.የኢሳት አማርኛ ዜና

በጋምቤላ ክልል የታፈኑትን ህጻናት ለማስመለስ በቂ ትኩረት አልተሰጠም ተባለ

ኢሳት (ሚያዚያ 2 ፥ 2009) ከጋምቤላ ክልል በቅርቡ ታፍነው የተወሰዱት ህጻናትን ለማስመለስ መንግስት በቂ ትኩረት አልሰጠም ሲሉ በጋምቤላ ክልል ስላለው የሰብዓዊ መብት መከበር ዙሪያ የሚሰሩ አካላት ገለጹ። የኢትዮጵያ መንግስት ታፍነው የተወሰዱ ከ40 በላይ ህጻናትን ለማስለቀቅ ቃል ቢገባም፣ እስካሁን ድረስ የተመለሱ አለመኖራቸውንና ጥቃቱ በነዋሪው ዘንድ ስጋትን ማሳደሩን የደቡብ ሱዳን የዜና አገልግሎት ነዋሪዎችንና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አካላትን ዋቢ በማድረግ ሰኞ ዘግቧል። ባለፈው ...

Read More »

የማላዊ ፖሊስ በህገወጥ መንገድ ገብተዋል ያላቸው 56 ኢትዮጵያውያንን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ

ኢሳት (ሚያዚያ 2 ፥ 2009) የማላዊ ፖሊስ ወደ ሃገሪቱ በህገወጥ መንገድ ገብተዋል የተባሉ 56 ኢትዮጵያውያን በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ሰኞ ገለጸ። በየወሩ በሃገሪቱ ለእስር የሚዳረጉ ስደተኞች ኢትዮጵያውያን ቁጥር እየጨመረ በመሄድ ላይ መሆኑንና ድርጊቱ አሳሳቢ መሆኑን የማላዊ ኢሚግሬሽን ለመገናኛ ብዙሃን አስታውቋል። 56ቱ ኢትዮጵያውያን ካሮንጋ ተብሎ ከሚጠራ አካባቢ መዳረሻቸው ወደ አልታወቀ ቦታ በጭነት ተሽከርካሪ በመጓዝ ላይ እንዳሉ በጸጥታ ሃይሎች መያዛቸውን ማላዊ 24 የተሰኘ ...

Read More »

በግብፅ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት 44 ሲሞቱ ከ 100 በላይ መቁሰላቸው ተገለጸ

ኢሳት (ሚያዚያ 2 ፥ 2009) በግብፅ በሁለት የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያኖች ላይ ዕሁድ በተፈጸመው የቦንብ ጥቃት የሟቾች ቁጥር 44 መድረሱንና ከ100 በላይ ሰዎች ደግሞ ጉዳት እንደደረሰባቸው የሃገሪቱ ባለስልጣናት አስታወቁ። የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ በቤተ-ክርስቲያኖቹ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት በማውገዝ የግብፅ ፕሬዚደንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ጉዳዩን በአግባቡ እንደሚይዙት ገልጸዋል። ከተለያዩ የአለም አቀፍ ሃገራትና ተቋማት እየቀረበ ያለውን ውግዘት ተከትሎ ግብፅ የሶስት ወር የአስቸኳይ ጊዜ እንዲታወጅ ...

Read More »

በቆላድባ አንድ ወታደር የ14 ዓመት ልጃገረድ መድፈሩን ተከትሎ ህዝቡ ተቃውሞውን አሰማ

ሚያዝያ ፩ (አንድ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአካባቢው የሚታየውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለመቆጣጠር ከተላኩት ወታደሮች መካከል አንዱ የሆነው ለጊዜው ስሙ ያልታወቀው ወታደር፣ እሁድ ሚያዚያ 1 ፣ ከጓደኛው ጋር በመሆን አንዲት የ14 ዓመት ታዳጊ በጉልበት ወስዶ ደፍሯታል። ታዳጊዋ ደም እየፈሰሳት ለአካባቢው ሰዎች መናገሩዋን ተከትሎ ህዝቡ ተቃውሞውን እያሰማ ወደ ፖሊስ ጣቢያ አምርቷል። ሰቀልት ክፍል ወይም ቀበሌ ዜሮ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ነዋሪ የሆነቸው ...

Read More »

በምስራቅ ጉጂ በረሃብና በበሽታ ህጻናት እያለቁ ነው ተባለ

ሚያዝያ ፩ (አንድ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት በኦሮምያ ክልል በምስራቅ ጉጂ ዞን ቆላ ተብለው በሚጠሩ አካባቢዎች ከፍተኛ ድርቅ መግባቱንና ይህንን ተከትሎም ወረርሽኝ በመከሰቱ የበርካታ ህጻናት ህይወት እያለፈ ነው ። በተለይ በዞኑ በሚገኙ 6 ወረዳዎች የሚላስ የሚቀመስ የለም የሚሉት ነዋሪዎች፣ ህጻናት በተቅማጥና ትውከት እያለቁ ነው ይላሉ። በሃራቀሎ፣ ሉባን፣ ሰባ ቦሩ እና ደዋ ቀበሌ የሚኖሩ ነዋሪዎች የሚደርስላቸው ...

