ኢሳት (ሚያዚያ 5 ፥ 2009) በኢትዮጵያ በመባባስ ላይ ባለው አዲስ የድርቅ አደጋ አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ የሚፈልጉ ወረዳዎች ቁጥር ወደ 364 ማሻቀቡ ተገለጠ። ሲጠበቅ የነበረው የበልግ ዝናብ በሚፈለገው መጠን ባለመጣሉ ምክንያት 5.6 ሚሊዮን የሆነው የተረጂዎች ቁጥር በቀጣዮቹ ጥቂት ወራቶች እንደሚጨምር የአደጋ መከላከልና አስተዳደር ኮሚሽን ማስታወቁን የቱርኩ ዜና አገልግሎት አናዱሉ ዘግቧል። ከአንድ ወር በፊት በድርቁ የተጎዱ ወረዳዎች ቁጥር ወደ 240 አካባቢ እንደነበር ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ግጭት ዕልባት አለመሰጠቱ የአፍሪካ ቀንድን መረጋጋት አደጋ ውስጥ ገብቷል ሲል አውሮፓ ህብረት አስታወቀ
ኢሳት (ሚያዚያ 5 ፥ 2009) ኢትዮጵያና ኤርትራ በመካከላቸው ያለውን የድንበር ግጭት ዕልባት አለመስጠታቸው የአፍሪካ ቀንድን መረጋጋት አደጋ ውስጥ ከቶታል ሲል የአውሮፓ ህብረት ሃሙስ ስጋቱን ገለጠ። የኢትዮጵያና ኤርትራ የድንበር ኮሚሽን የሁለቱ ሃገራት የድንበር ይገባኛል ጥያቄን እልባት ለመስጠት ውሳኔ ያስተላለፈበትን 15ኛ አመት አስመልክቶ መግለጫን ያወጣው ህብረቱ፣ ጉዳዩን የአህጉራዊ ትብብርና ልማትን ለማጠናከር በተያዘው እንቅስቃሴ ላይም አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን አመልክቷል። በሁለቱ ሃገራት መካከል የተቋቋመው ...
Read More »የኢትዮጵያ ገበሬዎች በአል-ፋሻጋ አካባቢ ዘልቀው ገብተዋል ሲል የሱዳን መከላከያ ሚኒስትር ቅሬታ አቀረበ
ኢሳት (ሚያዚያ 5 ፥ 2009) የኢትዮጵያ ገበሬዎች አጨቃጫቂ በሆነው የአል-ፋሻጋ አካባቢ ወደ ሱዳን ግዛት ዘልቀው ገብተዋል ሲል የሱዳን መከላከያ ሚኒስቴር ሃሙስ ቅሬታን አቀረበ። በዚሁ የድንበር ዙሪያ የሚኖሩ የሁለቱ ሃገራት ዜጎች በዓል-ፋሸጋ ስር የሚገኝ ሰፊ የእርሻ ቦታ ላይ ለአመታት የቆየ የይገባኛል ጥያቄ ሲያቀርቡ መቆየታቸው ይታወሳል። በድንበሩ አዋሳኝ አካባቢ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ገበሬዎች የሱዳን የፀጥታ ሃይሎች በተደጋጋሚ ወደ ይዞታቸው እየመጡ መሬቱ ለሱዳን የተሰጠ ...
Read More »ኢህአዴግ “በአገሪቱ የተነሳው ህዝባዊ አመጽ በጠባብነትና ትምክተኝነት የተነሳ ነው” ሲል ራሱን ሸንግሎ ተሃድሶውን ማጠናቀቁን አስታወቀ
ሚያዝያ ፬ (አራት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮምያና አማራ እንዲሁም በአንዳንድ የደቡብ ክልሎች የታዩትን ህዝባዊ ተቃውሞዎች ተከትሎ አገሪቱን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስአዋጅ አውጥቶ በወታደራዊ ሃይል እየገዛት ያለው ኢህአዴግ፣ ፖለቲካዊ መፍትሄ ብሎ ያስቀመጠውን ጥልቅ ትሃድሶ ሲያጠናቅቅ፣ ለተቃውሞው መነሻ በውጭ የሚገኙ የመገናኛ ብዙሃንን ተጠያቂ አድርጓል። ኢህአዴግ ጥልቅ ተሃድሶው በድል ተጠናቋል ቢልም ህዝቡ ግን ተሃድሶው የተባለውን ከቁም ነገር አልቆጠረውም። የኢህአዴግ ምክር ቤት ...
Read More »ታጋዮች በበለሳ ወረዳ በሚገኝ ወታደራዊ ካምፕ ላይ ጥቃት ፈጽሙ
ሚያዝያ ፬ (አራት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአርበኞች ግንቦት7 ታጋዮች ለኢሳት በላኩት መግለጫ በበለሳ ወረዳ ባጃየ ንኡስ ወረዳ ሚያዚያ 4 ቀን 2009 ዓም ሌሊት ላይ በወታደራዊ ካምፕ ላይ ጥቃት ፈጽመዋል። ታጋዮቹ ለግማሽ ሰአት ያክል አካባቢውን መቆጣጠራቸውንና ያለምንም ጉዳት ወደ አካባቢያቸው መመለሳቸውን ገልጸዋል። ጥቃቱን በተመለከተ በገዢው ፓርቲ በኩል የተሰጠ መልስ የለም። ይህ በእንዲህ እንዳለ በአዲስ ዘመን በመስተዳድሩ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት ...
