዋል የሚል ጥያቄ ማስነሳቱን ቴሌግራፍ ...

Read More »

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር የተማዋን የትራንስፖርት አገልግሎት መቅረፍ አልቻለም ተባለ

ኢሳት (መጋቢት 4 ፥ 2009) በቅርቡ ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ተገንብቶ አገልግሎት መስጠት የጀመረው የአዲስ አበባ ቀላል የባቡር መስመር አገልግሎት የከተማዋን የትራንስፖርት ችግር መፍታት ሳይችል መቅረቱን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ (AFP) ዘገበ። በከፍተኛ የውጭ ብድር የተገነባው የባቡር አገልግሎት የከተዋን ነዋሪዎች ፍላጎት ማሟላት ባለመቻሉ ምክንያት ተጠቃሚዎች ፊታቸውን ወደ መለስተኛ አውቶቡስ የታክሲ አገልግሎት እያዞሩ መሆኑን የዜና አውታሩ በጉዳዩ ዙሪያ ባቀረበው ሪፖርት አመልክቷል። ...

Read More »

የሃዘን መግለጫ

ቅዳሜ መጋቢት 2, 2009 አም በአዲስ አበባ ከተማ በደረሰው አሰቃቂ አደጋ የመላው የኢሳት ቤተሰብ የተሰማው ሃዘን እየገለጸ፣ ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እንመኛለን። በትንሹ ከ60 በላይ ኢትዮጵያውያን ያለቁበትና አሁንም የሟቾቹ ቁጥር እየጨመረ የሚገኘውን ይህን አደጋ በተመለከተ ኢሳት የሶስት ቀና ሃዘን እንዲሆን ወስኗል። ከማክሰኞ መጋቢት 5 ጀምሮ እስከ ሃሙስ መጋቢት 7 2009 በሚቆየው የሃዘን ቀን በኢሳት ማናቸውም ሙዚቃዎች የማይተላለፉ ሲሆን፣ ፕሮግራሞቹ  በሃዘን መግለጫዎች ይታጀባሉ። ...

Read More »

በህዝባዊ ወያነ ኃርነት ትግራይ-ህወኃት መሪነት በጋምቤላ የተቀናጀ ጭፍጨፋ እየተደረገ ነው ተባለ

መጋቢት ፩ (አንድ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የጋምቤላ ኒሎቴ አንድነት ንቅናቄ ለኢሳት በላከው መግለጫ በአሁኑ ወቅት ጋምቤላ ውስጥበታጠቁ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች እንዲሁም የንዌርና ሙርሌ ጎሳ በሆኑ የግመል አርቢዎች አማካይነት መጠነ ሰፊ ጥቃት እየተፈጸመ እነደሆነ በመጥቀስ ድርጊቱን አጥብቆአውግዟል። እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር መጋቢት 1 ቀን 2017 አመተ ምህረት ከደቡብ ሱዳን የተነሱ የታጠቁየሙርሌ ሚሊሻዎች ድንበር አሳብረው በመግባት በኦቱዎል መንደር በጆር ቀበሌ ስምንት ሰዎችን ...

Read More »