.የኢሳት አማርኛ ዜና

መንግስት በአዲስ አበባ ፈለገ-ዮርዳኖስ ለሚኖሩ ነዋሪዎች ቦታ ሳይሰጣቸው የመኖሪያ ቤቶቻቸው ማፍረስ መጀመሩ ተገለጸ

ኢሳት (መጋቢት 22 ፥ 2009) በአዲስ አበባ ከተማ በወረዳ 11 በተለምዶ ፈለገ-ዮርዳኖች ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች የከተማ አስተዳደሩ አማራጭና ምትክ ቦታ ሳይሰጣቸው ለረጅም ጊዜ የኖሩበትን የመኖሪያ አካባቢ ማፍረስ መጀመሩን አስታወቁ። ሜክሲኮ ተብሎ ከሚጠራ አደባባይ ወደ ቄራ በሚወስደው ዋና መንገድ ዙሪያ የሚገኙ እነዚሁ ነዋሪዎች አካባቢው ለልማት ይፈለጋል ተብለው በሃይል እንዲለቁ በመደረግ ላይ መሆኑን ለሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል። የከተማ አስተዳደሩ ...

Read More »

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዲሱ አስተዳደርና በጋምቤላ የሚገኙ ኢንቨስተሮች ውዝግብ ቀጥሏል

ኢሳት (መጋቢት 22 ፥ 2009) በ5 ቢሊዮን ብር ብክነት የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ ልማት ባንክና አዲሱ አስተዳደር በጋምቤላ ከሚገኙ ኢንቨስተሮች ጋር የጀመሩት ውዝግብ ቀጥሏል። የቀድሞ የባንኩ ፕሬዚደንት አቶ ኢሳያስ ባህረን የተኩት አቶ ጌታሁን ናና በጋምቤላ እርሻ ኢንቨስትመንት ላይ በተሰማሩ የትግራይ ተወላጆች ወቀሳ የቀረበባቸው ሲሆን፣ የኢሳትን ወሬ እየሰማችሁ ተሽመድምዳችኋል በማለት ለደርግና ለግንቦት 7 ኮሎኔሎች ማበደር ፈልጋችሁ ነው ወይ ሲሉ ጠየቁ። ባለፈው ቅዳሜ የኢትዮጵያ ...

Read More »

ከ30 በላይ የሚሆኑ ወታደሮች በመኪና አደጋ አለቁ

መጋቢት ፳፪ (ሃያ ሁለት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት ወታደራዊ ምንጮች እንደገለጹት ከሳምንት በፊት አንድ ኦራል ተሽከርካሪ ከ30 በላይ ወታደሮችን አሳፍሮ ከመተማ ወደ ቋራ ወረዳ በመጓዝ ላይ እያለ ለምለም ተራራ ላይ ሲደርስ በመገልበጡ ሁሉም ወታደሮች አልቀዋል። ምንጮች አሰቃቂ ሲሉ በጠሩት በዚህ አደጋ የአንድም ወታደር ህይወት ሊትርፍ አለመቻሉን ተናግረው፤ በከፍተኛ ሁኔታ የተቃጠሉና አካላቸው የተለያዩ ወታደሮች አስከሬን እየተለቀመ ተወስዷል። አደጋው በምን ...

Read More »

በቡሌ ሆራ ወረዳ 12 ሰዎች ተይዘው ታሰሩ

መጋቢት ፳፪ (ሃያ ሁለት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮምያ ክልል በቡሌሆራ የተነሳውን ህዝባዊ አመጽ ተከትሎ ጥቃት ይደርስብናል በሚል ተሸሽገው የቆዩ 12 ሰዎች ተይዘው መታሰራቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ሰዎቹ የተያዙት ከዚህ በሁዋላ ምንም እንደማይደርስባቸው በአገር ሽማግሌዎች ማረጋገጫ ከተሰጣቸው በሁዋላ ነው። በአሁኑ ሰአት የአካባቢው ህዝብ በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደሚገኝ የገለጹት ምንጮች፣ በርካታ ሰዎች አካባቢውን ጥለው እየሸሹ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ...

Read More »

በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ የፈሰሰበት የሲቪል ሰርቪስ የምዘና ሂደት መከነ

መጋቢት ፳፪ (ሃያ ሁለት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የደኢህዴግ ከፍተኛ ካድሬ በሆኑት አቶ ታገሰ ጫፎ የሚመራው የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር ለመተግበር እየሞከረ ያለው የመሠረታዊ የሥራ ሒደት (BPR) እና የውጤት ተኮር ሥርዓት (Balanced Score Card/BSC) ምዘና መምከኑን ምንጮች ገልጹ። የምዘና ዕቅዱ በሰራተኞች ተቀባይነት አጥቶ ቢከሽፍም፣ የኢህአዴግ አገዛዝ ግን ዕቅዱን ለማስፈጸም በሚል ዛሬም ከፍተኛ ገንዘብ እያፈሰሰ ነው። የሚኒስቴሩ ምንጮች ...

