ኢሳት (መጋቢት 18 ፥ 2009) በልማት ሰበብ የዋልድባ ገዳም አይፈርስ በሚል ሲቃወሙና ድርጊቱን በመገናኛ ብዙሃን ያጋለጡት የዋልድባው መነኩሴ አባ ገብረየሱስ በመንግስት ሃይሎች ታፍነው መወሰዳቸው ተነገረ። የዋልድባው መነኩሴ የመንግስት ስራ በማጋለጣቸው ለረጅም አመታት ከኖሩበት ገዳም እንዲወጡ ተደርጉ ከአምስት አመታት በላይ መቆሚያና መቀመጫ አጥተው ከገዳም ገዳም ሲዞሩ ቆየተዋል አሁን ደግሞ ባለፈው ጥር 2009 አም ሱባዔ ከያዙበት ጎንደር ከሚገኝ አንድ ገዳም በመንግስት ሃይሎች ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የግል ባንኮች የውጭ ምንዛሪ አያያዛቸውን የሚያሳይ መረጃ እንዲያቀርቡ ታዘዙ
ኢሳት (መጋቢት 18 ፥ 2009) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በሃገሪቱ ያሉ ሁሉም የግል ባንኮች ካለፈው አመት ሃምሌ ወር ጀምሮ የውጭ ምንዛሪ አሰጣጣቸውን የሚያሳይ መረጃ እንዲያቀርቡ አዘዘ። ሃገሪቱ ያጋጠማትን የውጭ ምንዛሪ ክምችት ተከትሎ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ባንኮች የሚያደርጉትን የውጭ ምንዛሪ አሰጣት እና አያያዝ በተመለከተ ሪፖርት እንዲያቀርቡ አዲስ መመሪያ ማውጣቱ ይታወሳል። ይህንኑ መመሪያ በማድረግ ብሄራዊ ባንክ ሁሉም የግል ባንኮች ከሃምሌ ወር ጀምሮ ያካሄዱትን ...
Read More »በምስራቅ አፍሪካ የተከሰተው የድርቅ አደጋ ወደ 700ሺ ህጻናትን ህይወት ሊያሳጣ እንደሚችል ተገለጸ
ኢሳት (መጋቢት 18 ፥ 2009) ኢትዮጵያን ጨምሮ በሶስት የምስራቅ አፍሪካ ሃገራት እየተባባሰ ባለው የድርቅ አደጋ ወደ 700ሺ የሚጠጉ ህጻናት ህይወታቸውን ሊያጡ እንደሚችል ወርልድ ቪዥን የተሰኘ የእርዳታ ድርጅት ሰኞ አሳሰበ። በደቡብ ሱዳንና ሶማሊያ የድርቁ አደጋ ወደ ረሃብ በመለወጡ ምክንያት ሰዎች በመሞት ላይ መሆናቸውን የገለጸው የሰብዓዊ ተቋሙ በኢትዮጵያና ኬንያ ድርቁ እየከፋ መምጣቱን በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኢትዮጵያ የሶማሌ ...
Read More »በደቡብ ሱዳን ስድስት የሰብዓዊ ዕርዳታ ሰራተኞች መገደላቸው ስጋት እንዳሳደረበት ተመድ ገለጸ
ኢሳት (መጋቢት 18 ፥ 2009) በደቡብ ሱዳን ስድስት የሰብዓዊ ዕርዳታ ሰራተኞች መገደላቸው ስጋት እንዳሳደረበት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰኞ አስታወቀ። የእርዳታ ሰራተኞች የያዘ ተሽከርካሪ ከመዲናይቱ ጁባ ምስራቅ የሃገሪቱ ክፍል ወደ ምትገኘው የፒቦር ከተማ በማቅናት ላይ እንዳሉ የደፈጣ ጥቃት እንደተፈጸመባቸው በደቡብ ሱዳን የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ ተወካይ የሆኑት ኡጊን አውሶ ለመገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል። በደቡብ ሱዳን ከረሃብ ጋር በተገናኘ ሰዎች መሞት እንደጀመሩ ...
Read More »የዩኒቨርስቲ መምህራን የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ አገሪቱን የማይመጥን በመሆኑ መቀየር እንዳለበት ገለጹ
መጋቢት ፲፰ (አሥራ ስምንት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከወራት በፊት የህወሃት ኢህአዴግ አገዛዝ በጀመረው የጥልቅ ተሃድሶ ስብሰባ ላይ መመህራን የያዙት አቋም ካስደነገጠው በሁዋላ፣ ድጋሜ ጥልቅ ተሃድሶ እንዲካሄድ ባሳሰበው መሰረት በቅርቡ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች መምህራን ለብቻ ስራ አቁመው ውይይት ሲያካሂዱ ቢሰነብቱም፣ መምህራን ግን ቀደም ብሎ ያሳዩትን ጠንካራ አቋም አሁንም አሳይተዋል። በጎንደር፣ ደሴ፣ ደብረማርቆስ፣ ደብረታቦርና በሌሎችም ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ በተካሄደው ስብሰባ መምህራን የህወሃት/ኢህአዴግ ...
