.የኢሳት አማርኛ ዜና

አሜሪካ በሶሪያ ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ የሚሳይል ጥቃት ሰነዘረች

ኢሳት (መጋቢት 29 ፥ 2009) የሶሪያ መንግስት ከቀናት በፊት በንጹሃን የሃገሪቱ ዜጎች ላይ ፈጽሞታል የተባለውን የኬሚካል የጦር መሳሪያ ዕርምጃ ተከትሎ አሜሪካ በተመረጡ የሃገሪቱ ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ የሚሳይል ጥቃት መውሰዷን ሃሙስ ይፋ አደረገች። የአሜሪካ ወታደራዊ ባለስልጣናት ከምስራቅ የሜዲትራኒያን ባህር ላይ ከወታደራዊ መርከቦች የተወሰደው የሚሳይል ጥቃት በቅርቡ በሰሜናዊ ምዕራብ የሶሪያ ግዛት ጥቃት ለመፈጸም አገልግሎት የሰጠ ወታደራዊ ማዘዣ ጣቢያ ዋነኛ ኢላማ እንደነበር ገልጸዋል። ...

Read More »

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሱዳን ድንበር ዙሪያ ተጨማሪ የጸጥታ ሃይል መሰማራቱ ተነገረ

ኢሳት (መጋቢት 29 ፥ 2009) ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር በምትዋሰነት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የድንበር ዙሪያ ተጨማሪ የጸጥታ ሃይል በማሰማራት ቁጥጥር በማድረግ ላይ መሆኗን የመከላከያ ሰራዊት አርብ አስታወቀ። የቤኒሻንጉል ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ በአካባቢው ወታዳራዊ ርምጃዎችን በመውሰድ ላይ መሆኑን ሲገልጽ መቆየቱም ይታወሳል። ባለፈው ወር መንግስት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሚገኘው የአባይ ግድብ ላይ ጥቃት ለመፈጸም ተንቀሳቅሰዋል የተባሉ 13 ታጣቂዎች ገደልኩ ሲል መግለፁ ይታወሳል። ይህንኑ ...

Read More »

በበለጸጉ አገራት ለኢትዮጵያ ሊሰጥ የነበረው የ100 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ውድቅ ተደረገ

ኢሳት (መጋቢት 29 ፥ 2009) የአለም አቀፍ አረንጓዴ ከባቢ (ግሪን ክላይሜት) በጀት ለኢትዮጵያ ሊሰጥ ባሰበው የ100 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ላይ የበለጸጉ ሃገራት  ያቀረቡትን ተቃውሞ ተከትሎ ለኢትዮጵያ ሊለቀቅ የነበረው የገንዘብ ድጋፍ ውድቅ ተደረገ። ከ20 የሚበልጡ የተቋሙ የቦርድ አባላት ሃሙስ ለሁለተኛ ቀን በቀጠሉት ውይይት ለኢትዮጵያ ሊሰጥ በነበረው የ100 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ላይ ሰፊ ልዩነት ማንጸባረቃቸውን ሮይተርስ ከደቡብ ኮሪያ ዘግቧል። አሜሪካ፣ ካናዳ፣ ስዊዘርላድ፣ ...

Read More »

በሽብርተኛ ወንጀል ክስ ነጻ የተሰናበቱት ሁለት ጦማሪያን በአዲስ ወንጀል ክስ እንዲከሰሱ የተላለፈው ውሳኔ ውድቅ እንዲደረግ ሲፒጄ ጠየቀ

ኢሳት (መጋቢት 29 ፥ 2009) ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሽብርተኛ ወንጀል ክስ ነጻ የተሰናበቱት ሁለት ጦማሪያን በአዲስ ወንጀል ክስ እንዲከሰሱ ያስተላለፈው ውሳኔ ውድቅ እንዲደረግ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ጠየቁ። የታችኛው ፍርድ ቤት ባለፈው አመት የሽብርተኛ ወንጀል ክስ የተመሰረተባቸው ጦማሪያን መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ እንዲሰናበቱ ውሳኔ ሰጥቶ እንደነበር ይታወሳል። ይሁንና ከሳሽ አቃቤ ህግ ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ፍርድ በመቃወም ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ...

Read More »

ታዋቂው አርበኛ ሌተናል ጄኔራል ጃጋማ ኬሎ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

ኢሳት (መጋቢት 29 ፥ 2009) ኢትዮጵያን ከጠላት የጣሊያን ወራሪ ጦር የተከላከሉት ታዋቂው አርበኛ ሌተናል ጄኔራል ጃጋማ ኬሎ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ። ከ15 አመት ለጋ እድሚያቸው ጀምሮ ጫካ በመግባት የጣሊያንን ጦር ያርበደበዱት ጀግናው ሌተናል ጄኔራል ጀጋማ ኬሎ በአጼ ሃይለ-ስላሴ ዘመን የጦር አዛዥ እስከመሆን ደርሰዋል። በኦሮሚያ ክልል በሸዋ ጊንጪ አቅራቢያ በጅባትና ሜጫ አውራጃ በዳንዲ ወረዳ ዩብዶ በሚባል ቦታ የተወለዱት ሌተናል ጄኔራል ጀጋማ ...