Read More »ገዢው ፓርቲ ያልተመዘገቡ ናቸው ያላቸውን ከ300 ሺ በላይ የስልክ ሲም ካርዶችን ከአገልግሎት ውጭ አደርጋለሁ አለ
ሚያዝያ ፬ (አራት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በስልክ የሚታገዙ ወንጀሎችን፣ ማጭበርበርን እንዲሁም ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ደንበኞች የሚገለገሉባቸውን ሲም ካርዶች ባለማስመዝገባቸው 349 ሺ 261 ሲምካርዶች ከአገልግሎት ውጭ ለማድረግ ዝግጅት ማጠናቀቁን የኢትዮጵያ ቴሌኮምኒኬሽን መስሪያ ቤት አስታውቋል። የመገናኛ እና ኢንፎርሜሽን ሚንስትር ዶ/ር ደብረ ፅዩን ገ/ሚካኤል ፣ ሲም ካርዶቹ ከአገልግሎት ውጭ ከመሆናቸው በፊት ሰነድ የሌላቸውን የሲም ካርድ ባለቤቶች ለመመዝገብ ፣ በአሁኑ ስዓት ማንነታቸው በማይታወቁ ...
Read More »በመርሃቤቴና በመንዝ ወረዳዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጋዮች ከፍተኛ ጉዳት እንዳደረሱ የዞኑ ፖሊስ አመነ
ሚያዝያ ፬ (አራት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአማራ ክልል በሰሜን ሽዋ ዞን በመርሃ ቤቴና በመንዝ ቀያ ወረዳዎች በመዘዋወር ለነጻነታቸው ሲዋጉ የተሰውት ሁለቱ የነጻነት ታጋዮች ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸውን የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ አምኗል። በነበሩ ከመሰለውና ጭንቅል አስጨናቂ የተባሉት የነጻነት ታጋዮች ፣ በገዢው ፓርቲ አመራሮች ላይ እርምጃ በመውሰድ ለገዢው ፓርቲ ከፍተኛ ራስ ምታት ሆነው ነበር። ታጋዮቹ በደቡብ ወሎ ዞን ወረኢሉ ...
Read More »የአውሮፓ ህብረት ካውንስል ጽ/ቤት የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ኮሚሽኑ ውሳኔ ተግባራዊ መሆን አለበት ሲል አሳሰበ
ሚያዝያ ፬ (አራት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከ15 ዓመት በፊት በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል የተፈጠረውን የመሬት ይገባኛል ጥያቄ ተከትሎ የተነሳውን ጦርነት ለማስቆም የተፈረመውን የአልጀርስ ስምምነት ተከትሎ፣ የተቋቋመው የድንበር ኮሚሽን (EEBC) የሰጠው ውሳኔ ተግባራዊ ሊሆን ይገባል ብሎአል። የአፍሪካ ቀንድን ችግር በዘላቂነት ይፈታል የተባለውን የድንበር ኮሚሽን ውሳኔ ተግባራዊ አለመደረጉ እንደሚያሳስባቸው የገለጹት የህብረቱ ካውንስል ጻሃፊ ወ/ሮ ፌዴሪካ ሞጎሪኒ ፣ ችግሩ ከቀጠናው ባለፈም ...
Read More »የመንግስት ንግድ ባንኮች ከውጭ አገር ገንዘብ ለሚያስልኩ በእጣ እስከመኖሪያ ቤት ድረስ የሚደርስ ሽልማት ማቅረባቸው በምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ቅሬታ አስነሳ
ኢሳት (ሚያዚያ 4 ፥ 2009) የመንግስት ንግድ ባንኮች በውጭ ሃገር ያሉ ዜጎች ወደ ሃገር ውስጥ ገንዘብን ለሚያስልኩ እስከ መኖሪያ ቤት የደረሰ የዕድል እጣን ለመወዳደሪያነት ማቅረባቸው በግል ባንኮችና በምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ዘንድ ቅሬታን አስነሳል። ንግድ ባንኮች ሰሞኑን የሚከበረውን የፋሲካ በዓልና ሌሎች ጉዳዮችን በማስመልከት ከውጭ ገንዘብ የሚያስልኩ ተወዳዳሪዎችን እስከመኖሪያ ቤት የሚደርስ ሽልማት ለመስጠት ሰፊ የማስታወቂያ ዘመቻ እያካሄዱ መሆኑ ታውቋል። ይሁንና መንግስታዊ ባንኮች ...
Read More »ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ ውጭ ለአለም አቀፍ ገበያ እንዳይቀርብ ተጥሎ የነበረው የቡና ሽያጭ እገዳ ተነሳ
ኢሳት (ሚያዚያ 4 ፥ 2009) የኢትዮጵያ የቡና ውጭ ንግድ ገቢ ማሽቆልቆሉን ተከትሎ መንግስት ቡና ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ ውጭ ለአለም አቀፍ ገበያ እንዳይቀርብ ጥሎት የነበረን እገዳ አነሳ። የምርት ገበያ ከስምንት አመት በፊት መቋቋሙን ምክንያት በማድረግ ሁሉም ቡና ላኪ ድርጅቶች ለውጭ ገበያ የሚያቀርቡትን ቡና በኢትዮጵያ ምርት ገበያ በኩል ብቻ እንዲያደርጉ ተደርጎ መቆየቱ ይታወሳል። ይሁንና ለስምንት አመት ሲሰራበት የቆየውን ይህንኑ መመሪያ መንግስት ከተያዘው ...
Read More »