ኢሳት (ሚያዚያ 4 ፥ 2009) በቦሌ ክፍለ ከተማ በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩና የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ አመራር አቶ ዳንዔል ሽበሺ የእስር ቤቱ አመራሮች ፍርድ ቤት ሊያቀርቧቸውም ሆነ ሊለቋቸው እንደማይችሉ እንደገለጹላቸው ከእስር ቤት ባስተላለፉት መልዕክት አስታወቁ። ላለፉት አምስት ወራት ፍርድ ቤት ሳይቀቡና ክስ ሳይመሰረትባቸው በእስር ላይ የሚገኙት ሁለቱ ተጠርጣሪዎች የእስር ቤቱ ሃላፊዎች ጉዳያችሁ ከአቅማችን በላይ ነው ሲሉ ሰሞኑን ምላሽ እንደሰጧቸው ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በሶማሌ ክልል በበርካታ ወረዳዎች የተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ ለሰዎች ሞት ምክንያት መሆኑን ተመድ አስታወቀ
ኢሳት (ሚያዚያ 4 ፥ 2009) በኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል በመባባስ ላይ ያለውን የድርቅ አደጋ ተከትሎ በበርካታ ወረዳዎች የተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ ለሰዎች ሞት ምክንያት መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ረቡዕ ይፋ አደረገ። ድርጅቱ በበሽታው ምን ያህል ሰዎች እስካሁን ድረስ ህይወታቸው እንዳለፈ ከመግለጽ ቢቆጠብም፣ ወረርሽኙ በትንሹ በ40 ወረዳዎች ጉዳት እያደረሰ መሆኑን በድርቁ ዙሪያ ባወጣው ሪፖርት አመልክቷል። ከተለያዩ ክልሎች የተውጣጡ ከ300 በላይ የጤና ባለሙያዎች በክልሉ ...
Read More »ወደ አውሮፓ የሚጓዙ ስደተኞች በህገ-ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች በባርነት በመሸጥ ላይ መሆናቸውን የአለም አቀፉ ስደተኞች ድርጅት (IOM) አስታወቀ
ኢሳት (ሚያዚያ 4 ፥ 2009) በሊቢያ በኩል ወደ አውሮፓ ለመሰደድ ሙከራን የሚያደርጉ የተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት ስደተኞች በህገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች በባርነት በመሸጥ ላይ መሆናቸውን የአለአም አቀፉ ስደተኞች ድርጅት (IOM) አስታወቀ። ስደተኞቹን በቁጥጥር ስር የሚያውሉ ታጣቂዎች እና ህገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች ስደተኞቹን በቁጥጥር ስር ካዋሉ በኋላ በአደባባይና በመኪና ማቆሚያ ስፍራዎች በጨረታ እንደሚሸጧቸው የስደተኛ ድርጅቱ ከድርጊቱ ያመለጡ ሰዎችን ዋቢ በማድረግ ሪፖርት ማስራጨቱን ቢቢሲ ዘግቧል። ...
Read More »በአዲስ ዘመን የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ተጨማሪ ወታደሮች ወደ ከተማው ገቡ
ሚያዝያ ፫ (ሦስት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቅርቡ በሊቦ ከምከም ወረዳ አዲስ ዘመን ከተማ ላይ በወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ፣ ተጨማሪ ጥቃት ሊኖር ይችላል በሚል ቁጥራቸው ሁለት መቶ የሚሆኑ ወታደሮች ትናንት ምሽት ወደ ከተማዋ በመግባት በድሮው ፖሊስ ጣቢያና ፍርድ ቤት አካባቢዎች መስፈራቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ገልጸዋል። ምሽቱን የተኩስ ድምጽ ይሰማ እንደነበር ነዋሪዎች ቢገልጹም፣ የተኩሱን መንስኤ ግን ለማወቅ አለመቻላቸውን ...
Read More »“የመንግስት ጣልቃ ገብነት ሊቆም ይገባል” ሲል የዋድላ ወረዳ ቤ/ክህነት አስታወቀ
ሚያዝያ ፫ (ሦስት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ቤተ ክርስቲያን የራሱዋ የሆነ መተዳዳሪያ ደንብ ያላት ቢሆንም፣ አገዛዙ በየጊዜው ጣልቃ እየገባ መመሪያዋን ተግባራዊ ማድረግ አለመቻሉዋን የወረዳው ቤ/ክህነት ሃላፊዎች አቤቱታ አሰምተዋል። አመራሮቹ ፣ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ጠዋት ወደ ቤ/ክርስቲያን እየመጡ “ ስብሰባ አለ፣ መልዕክት አለ፣ ይህን ክፍያ ክፈሉ” እያሉ መእመናንን እያስቸገሩ ነው ያሉ ሲሆን ፣ አሰራሩ ቤ/ክርስቲያኑዋ የሰበሰበቻቸውን ምዕመን ለመበተን የተደረገ አሰራር ...
