ኢሳት (ሚያዚያ 9 ፥ 2009) በቢሾፍቱ ከተማ የአህያ ስጋን እያዘጋጀ ለውጭ ሃገር ገበያ የሚያቀርበው ቄራ ከህዝቡ በተነሳ ተቃውሞና ጫና መዘጋቱ ተገለጸ። በኦሮሚያ ክልል የቢሾፍቱ አስተዳደርን ጠቅሶ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ፅ/ቤት የአህያ እርድ ቄራው መዘጋቱን አረጋግጧል። የአህያ ስጋ ቄራው በመንግስት ፈቃድ ተሰጥቶት በቀን 2መቶ አህዮችን በማረድ ስጋውን እና ቆዳውን ወደ ቻይና መላክ ጀመሮ ነበር። ጉዳዩ ከተሰማ በኋላ የአህያ ቄራው ከህዝቡ ሃይማኖት እና ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ኢትዮጵያ በሰው ሃብት ልማት ከሰሃራ በታች ከሚገኙ አገራት ዝቅተኛ አፈጻጸም ላይ እንደምትገኝ ተመድ ገለጸ
ኢሳት (ሚያዚያ 6 ፥ 2009) ኢትዮጵያ በሰው ሃብት ልማት ከሰሃራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ ሃገራት መካከል ዝቅተኛ አፈጻጸም ላይ እንደምትገኝ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም (UNDP) ይፋ አደረገ። የ2016 አም አመታዊ ሪፖርቱን ይፋ ያደረገው ድርጅቱ ኢትዮጵያ ከ189 ሃገራት በሰው ሃብት ልማቱ በ174ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧንና የያዘችው ደረጃም በአህጉሪቱ ዝቅተኛው መሆኑን አስታውቋል። የተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት ጥናቱን ካካሄደባቸው 189 ሃገራት መካከል 41ዱ ...
Read More »የስቅለት በዓል በመላ ኢትዮጵያ በደማቅ ሃይማኖታዊ ስነስርዓት ተከበረ
ኢሳት (ሚያዚያ 6 ፥ 2009) የዘንድሮው የእየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በአዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በመላ ሃገሪቱ በደማቅ ሃይማኖታዊ ስነስርዓት ተከበረ። ይኸው የስቅለት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን፣ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን እና በወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት በስግደት እንዲሁም በልዩ የጾም ስነ-ስርዓት ተከብሮ መዋሉን ከሃገር ቤት ከተገኘ መረጃ ለመረዳት ተችሏል። አርብ መከበር የጀመረው የስቅለት በዓል ምሽቱን በተለያዩ ቤተክርስቲያኖች በሚካሄዱ መንፈሳዊ ዝግጅቶች የሚቀጥል ሲሆን፣ ...
Read More »በሶማሌ ክልል የተከሰተው የኮሌራ በሽታ ወረርሽን 50 ሰዎችን መግደሉ ተገለጸ
ኢሳት (ሚያዚያ 6 ፥ 2009) በኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል ኦጋዴን አካባቢ በምትገኘው የብርቆድ ከተማ በመዛመት ላይ ባለ የኮሌራ በሽታ ወረርሽን 50 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ። በአካባቢው በመንግስት የተጣለው የንግድና የሰዎች ዝውውር እገዳ የበሽታው ስርጭት ወደ ከፋ ደረጅ እንዲሸጋገር ማድረጉን መቀመጫውን በቤልጅየም ብራሰልስ ከተማ ያደረገውና Unrepresented Nations and People’s Organization (UNDO) የተሰኘው አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድርጅት የተለያዩ አካላትን ዋቢ በማድረግ አስታውቋል። በዚሁ ...
Read More »ቤት ለመግዛት አስፈላጊውን ክፍያ የፈጸሙ በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ቤታቸውን ለመረከብ ሲሄዱ ወደሆቴልነት ተቀይሮ እንደጠበቃቸው ተገለጸ
ኢሳት (ሚያዚያ 6 ፥ 2009) በውጭ ሃገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የመኖሪያ ቤት ለመግዛት ክፍያን ከፈጸሙ በኋላ ቤቱን ለመረከብ ሲሄዱ ሆቴል ሆኖ እንደጠበቃቸው ተዘገበ። ድርጊቱን የፈጸመው ኬርያ የተባለው ሪል ስቴት መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ቢያመራም የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ይበልጥ አስገራሚ መሆኑ ተመክቷል። የማምኮ ወረቀት ፋብሪካ ሃላፊ በሆኑ በሼክ መሃመድ አላሙዲ አጎት በአቶ መርዱፍ የተቋቋመው ኬሪያ ሪል ስቴት፣ ከሰባት አመት ...