Read More »

በኢትዮጵያ ሃሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች ይዘው የሚሰሩ ዜጎች መበራከታቸውን መረጃዎች አመለከቱ ። በአገሪቱ የሚታየው የሃሰተኛ የትምህርት ማስረጃ መበራከት ከፍተኛ ስጋት መፍጠሩን ዜጎች ይናገራሉ።

መጋቢት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሃሰት የትምህርት ማስረጃ ይዘው ከሚሰሩት መካከል ደግሞ መምህራንና የጤና ባለሙያዎች መገኘታቸው በትውልዱ ላይ ከፍተኛ አደጋ መደቀኑን ዜጎች ይናገራሉ። በዲግሪ የተመረቁ መምህራን 8ኛ ክፍል ማስተማር አንችልንም ብለው ወደ አንደኛ ደረጃ እንዲመደቡ የጠየቁ መኖራቸውን የክልሉ ሌላው ባለስልጣን ይናገራሉ ። ህክምና ተምረው ሃኪም ያዘዘውን መድሃኒት በትክክል ለመስጠት የማይችሉ ፋርማሲስቶች መኖራቸውንም ባለስልጣኖች ይገልጻሉ ። በኢትዮጵያ ...

Read More »

በአዲስ አበባ ቤት የማፍረስ ዘመቻው ተባብሶ ቀጥሏል ከ20 ሽህ በላይ ነዋሪዎች ተፈናቀሉ

መጋቢት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አካባቢ ያሉ ነባር ባለይዞታ ነዋሪዎች ካለምንም ቅድመ ማስጠንቀቂያ ከመኖሪያ ቀያቸው ማፈናቀሉ ተባብሶ ቀጥሏል። ለዘመናት ተወልደው ያደጉበት መኖሪያ ቤት፣ የሸቀጥ ማከፋፈያ ሱቆች፣ ስጋ ቤቶች፣ ፋርማሲዎች፣ ግሮሰሪዎች፣ የተለያዩ አነስተኛ እና የጅምላ ማከፋፈያ የንግድ ድርጅቶች በዘመቻ እንዲፈርሱ እየተደረገ ነው። በቀበሌ ቤቶች ውስጥ ነዋሪ ለሆኑት ለ6 ወራት የቤት ኪራይ የሚሆን ...

Read More »

በአርባምንጭ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ለዘመናት ከኖሩበት ቦታ እየተፈናቀሉ መሆኑን ገልጹ

መጋቢት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት፣ ሃንዳዋሎ በሚባለው አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ከ1500 በላይ አባዎራዎች ከተማዋ የዛሬ 50 ዓመት ስትቆረቆር ጀምሮ ከነበሩበት ቀየ ለቃችሁ ውጡ በመባላቸው፣ ለከፍተኛ ችግር ተጋልጠዋል። ነዋሪዎች እንደሚሉት ከነባር ይዞታቸው ሲነሱ አስፈላጊው ቤትና ቦታ አልተሰጣቸውም። ለምን ብለው የጠየቁ ከ10 ያላነሱ ሰዎች በእስር ላይ እንደሚገኙ ነዋሪዎች ገልጸዋል። ዜጎች እየተፈናቀሉ መሬቱ ለካቢኔ አባላቱ እየተሰጠ ...

Read More »

በደንቢያ የቻይና የመንገድ ስራ ድርጅት እንደገና ወደ ካምፑ እንዲገባ ከተደረገ በሁዋላ በደረሰ ሁለተኛ ጥቃት ተመልሶ ወጣ

መጋቢት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደንቢያ ወረዳ ጎርጎራ አካባቢ በሚገኘው የቻይና ካምፕ ላይ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱት ሃይሎች ያደረሱትን ጥቃት ተከትሎ ኩባንያው ሰራተኞችንና መኪኖችን ወደ ቆላ ድባ ካስወጣ በሁዋላ፣ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የመከላከያ ሰራዊት ወደ አካባቢው በመጓዝ አካባቢውን ማረጋጋቱን በመግለጽ፣ ኩባንያው ወደ ቦታው እንዲመለስ ቢያደርግም፣ ዛሬ አርብ በደረሰ ተጨማሪ የቦንብ ጥቃት ተሽከርካሪዎች እንደገና አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል። ከፍተኛ የመከላከያ ...

Read More »

የጃፓን መንግስት በሶማሊያ ክልል ለድርቅ ለተጠቁ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች የሚውል የ2 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ለዩኒሴፍ ለገሰ።

መጋቢት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የገንዘብ እርዳታው በዩኒሴፍ አማካኝነት ለውሃ፣ ለጤና፣ ለንጽህና አገልግሎቶች፣ ለተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት እና ለአጣዳፊ የጠቅማጥ በሽታ መድሃኒት መግዣ እንደሚውልም ተገልጿል። ድርቁን ተከትሎ ተላላፊ በሽታዎች በመዛመታቸው በአካባቢው ያሉ ነዋሪዎችን ሕይወት ለመታደግ ለንጽህና አገልግሎት 1.5 ሚሊዮን ዶላር ተመድቧል።የኢትዮጵያው ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ባቀረቡት አፋጣኝ የእርዳታ ጥያቄ ...

Read More »