Read More »በኦሮምያ የመንግስት ሰራተኞች ለኦህዴድ በግዳጅ የሚከፍሉት ክፍያ እንዲቆም ጠየቁ
ሚያዝያ ፫ (ሦስት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮምያ አንዳንድ ወረዳዎች የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ለኦህዴድ ማጠናከሪያ በሚል ለአመታት ያለፈቃዳቸው ከደሞዛቸው የሚቆረጠው ገንዘብ እንዲቆም ጥያቄ አቅርበዋል። በክልሉ ውስጥ የሚኖር የየትኛውም ብሄር ተወላጅ ከደሞዙ 5 በመቶ ለኦህዴድ በግዴታ ይከፍላል። በጅማ ዞን በሚገኙት ሰቃ፣ ደዶ እና ጎማ ወረዳዎች የሚሰሩ የመንግስት ሰራተኞች ከእንግዲህ ክፍያ አንከፍልም በማለት ተቃውሞ ያሰሙ ሲሆን፣ ከእንግዲህ ደሞዛችን በግድ የሚቆረጥ ከሆነ ...
Read More »ኢትዮጵያን ጨምሮ በሰሜናዊ ምስራቅ አፍሪካ 11 ሚሊዮን ሕዝብ ለርሃብ ተጋላጭ መሆኑን ተመድ አስታወቀ
ሚያዝያ ፫ (ሦስት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜናዊ ምስራቅ አፍሪካ አገራት በተከሰተ ድርቅ 11 ሚሊዮን የኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ሶማሊያ ዜጎች አፋጣኝ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ሲሉ በተባበበሩት መንስግታት ድርጅት የሕጻናት አድን ድርጅት ዩኒሴፍ እና የዓለም የምግብ ድርጅት በጋራ አስታውቀዋል። ድርቁ በደቡብ ሱዳን ከ100 ሺ በላይ ነዋሪዎችን ሲያጠቃ፣ ከ20 ሺ በላይ የሚሆኑት ሕጻናት ናቸው። በደቡብ ሱዳን ከድርቁ በተጨማሪ የእርስበርስ ጦርነቱ በነዋሪዎቹ ...
Read More »የብሪታኒያ ኩባንያ በአፋር ክልል ወርቅ ለማውጣት የደረሰው ስምምነት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት ተጓትቶብኛል አለ
ኢሳት (ሚያዚያ 3 ፥ 2009) መቀመጫውን በብሪታኒያ ያደረገ አንድ አለም አቀፍ የማዕድን ኩባንያ በአፋር ክልል ወርቅን ለማውጣት የደረሰው ስምምነት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት መጓተቱን ማክሰኞ ገለጸ። ከፊ ሚነራል የተባለው ይኸው ኩባንያ፣ ባለፈው አመት የወርቅ ቁፋሮን በክልሉ የቱሉ ካፒ ፕሮጄክት ለመጀመር ከመንግስት ጋር ስምምነት የደረሰ ሲሆን፣ ፕሮጄክቱ ከ100 ሚሊዮን ዶላር በላይ ኢንቨስትመንት እንደሚፈልግ ከኩባንያው የተገኘ መረጃ ያመለክታል። ይሁንና ኩባንያው ስራውን ለመጀመር ...
Read More »በወላይታ ዞን አረካ የሚገኝ አንድ የገበያ ቦታ መቃጠሉ ተነገረ
ኢሳት (ሚያዚያ 3 ፥ 2009) በጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ የትውልድ ቦታ አረካ የሚገኝ አንድ የገበያ ቦታ መቃጠሉ ተነገረ። የቃጠሎው ምክንያት በውል ባይታወቅም በህዝቡ ውስጥ ከንግድና ከአስተዳደር በደል የመነጨ ሊሆን እንደሚችል የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ። ነዋሪዎቹ እንደሚሉት የገበያ ቦታው እና በዚያው የነበሩ ሱቆች በደህዴን ካድሬዎች እና በአቶ ሃይለማሪያም ደጋፊዎች የተያዙ ነበሩ። በዚሁ ሳቢያ ወጣቶች የስራ ዕድል ባላገኙበት ሁኔታ ጥቂቶች ተጠቃሚ መሆናቸው በህዝቡ ...
Read More »የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት የሚፈልጉ የሃገር ውስጥ ኩባንያዎች LC ለመክፈት 100 % ገንዘብ በባንክ እንዲያስቀምጡ ተጠየቁ
ኢሳት (ሚያዚያ 3 ፥ 2009) የብሄራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት የሚፈልጉ የሃገር ውስጥ ኩባንያዎች ሌተር ኦፍ ክሬዲት (LC) ለመክፈት ያስቀመጠውን የ30 በመቶ መጠን ወደ 100 ፐርሰንት ከፍ አደረገ። ባንኩ የወሰደውን ይህንኑ ዕርምጃ ተከትሎ አስመጪ ነጋዴዎች በግል ባንክ ያስቀመጡትን ገንዘብ በማውጣት ወደ ብሄራዊ ባንክ ለማስገባት መገደዳቸውን አዲስ ፎርቹን ጋዜጣ ዘግቧል። የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች በበኩላቸው ዕርምጃው የግል ባንኮች የገንዘብ እጥረት እንዲያጋጥማቸው በማድረግ ...
Read More »