Read More »የስቅለት በዓል በመላው ክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ተከብሮ ዋለ
ሚያዝያ ፭ (አምስት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ እና በመላው ዓለም የሚኖሩ የክርስትና እምነት ተከታዮች የስቀለት በዓልን አክብረው ውለዋል። በኢትዮጵያ የእምነቱ ተከታዮች እለቱን በስግደት እና ጸሎት አሳልፈዋል። በዚህ አመት የአመት በአል ገበያ የዋጋ ጭማሪ እያሳየ መሆኑን ወኪላችን ገልጿል። በተለይም በእርድ በሬ፣ ዶሮና ሽንኩርት ላይ የዋጋ ጭማሪ ታይቷል።በደቡብ እና ኦሮምያ ክልሎች አንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ ዘይትና ስኳር ሙሉ በሙሉ ከገበያ ...
Read More »በአዲስ አበባ ፍተሻው ተጠናክሮ ቀጥሎአል
ሚያዝያ ፭ (አምስት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወኪላችን እንደዘገበው ካለፈው ረቡዕ ጀምሮ በአዲስ አበባ የተለያዩ ቦታዎች በተለይም በፒያሳ አካባቢ የታጠቁ የፌደራል ፖሊስ አባላት በብዛት የሚታዩ ሲሆን ፣ ምሽት ላይ ነዋሪዎች ወደ ቤታቸው በሚያመሩበት ጊዜ ፍተሻ ያደርጋሉ። አንዳንድ የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ነዋሪዎችን በሚፈትሹበት ወቅት ‘ አይዟችሁ አትፍሩ ታዘን ነው የምንፈትሸው እንደሚሉ” ወኪላችን ገልጿል። የገዢው ፐርቲ የደህንነት አባላት በአሉን ...
Read More »በኢትዮጵያ በረሃብ የተጠቁ ዜጎች ቁጥር ሊያሻቅብ ይችላል ሲል ተመድ አስጠነቀቀ
ሚያዝያ ፭ (አምስት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ቀውስ ተቋም ከመጋቢት እስከ ግንቦት ወራት ድረስ የሚጥለው የዝናብ መጠን ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከ20 እስከ 30 ቀናት ዘግይቶ እንደሚጀምር እና የዝናቡም መጠን በአማካኝ ከነበረው አነስተኛ ሊሆን እንደሚችል በወርሃዊ ሪፖርቱ ገልጿል። በድርቅ ክፉኛ ተጠቂ በሆኑ አካባቢዎች ደግሞ የዝናብ ስርጭቱ ከ30 እስከ 40 ቀናት ዘግይቶ ይጥላል ...
Read More »የተመድ የልማት ፕሮግራም ኢትዮጵያን በመጨረሻዎች ደሃ አገራት ደረጃ አስቀመጠ
ሚያዝያ ፭ (አምስት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በእየለቱ ብዙ የሚባልለት የኢትዮጵያ ባለሁለት አሃዝ ኢኮኖሚ እድገት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራምን እጅግም አልመሰጠው። ዘንድሮም ድርጅቱ አገሪቱን በአለም እጅግ ድሃ ከሚባሉ አገራት ተራ መድቧታል። ምንም እንኳ ባለፉት 25 ዓመታት መሻሻሎች ቢኖሩም ፣ ኢትዮጵያ በብዙ መስፈርቶች አሁንም እጅግ ዝቅተኛ ሰብአዊ ልማት ( Low Human Development Category) ካላቸው አገራት ተርታ ትመደባለች ያለው ...
Read More »በይርጋለም የታሰሩት የመንግስት ሰራተኞች በእስር እንዲቆዩ ውሳኔ ተላለፈባቸው
ሚያዝያ ፭ (አምስት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ክልል ይርጋለም ከተማ በአንድ ጊዜ ከ10 በላይ የመንግስት ሰራተኞች ተይዘው የታሰሩ ሲሆን፣ የሲዳማ ዞን ከፍተኛው ፍርድ ቤት ሰራተኞች ያቀረቡትን የዋስ መብት ጥያቄ ባለመቀበል ለተጨማሪ 10 ቀናት በእስር ቤት እንዲቆዩ ወስኗል። በግለሰቦቹ ላይ የቀረበው ክስ የበሉትን አበል አላወራረዱም የሚል መሆኑን ችሎቱን የተከታተሉ ሰዎች ለኢሳት ገልጸዋል። ምንጮች እንደሚሉት ግን በጅምላ የተደረገው እስር ...
Read More »