.የኢሳት አማርኛ ዜና

የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በሸንኮራ አገዳ ምርት እጥረት ወደ ስራ አለመግባቱ ተገለጸ

ኢሳት (ሚያዚያ 18 ፥ 2009) ከሁለት አመት በፊት ስኳርን ለውጭ ገበያ ያቀርባል ተብሎ የነበረውና ግንባታው በቅርቡ የተጠናቀቀው የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በሸንኮራ አገዳ ምርት እጥረት ወደ ስራ አለመግባቱ ተገለጸ። ይኸው ከህንድ መንግስት በተገኘ ብድርና ከሃገር ውስጥ የመንግስት በጀት የተቋቋመው የስኳር ፋብሪካ ኣጋጥሞታል የተባለው የምርት አቅርቦት እስከቀጣዩ አራት አመት ድረስ የሚዘልቅ መሆኑም ታውቋል። የፋብሪካውን ሁኔታ አስመልክቶ ሪፖርትን ለፓርላማ ያቀረበው የመንግስት የልማት ድርጅቶች ...

Read More »

በአርባምንጭ ገዢው ፓርቲ የሚያሰማው የቦንድ ግዢ ቅስቀሳ ሰሚ አላገኘም

ሚያዝያ ፲፰ (አሥራ ስምንት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የከተማዋ ነዋሪዎች እንደገለጹት የአባይ ግድብ ዋንጫ ወደ ከተማው ይመጣል በሚል ህዝቡ ዋንጫውን እንዲቀበል የገንዘብ መዋጮና የቦንድ ግዢ እንዲፈጽም ቢጠየቅም፣ ከህዝቡ የተገኘው ምላሽ ዝቅተኛ ነው። ነጋዴዎች እስከ 20 ሺ ብር፣ በአነስተኛ ስራ የሚተዳደሩት ደግሞ እስከ 150 ብር እንዲከፍሉ ሲጠየቁ፣ ነዋሪዎች ግን መክፈል ካለብን በፈቃዳችን እንከፍላለን እንጅ ልንገደድ አይገባም በማለት ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል። ...

Read More »

ጄ/ል ገብሬ አዲሱን የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ነቀፉ

ሚያዝያ ፲፰ (አሥራ ስምንት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ራሳቸውን የምስራቅ አፍሪካ አገራት ሕብረት -ኢጋድ የሶማሊያ ተወካይ አድርገው የሚቆጥሩት የቀድሞው በኢትዮጵያ የሶማሊያ ጦር አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ገብሬ ዲላ ፣ አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት መሀመድ አብዱላሂ ፎርማጆ በሶማሊያ ለተሰማሩት የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ጦር አባላት አክብሮት አላሳዩም በሚል ነቅፈዋቸዋል። ብ/ ጄኔራል ገብሬ በኦፊሻል የትዊተር ገጻቸው ላይ በጻፉት አጭር መልእክት ላይ እንዳሉት ”ፕሬዚዳንቱ ...

Read More »

የሰብአዊ ኮሚሽን ሪፖርትን ተከትሎ አመጽ ይነሳል በሚል በኦሮምያ የፌደራል ፖሊሶች ተሰማሩ

ሚያዝያ ፲፰ (አሥራ ስምንት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቀደሞው ምርጫ ቦርድ ም/ል ሰብሳቢ በህወሃቱ አባል ዶ/ር አዲሱ ገ/እግዚአብሄር የሚመራው ራሱን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ብሎ የሚጠራው ድርጀት ከፍተኛ አመጽ ተነስቶባቸው በነበሩ የኦሮምያ ከተሞች 495 ሲቪል ዜጎች መገደላቸውን ይፋ ካደረገ በሁዋላ፣ ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቀሴ በድጋሜ ሊጀመር ይችላል በሚል በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላትን ወደ አካባቢው ልኳል። በደንብ የታጠቁ ወታደሮች የአመጹ ...