Read More »

በደቡብ ክልል የአርበኞች ግንቦት7 አባላት ወረቀቶችን በትነው ማደራቸውን አስታወቁ

ሚያዝያ ፩ (አንድ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የህዝባዊ እምቢተኝነት አስተባባሪዎች ለኢሳት በላኩት መረጃ በሐዋሳ ፣ በወላይታ ከተማ ፣ በአርባምንጭ ፣ በኮንሶ ፣ በጅንካ እንዲሁም በአቶ ኃ/ማሪያም ደሰላኝ የትውልድ አከባቢ በሆነው አረካ አካባቢ “ ከአሁን በሁዋላ በወያኔ መታለል ይቁም፣ የታጋይ አርበኞቻችን ደም በከንቱ እንደፈሰሰ አይቀርም፣ በወያኔ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የህዝቡን መብት ለማፈን እና አርበኞችን ትግል ለማደናቀፍ ያለመ ቢሆንም የአርበኞች ...

Read More »

መሬታቸውን የተነጠቁ አርሶአደሮች ካሳ ሳይከፈላቸው ለአመታት መቆየታቸውን ገለጹ

ሚያዝያ ፩ (አንድ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከአዋሽ ሐራ ገበያ – መቀሌ እየተገነባ ካለው የባቡር መስመር ጋር ተያይዞ አርሶአደሮች ያላ አንዳች የካሳ ክፍያ ለዓመታት መቆየታቸውን ተናገሩ፡፡ በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳን አቋርጦ ወደ መቀሌ ከተማ እየተገነባ ያለው የባቡር መስመር በርካታ አርሶአደሮችን ለችግር ዳርጐ መቆየቱን የቀበሌ ነዋሪዎች ለመንግስት ጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡ በባቡር ሃዲዱ ግንባታ ምክንያት መሬታቸው የተወሰደባቸው አርሶ አደሮች ለሁለት ...

Read More »

የአዲስ አበባ መስተዳደር ተቃውሞ የተነሳበትን የመንገድ አዋጅ ተግባራዊ እንደሚያደርገው ገለጸ

ሚያዝያ ፩ (አንድ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ታናሽ ወንድም አቶ ገነቱ ደሳለኝ የሚመራው የአዲስአበባ ከተማ የመንገድ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አወዛጋቢውን የመንገድ ትራፊክ መቆጣጠሪያ ደንብ ቁጥር 395/2009 ተግባራዊ ለማድረግ መዘጋጀቱን ይፋ አደረገ፡፡ በአዲሱ ደንብ በሚያዝ ሪከርድ መሠረት በተደጋጋሚ አጥፍተዋል የተባሉ አሽከርካሪዎች ፈቃዳቸው ታግዶ የተሀድሶ ስልጠና እንዲወስዱ ይገደዳሉ፡፡ ኤጀንሲው ተግባራዊ እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቱን በአዲስዘመን ጋዜጣ መጋቢት 28 ቀን ...

Read More »

ወደ ማላዊ የገቡ 56 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ሚያዝያ ፩ (አንድ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሕገወጥ መንገድ ወደ ማላዊ ገብተዋል የተባሉ 56 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በማላዊ የድንበር ፖሊሶች መያዛቸውን የአገሪቱ ባለስልጣናት አስታወቁ። ለጊዜው መነሻቸው ከየት እንደሆነ ያልታወቀው ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች በመኪና ተጭነው በሕገወጥ መንገድ ወደ ካሮንጋ ግዛት ሲያቀኑ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታውቋል። ሃምሳ ስድስቱም ኢትዮዮጵያዊያን ስደተኞች በሙሉ ወንዶች መሆናቸውን እና የጭነት መኪናው አሽከርካሪ መኪናውን በመተው ከአካባቢው መሰወረኑን ፓሊስ ...

Read More »

አሜሪካ የሶሪያው መሪ ባሽር አልአሳድ ከስልጣን የሚወገዱበት አማራጭ ይፋ አደረገች

ኢሳት (መጋቢት 29 ፥ 2009) አሜሪካ የሶሪያው ፕሬዚደንት ባሽር አልአሳድ ከስልጣን የሚወገዱበት ሁኔታ መታየት ወዳለበት አማራጭ መድረሱን ይፋ አድረገች። በሶሪያ መንግስት ከቀናት  በፊት በንጹሃን ሰዎች ላይ ጥቅም ላይ ውሏል በተባለ የኬሚካል ጦር መሳሪያ ግድያ ተቃውሞዋን ስታሰማ የሰነበተችው አሜሪካ ፕሬዚደንት አሳድ ስልጣናቸው በሃይል የሚያከትምበት ጊዜ መቃረቡን ለመጀመሪያ ጊዜ ፍንጭ መስጠቷን መገናኛ ብዙሃን በመዘገብ ላይ ናቸው። ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ ወታደራዊ ባለስልጣናት በበኩላቸው ...

Read More »