Read More »

የአባይ ግድብ በእንቦጭ አረም ሊጠቃ እንደሚችል ስጋት መኖሩ ተነገረ

መጋቢት ፳፪ (ሃያ ሁለት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ ክልል አቀፍ የእምቦጭ አረም አስወጋጅ ዩኒት አስተባባሪ ሆነው በማገልገል ላይ ያሉት ወ/ሮ በፍታ ጥሩነህ ሰሞኑን ለመንግስት ሚዲያዎች እንደተናገሩት የአረሙ ስጋት በጣም ሠፊ በመሆኑ ተስፋ የተጣለበት ይህ ትልቅ ግድብ በእንቦጭ አረም ሊጠቃ እንደሚችል ስጋቱ ከፍተኛ መሆኑን ለመገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል፡፡ ዩኒት አስተባባሪዋ ስለመጤ አረሙ ሲያስረዱ የውሀን ተፈጥሯዊትነት በማዛባት እንዲደርቅ የሚያደርገው ...

Read More »

አንድ የአሜሪካ የፓርላማ አባል ለኢትዮጵያ መንግስት የሚሰጠው እርዳታ እንዲቋረጥ ጠየቁ

መጋቢት ፳፪ (ሃያ ሁለት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኮሎራዶ 6th ዲስትሪክት ተወካይ የሆኑት ማይክ ኮፍማን ለአገራቸው ምክር ቤት የውጭ እርዳታ አስተባባሪ ክፍል በጻፉት ደብዳቤ የኢህአዴግ መንግስት የሚፈጽመው የሰብአዊ መብት ጥሰት እስኪቆም ድረስ በመጪው አመት ሊሰጥ የታሰበው የእርዳታ ገንዘብ እንዲቋረጥ ጠይቀዋል። “ዛሬ ይህንን ደብዳቤ እንድጽፍ ያደረገኝ እኔን የመረጡኝ አብዛኛዎቹ ኢትዮ-አሜሪካዊያንን ባቀረቡልኝ ጥያቄ መሰረት ነው። “ ያሉት የፓርላማ አባሉ፣ በስልጣን ላይ ...

Read More »

በድንበር አካባቢ ያለው ጸጥታ አለመረጋጋቱን ሚኒስትሩ አስታወቁ

መጋቢት ፳፩ (ሃያ አንድ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለሚቀጥሉት አራት ወራት እንዲራዘም ለተወካዮች ምክርቤት ጥያቄ አቅርበው የተፈቀዳላቸው የወታደራዊ እዙ ( ኮማንድ ፖስት) ዋና ጸሃፊና የመከላከያ ሚኒስትሩ ሲራጅ ፈርጌሳ፣ አዋጁ እንዲራዘም ያስፈለገው ክልሎች በሚዋሰኑባቸው አካባቢዎች ጸረ ሰላም ሃይሎች እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ገልጸዋል። ሚኒስትሩ በአማራ ክልል በትግራይና አማራ ፣ በኦሮምያ እና በሶማሊ እንዲሁም በቤንሻንጉልና በአማራ ድንበሮች አካባቢ ጦርነቶች እየተደረጉ ...

Read More »

ባህርዳር ውስጥ በእግረኞች ማቋረጫ መንገድ ላይ አንድን ወጣት ገጭቶ የገደለው ባለስልጣን ከተለቀቀ በሁዋላ መልሶ ታሰረ

መጋቢት ፳፩ (ሃያ አንድ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሃይለኛ የስካር መንፈስ ውስጥ ሆኖ ሲያሸከረክር የነበረው የአማራ ክልል አመራር አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር አቶ አገኘሁ ተሻገር በእግረኞች ማቋረጫ መንገድ ወይም “ዜብራ ክሮስ” ላይ ጋሻው የተባለውን ወጣት ገጭቶ ከገደለው በሁዋላ፣ በእለቱ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ቢወሰድም በማግስቱ የተለቀቀ ሲሆን፣ ኢሳት ዜናውን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ግን ተመልሶ እንዲታሰር መደረጉን ምንጮች ገልጸዋል። ድርጊቱ የከተማው ህዝብ ...

Read More »

ከውጭ አገራት በተለያዩ መንገዶች የገባ 50 ቢሊዮን ብር ባንክ ውስጥ እንደሚገኝ ተገለጸ

መጋቢት ፳፩ (ሃያ አንድ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የተለያዩ የውጭ አገር መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ለኢትዮጵያውያን ለልማት እያሉ በብሄራዊ ባንክ በኩል ከሚያስተላልፉት ገንዘብ ውስጥ 50 ቢሊዮን ብር ጥቅም ላይ ሳይውል ተቀምጦ እንደሚገኝ የብሄራዊ ባንክ ምንጮቻችን ገልጸዋል። የውጭ አገር ዜጎች ለልማት እያሉ የሚያስገቡት ገንዘብ፣ በድርጅቶቹ ደካማ እቅድ አፈጻጸም ወይም በሌሎች ምክንያቶች ጥቅም ላይ ሳይውል ተከማችቶ እንደሚገኝ የሚገልጹት ምንጮች፣ የባንኩ ሃላፊዎችና ...

Read More »