Read More »የቆሼ አካባቢ ነዋሪዎች በአፋጣኝ ከቦታቸው እንዲነሱ ታዘዙ
መጋቢት ፲፰ (አሥራ ስምንት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቅርቡ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ቆሸ ወይም ረጲ እየተባለ በሚጠራው የአዲስ አበባ የቆሻሻ ማከማቻ አካባቢ የነበሩ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ማለቃቸውን ተከትሎ ፣ የመስተዳድሩ ባለስልጣናት በአካባቢው የሚኖሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በአፋጣኝ አካባቢውን እንዲለቁ አስጠንቅቀዋል። ነዋሪዎች እንደገለጹት የመጨረሻው የመልቀቂያ ቀን ዛሬ ነው። ምንም አይነት የሚገቡበት ቤት ሳይኖር ልቀቁ መባላቸው ድንጋጤ የፈጠረባቸው ነዋሪዎች፣ በሀዘን ላይ ...
Read More »በኢትዮጵያ ከ9.2 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለውሃ እጥረት ተጋላጭ ሆነዋል ሲል ዩኔሴፍ አታወቀ
መጋቢት ፲፰ (አሥራ ስምንት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በህንድ ውቂያኖስ ባህር ሙቀት ምክንያት በተከሰተው የምስራቅ አፍሪካ አገራት ድርቅ ምክንያት በተለይ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ከ9.2 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለውሃ ጥም ተጋላጭ መሆናቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የህጻናት አድን ድርጅት ፣ ዩኒሴፍ /UNICEF/ በሪፖርቱ አስታወቀ። ድርቁ በሶማሊያ፣ደቡብ ክልል እና ኦሮሚያ በከፋ ሁኔታ ተባባሶ ቀጥሏል። የበልግ ዝናብ ባልጣለባቸው በሶማሊያ፣ ደቡብ ክልል፣ በትግራይ፣ አፋር ...
Read More »በባህርዳር መንጃ ፈቃድ የሌለው የመንግስት ባለሥልጣን ጠጥቶ በማሽከርከር ሰው ገጭቶ ገደለ
መጋቢት ፲፰ (አሥራ ስምንት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ትናንት እሁድ ምሽት ላይ አንድ የመንግስት ባለሥልጣን ያለመንጃ ፈቃድ በስካር በማሽከርከር ጋሻው የተባለ የከተማውን ወጣት ገጭቶ መግደሉን የኢሳት ወኪል ከስፍራው ያደረሰን መረጃ ያመለክታል። የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አመራር አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አገኘሁ ተሻገር ገሰሰ ከመጠን በላይ መጠጥ ጠጥተው ኮድ 04 የታርጋ ቁጥር አማ 04055 የሆነ የመንግስት መኪና እያሽከረከሩ ሲሄዱ ...
Read More »ሂውማን ራይትስ ወች የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ዙሪያ ያወጣውን መግለጫ ተቃወመ
መጋቢት ፲፭ (አሥራ አምስት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ታዋቂው የሰብአዊ መብቶች ተከራካሪ ድርጅት የሆነው ሂውማን ራይትስ ወች ፣ ለአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ክፍል ሃላፊ ለሆኑት ፍሬዲሪካ ሞጋሪ በጻፈው ደብዳቤ፣ የህብረቱ ልኡካን ቡድን አባላት ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ ያወጣው መግለጫ እጅዝ አሳዛኝ መሆኑን ገልጿል። ህብረቱ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው አፈና ለአገሪቱ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እንዲሁም ከአውሮፓ ህብረት ጋር በትብብር ...
Read More »ከመከላከያ ሰራዊት የተቀነሱ አባላት በድጋሜ ጥሪ ተደረገላቸው
መጋቢት ፲፭ (አሥራ አምስት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቤንሻንጉል ጉሙዝ በአሶሳ ከተማ በ7 ዓመት ወይም በ10 ዓመት አገልግሎት ከሰራዊቱ በክብር የተሰናበቱ የቀድሞ ወታደሮች ለሰላም ማስከበር ግዳጅና ለብሄራዊ ተጠባባቂ ሃይል እንዲመዘገቡ የሚጠይቁ ማስታወቂያዎች ተለጥፈዋል። እድሜው ከ42 ዓመት በታች የሆነ ወይም የሆነች፣ በተለያዩ አግባብ ከሰራዊቱ የተሰናበተ፣ በ7 ወይም 10 ዓመት አግልግሎት ጨርሶ በክብር የተሰናበተ፣ በጸረ ሰላም ሃይሎች እንቅስቃሴ ያልተሳተፈና ያልወገነ እንዲሁም ...
Read More »