መጋቢት ፲፭ (አሥራ አምስት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰሞኑን የግድቡን ምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ ለጉብኝት የተጋበዙ የህብረተሰቡ ክፍሎችና ጋዜጠኞች፤የፕሮጀክቱ ኃላፊዎች ግድቡ የደረሰበትን ደረጃ በመቶኛ የመግለጽ ፍላጎቱ እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡ የግድቡን ምስረታ በዓል በከፍተኛ ፌሽታ ለማክበር ላይ ታች የሚለው የህውሃት /ኢህአዴግ መንግስት ባለስልጣናት ከተለያዩ ሚዲያዎችና ከቻግኒ ከተማ የተሰባሰቡ የስርዓቱ ደጋፊዎችን በማስጎብኘት ስለግድቡ ስራ መቀጠል ለማስረዳት ቢሞክሩም የግድቡ ስራ ግንባታ በታለመለት መልኩ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ከደሴ ከተማ ታግተው የተወሰዱት አቶ መኳንንት ካሳሁን እና አቶ ብስራት አቢ በማዕከላዊ የወንጀል ምርመራ ከፍተኛ ድብደባና ሰቆቃ እየተፈፀመባቸው ነው
መጋቢት ፲፭ (አሥራ አምስት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ወሎ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ የነበረው አቶ መኳንንት ካሳሁን እና የማእከላዊ ኮሚቴ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ የሆኑት አቶ ብስራት አቢ ከስራ እና ከመኖሪያ ቤታቸው ታግተው ከአንድ ወር በላይ አድራሻቸው መጥፋቱ ይታወሳል። ከሕግ አግባብ ውጪ ታፍነው የተወሰዱት ሰላማዊ ታጋዮቹን አድራሻ ለማግኘት ቤተሰቦቻቸው ባደረጉት ጥረት በማዕከላዊ እስር ቤት ውስጥ ...
Read More »በሜዲትራኒያን ሁለት ጀልባዎች መስመጣቸውን ተከትሎ ከ200 በላይ መንገደኞች ሞተው ሊሆን ይችላል ተባለ
ኢሳት (መጋቢት 15 ፥ 2009) ከሊቢያ ወደ ጣሊያን በማቅናት ላይ የነበሩ ሁለት ጀልባዎች በሜዲትራኒያን ባህር ላይ የመስጠም አደጋ አጋጥሟቸው ከ200 በላይ መንገደኞች ሞተዋል የሚል ስጋት ማሳደሩን የነብስ አድን ሰራተኞች አስታወቁ። እያንዳንዳቸው ከ100 በላይ ስደተኞችን አሳፍረው ይጓዙ የነበሩት ጀልባዎች ከአቅማቸው በላይ ሰው በመጫናቸው ምክንያት አደጋው ሊደርስ መቻሉን የስፔን የግረሰናይ ድርጅትን ዋቢ በማድረግ ሮይተርስ ዘግቧል። ፕሮአክቲቭ ኦፐን አርምስ (Proactive Open Arms) የተሰኘው ...
Read More »በሶማሌ ክልል በድርቁ ሳቢያ ከ40ሺ በላይ የቁም እንስሳት መሞታቸው ታወቀ
ኢሳት (መጋቢት 15 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በመባባስ ላይ ባለው የድርቅ አደጋ በአንድ ዞን ውስጥ ብቻ እስከአሁን ድረስ ከ40ሺ በላይ የቁም እንስሳት መሞታቸውንና ድርቁ ለሰዎች ህይወት ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ። በክልሉ የሚገኘው የቆራሄ ዞን ካለፈው ሃምሌ ወር ጀምሮ ለድርቅ ተጋልጦ የሚገኝ ሲሆን፣ በዞኑ በእስካሁኑ ቆይታ ከ40ሺ በላይ የቁም እንስሳት መሞታቸው የዞኑ አስተዳደር ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን አስታውቀዋል። ድርቁ በዞኑ እያደረሰ ...
Read More »በአዲስ አበባ የነዳጅ ማደያዎችን ለማቃጠል ተንቀሳቅሰዋል የተባሉ የሽብር ክስ እንደተመሰረተባቸው ተገለጸ
ኢሳት (መጋቢት 15 ፥ 2009) በአዲስ ከተማ በሚገኙ ከሰባት በላይ የነዳጅ ማደያዎችን ለማቃጠል ተንቀሳቅሰዋል የተባሉ ዘጠኝ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው የሽብርተኛ ክስ እንደተመሰረተባቸው ጠቅላይ አቃቤ ህግ አርብ ገለጸ። ድርጊቱን ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ ነበር የተባሉ ተጠርጣሪዎች በውጭ ከሚገኝ የሽብር ድርጅት በተለያዩ ማህበራዊ መገናኛዎች ተልዕኮ ሲቀበሉ ነበር ሲል ከሳሽ አቃቤ ህግ በክሱ ማመልከቱን የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ይሁንና ጠቅላይ አቃቤ ህግ ተጠርጣሪዎቹ ...
