ኢሳት (ሚያዚያ 3 ፥ 2009) የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ያለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር በተገናኘ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ለእስር መዳረጉና እስራቱ አሁንም ድረስ መቀጠሉ ስጋት አሳድሮብኛል ሲል ማክሰኞ ገለጸ። ሃሳቡን የመግለጽ መብት እንዲከበር ህብረቱ አሳስቧል። ህብረቱ በሃገሪቱ ባሉ የሰብዓዊ መብት አያያዞችና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ ለመምከር በአውሮፓ ህብረት ልዩ የሰብዓዊ መብቶች መልዕክተኛ በሆኑ ስታርቮስ ላምብሪኒደስ የተመራ የልዑካን ቡድን ባለፈው ሳምንት ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ባለፈው አመት በተለያዩ ሃገራት ከ3 ሺ በላይ ሰዎች የሞት ቅጣት ተፈጸመባቸው
ኢሳት (ሚያዚያ 3 ፥ 2009) ባለፈው የፈረንጆች አመት 2016 ቻይናን ጨምሮ የተለያዩ ሃገራት ከ 3ሺ በሚበልጡ ላይ የሞት ቅጣት መፈጸማቸውን የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ማክስኞ ይፋ አደረገ። ቻይና በአለማችን ካሉ ሃገራት የሞት ቅጣቱን በብዛት በመፈጸም በግንባር ቀደምትነት የተቀመጠች ሲሆን፣ ኢራን፣ ሳውዲ አረቢያ፣ ኢራቅ እና ፓኪስታን ከሁለት እስከ አምስተኛ ደረጃ ይዘዋል። ባለፈው የፈረንጆች አመት ከ3ሺ በላይ ሰዎች ላይ ተፈጻሚ ከሆነው ...
Read More »አርበኞች ግንቦት7 ተጨማሪ ጥቃቶችን መፈጸሙን አስታወቀ
ሚያዝያ ፪ (ሁለት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን መፈጸሙን የሚገልጸው አርበኞች ግንቦት7 ፣ መጋቢት 28 ቀን 2009 ዓም ከሱዳን ተነስቶ ወደ ጎንደር በማቅናት ላይ የነበረ የሱዳን ታርጋ ያለው መኪና ላይ በፈጸመው ጥቃት የመኪናውን ከፊል አካል ማቃጠሉን ገልጿል። ጥቃቱ የተፈጸመው የመከላከያ ሰራዊት ካምፕ ካለበት አካባቢ ነው። እንዲሁም ሚያዚያ 1 ቀን 2009 ዓም አምባጊዮርጊስ አካባቢ የአገዛዙ ሰላይ ...
Read More »በይርጋለም ከተማ በርካታ የመንግስት ሰራተኞች ታሰሩ
ሚያዝያ ፪ (ሁለት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ክልል ይርጋለም ከተማ ከ15 በላይ የፋይናንስና የማዘጋጃ ሰራተኞች በሙስና በሚል ተሰብስበው ታስረዋል። እርምጃው የተወሰደው በቅርቡ በክልሉ የተካሄደውን ግምገማ ተከትሎ ነው። የድርጅተ ሰራተኞች እንደገለጹት በሙስና የተዘፈቁት ዋናዎቹ አመራሮች ሆነው እያለ እነሱን ወደ ሌሎች ቦታዎች በማዛወር፣ ከጉዳዩ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸውን ተራ ሰራተኞች ይዘው አስረዋል። እስሩን ተከትሎ በሰራተኞች ዘንድ አለመረጋጋት መፈጠሩን ሰራተኞች ተናግረዋል። ...
Read More »ኦብነግ ከሶማሊ ልዩ ሃይልና ከመከላከያ ጋር መዋጋቱ ተዘገበ
ሚያዝያ ፪ (ሁለት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኦጋዴን ኒውስ ኤጀንሲ እንደዘገበው ከሁለት ቀናት በፊት በመከላከያ ሰራዊት በሚደገፈው የሶማሊ ልዩ ሃይልና በኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅት መካከል በደጋሃቡር አውራጃ፣ በብርቆት ወረዳ ልዩ ስሙ ሊዲለይ በሚባል ስፍራ ላይ በተደረገ ውጊያ 3 አዛዦችን ጨምሮ 17 ወታደሮች መገደላቸውን የአይን እማኞችን ጠቅሶ ዘግቧል። 21 ቁስለኛ ወታደሮች ደግሞ በአየር ወደ ጅግጅጋ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የአይን እማኞች እንደገለጹለት ...