Read More »የአውሮፓ ህብረት ባለስልጣናት በኢትዮጵያ የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ በቂ ትኩረትን አልሰጡም ሲል ሂውማን ራይትስ ገለጸ
ኢሳት (መጋቢት 15 ፥ 2009) በቅርቡ በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደረጉ የአውሮፓ ህብረት ባለስልጣናት በሃገሪቱ በመፈጸም ላይ ባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በቂ ትኩረትን አልሰጡም ሲል ሂውማን ራይትስ ዎች ለህብረቱ የቅሬታ ደብዳቤን አቀረበ። በኢትዮጵያና በአውሮፓ ህብረት ባለ ትብብርና ግንኙነት ዙሪያ ለመምከር በአውሮፓ ኮሚሽን ምክትል ፕሬዚደንት ፊዴሪካ ሞገሪኒ የተመራ የልዑካን ቡድን በአዲስ አበባ ሰሞኑን ጉብኝትን ማድረጉ ይታወሳል። ይሁንና የልዑክ ቡድኑ በኢትዮጵያ በነበረው ቆይታ በሃገሪቱ ...
Read More »በጋይንት የአርበኛ ግንቦት ሰባት ታጋዮች በብዓዴን ጽ/ቤት ላይ ጥቃት ሰነዘሩ
ኢሳት (መጋቢት 14 ፥ 2009) በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር በጋይንት ከተማ የአርበኛ ግንቦት ሰባት ታጋዮች በብዓዴን ጽ/ቤት ላይ ጥቃት መሰንዘራቸው ተሰማ። በከተማዋ የአስተዳደር እና ጸጥታ መረጃ ሃላፊ መኖሪያ ቤት የቦንብ ጥቃት ተፈጽሞበታል። በወገራ ወረዳ እና ሌሎች አካባቢዎች በተሰነዘረው ጥቃት ደግሞ የህወሃት/ኢህአዴግ ወታደሮች ተገድለዋል። ጥቃቱ የተሰነዘረው በመከላከያና በጸረ-ሽምቅ ሚሊሺያዎችና መደበኛ የፖሊስ አባላት ላይ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል። የአርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ...
Read More »የድርቅ አደጋ ተባብሶ ሊቀጥል እንደሚችል ተመድ አስታወቀ
ኢሳት (መጋቢት 14 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ዳግም ተከስቶ ያለው የድርቅ አደጋ ከተያዘው ወር ጀምሮ እስከ መስከረም ወር ድረስ እየተባባሰ ሊሄድ እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ። የድርቁ አደጋ በተለይ በኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል በሚገኙት የዋርዴር እና የኮራህ ዞኖች የከፋ ጉዳት እያደረሰ በመሆኑ የምግብ እጥረቱ ወደ ረሃብ ደረጃ ለመሸጋጋር አንድ ደረጃ ብቻ እንደቀረው ድርጅቱ ይፋ አድጓል። ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ መገኘት ያለበት ድጋፍ በወቅቱ ...
Read More »አርበኞች ግንቦት7 ጥቃት መፈጸሙን አስታወቀ
መጋቢት ፲፬ (አሥራ አራት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ግንባሩ ለኢሳት በላከው መረጃ መጋቢት 13 ቀን 2009 ዓም የግንባሩ ታጋዮች ወደ ጋይንት ከተማ በመግባት ከምሽቱ 2 ሰአት ተኩል ላይ በብአዴን ጽ/ቤት እና ሹመት በተባለው አስተዳደር እና ጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ መኖሪያ ቤት ላይ ቦንብ በመወርወር ጉዳት ማድረሳቸውንና ማሽቱም በተኩስ ሲናወጥ ማደሩን ገልጿል። ሹመት የተባለው የደህንነት አባል ከዚህ በፊት በተደረገው ህዝባዊ አመጽ ...
Read More »በሃረር በከፍተኛ የውሃ ችግር ተከስቷል። ከ1 ቢሊዮን 500 ሚሊዮን ያላነሰ ገንዘብ የወጣባቸው ፕሮጀክቶች ተቋርጠዋል።
መጋቢት ፲፬ (አሥራ አራት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከአፍሪካ ልማት ባንክ በተገኘ የ747 ሚሊዮን 175 ሺ ብር ብድር የተሰራው የሃሳሊሶ የውሃ ፐሮጀክት ለ30 አመታት ለ350 ሺ ህዝብ ንጹህ የመጠጥ ውሃ እንደሚያቀርብ፣ በ2004 ዓም ሲመረቅ የመንግስት ባለስልጣናት ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተው የነበረ ቢሆንም፣ ፕሮጀክቱ ውሃው ሸሽቷል በሚል ምክንያት ተመርቆ 2 አመታት እንኳ በአግባቡ ሳያገለግል የተዘጋ ሲሆን፣ በአሁኑ ሰአት ሃረር በከፍተኛ ...
Read More »