Read More »የአረካ ገበያ ተቃጠለ
ሚያዝያ ፪ (ሁለት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት የአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ የትውልድ ስፍራ በሆነችው አረካ ከተማ የሚገኘው የገባያ ማእከል በመቃጠሉ ከፍተኛ ንብረት ወድሟል። አብዛኞቹ ሱቆች በአቶ ሃይለማርያም የቅርብ ዘመዶችና በደኢህዴን አባላት የተያዙ እንደነበሩ የሚገልጹት ምንጮች፣ የእሳቱ መንስኤም የአስተዳደር በደልንና ሙስናን ከመወጋት ጋር ሊያያዝ እንደሚችል ግምታቸውን ይገልጻሉ። የዚህ ከተማ ነዋሪዎች ከፍተኛ የአስተዳደር በደል የሚፈጸምባቸው ሲሆን፣ በተለይ ወጣቶች ...
Read More »በአማራ ክልል ካሉ ትምህርት ቤቶች 87 ከመቶ የሚደርሱት ከደረጃ በታች ናቸው ተባለ
ሚያዝያ ፪ (ሁለት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በክልሉ ያለው የመማር ማስተማር ሂደት ከጊዜ ወደ ጊዜ ተቆርቋሪ እያጣ ነው ተብሎአል። መሠረታዊ የግብዓት እጥረት መኖር ፣ የመምህራን ድጋፍ ማነስ፣ የወላጆች ክትትልና ድጋፍ አለመኖር፣የተማሪዎች የመማር ፍላጎትን ከመቀነስ አልፎ 87 በመቶ ትምህርት ቤቶች ከደረጃ በታች እንዲሆኑ ምክንያቶች መሆናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ መገምገሙን ገለጸ፡፡ ብዙዎቹ ተማሪዎች በአቅራቢያቸው ትምህርት ቤት የለም፡፡ በዚህ የተነሳ ተማሪዎች ተነሳሽነት ...
Read More »የጀግናው ሌተናል ጄኔራል ጃጋማ ኬሎ የቀብር ስነስርዓት በቅድስተ-ስላሴ ቤ/ክርስቲያን ተፈጸመ
ኢሳት (ሚያዚያ 2 ፥ 2009) የሌተናል ጄነራል ጃጋማ ኬሎ የቀብር ስነስርዓት ትናንት ዕሁድ በቅድስተ-ስላሴ ቤ/ክርስቲያን በርካታ ሰዎች በተገኙበት ተፈጸመ። በጣሊያን የወረራ ጦር ጊዜ ባደረጓቸው ትግሎች በርካታ ድሎች መጎናጸፋቸው የሚነገርላቸው ሌተናል ጀኔራል ጃጋማ ኬሎ፣ ባደረባቸው ህመም ሳቢያ የህክምና ክትትል ሲደረግላቸው ቆይቶ በ96 አመታቸው ባለፈው አርብ ከዚህ አለም በሞት መለየታቸው ይታወሳል። እሁድ በተከናወነው የቀብር ስነ-ስርዓት የቤተሰብ አባላት እንዲሁም የመንግስት ባለስልጣናትና የኢትዮጵያ አርበኞች ...
Read More »በወህኒ ቤት ሰቆቃ እየፈጸሙ ያሉት የትግራይ ተወላጆች መሆናቸው ተገለጸ
ኢሳት (ሚያዚያ 2 ፥ 2009) የኢትዮጵያ የፍትህ ስርዓት ከ90 በመቶ በላይ በትግራይ ተወላጆች ቁጥጥር ስር መውደቁን፣ በወህኒ ቤቱ ሰቆቃ የሚፈጽሙት በተመሳሳይ የትግራይ ተወላጆች መሆናቸውን አቶ ሃብታሙ አያሌው ገለጸ። የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የነበረውና ከአንድ አመት በላይ በወህኒ ቤት ያሳለፈው አቶ ሃብታሙ አያሌው ይህንኑ የተናገረው በዋሽንግተን ዲሲ አቅራቢያ በተዘጋጀ መድረክ ላይ መሆኑንም መረዳት ተችሏል። በቨርጂኒያ አርሊንግተን ከተማ ሼራተን ሆቴል ዕሁድ ...
Read More »በሰሜን ተራሮች የሚኖሩ በርካታ ነዋሪዎችን ከፓርኩ ለማስወጣት የተጀመረው ዘመቻ ውዝግብ ቀሰቀሰ
ኢሳት (ሚያዚያ 2 ፥ 2009) በህወሃት/ኢህአዴግ የሚመራው መንግስት በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ውስጥ የሚገኙ በርካታ ነዋሪዎችን ከፓርኩ ለማስወጣት የጀመረው ዘመቻ ከካሳ ክፍያ ጋር በተያያዘ አለመግባባት ቀሰቀሰ። በዚሁ ብሄራዊ ፓርክ የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ አርሶ አደሮችና ነዋሪዎች በፓርኩ ውስጥ ለሚገኙ ብርቅዬ የዱር አራዊት ቁጥር መመናመን ምክንያት ሆነዋል በሚል አገዛዝ ከሶስት አመት በፊት ነዋሪዎችን የማስወጣት ሂደት መጀመሩ ይታወሳል። በመጀመሪያ ዙር ከተካሄደው በዚሁ ዘመቻ ...
Read More »