Read More »

የሶማሊ ልዩ የሚሊሺያ አባላት የደሞዝ ጭማሪ ጠየቁ። ታጣቂዎቹ ትእዛዝ ለመቀበል ፈቀዳኛ አለመሆናቸውንም አስታውቀዋል

ሚያዝያ ፲፯ (አሥራ ሰባት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቅርቡ ከ200 ያላነሱ የኦሮሞ ተወላጆችን በመግደላቸው እየተወነጀሉ ያሉት በአቶ አብዲ ሙሃመድ ኡመር የሚመሩት የሶማሊ ልዩ ሚሊሺያ አባላት ፣የደረሰባቸውን ጥቃት ተከትሎ፣ የጉዳት ካሳና ደሞዝ ካልተጨመራቸው ማንኛውንም አይነት ትእዛዝ ለመቀበል ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ገልጸዋል። የክልሉ ልዩ ሃይል አባላት ለመዝመት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ወደ አካባቢው በቅርቡ የተጓዙት አዲስ የተሾሙት የደህንነት አባል መከላከያው የልዩ ሃይሉን ቦታ ...

Read More »

በደቡብ ጎንደር ዞን ዜጎች በብዛት እየታሰሩ ነው

ሚያዝያ ፲፯ (አሥራ ሰባት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ምንጮች እንደገለጹት በቅርቡ ወዲህ በተለያዩ ሰበቦች በርካታ ዜጎች እየታፈሱ ወደ እስር ቤት ተወስደዋል። የማሰር ዘመቻው ወደ ካህናቱም ወርዶ በትናንትናው እለት በአንዳቤት ወረዳ በርካታ ካህናት ቤተክርስቲያን ማስተዳደር አልቻላችሁም ተብለው ታስረዋል። የደቡብ ጎንደር ሃገረ ሰብከት ዋና ስራ አስኪያጅ የነበሩት መላከ ሰላም አባ ሃይለየሱስ ቢያድግልኝ መታሰራቸውንም የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። የእርሳቸው መታሰር የአካባቢውን ...

Read More »

አራተኛው የህዝብ ቆጠራ ህዳር ወር ላይ ይካሄዳል ተባለ

ሚያዝያ ፲፯ (አሥራ ሰባት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሕዝብ ቆጠራ ኮምሽን በመጪው ዓመት ህዳር 10 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ አራተኛውን የህዝብና ቤት ቆጠራ እንደሚያካሂድ የኮምሽኑ ምንጮች ገለጹ። የሕዝብና ቤት ቆጠራ በ10 ዓመት አንድ ጊዜ የሚከናወን ሲሆን ኮምሽኑ በ1999/2000 ዓ.ም ያካሄደው ሶስተኛው ቆጠራ የብአዴን/ኢህአዴግ የፓርላማ አባላትን ጭምሮ በርካታ ዜጎችን ያስቆጣ ነበር። ኮምሽኑ ህዳር 25 ቀን 2001 ዓ.ም 3ኛውን የሕዝብና ...

Read More »

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የዓለማቀፉ ፕሬስ ኢንስቲትዩት የ2017 የፕሬስ ጀግኖች ሽልማት አሸናፊ ሆነ።

ሚያዝያ ፲፯ (አሥራ ሰባት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዓለማቀፉ የፕሬስ ኢንስቲትዩት በምህጻረ ቃሉ- አይ ፒ አይ ይፋ እንዳደረገው፤69ኛውን የዓላማችን የፕሬስ ጀግኖች ሽልማት ፣ ፕሬስን ለማፈን የወጣውን የጸረ ሽብርተኝነት ህጉን በመተቸቱ ምክንያት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2011 ጀምሮ በእስር ላይ የሚገኘው ኢትዮጵያዊው ጋዜጠኛና ጦማሪ እስክንድር ነጋ አሸንፏል። አይ ፒ አይ ዛሬ ባወጣው በዚሁ መግለጫ የአፍጋኒስታን ጋዜጠኞች ተከላካይ ኮሚቴ የነጻ ሚዲያ ...

Read More »

በኢትዮጵያ የተፈጠረውን ድርቅ ተከትሎ 16 ሺ ሰዎች በኮሌራ ወረርሽኝ መጠቃታቸው ተዘገበ

ሚያዝያ ፲፯ (አሥራ ሰባት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በምስራቅ ኢትዮጵያ በሚገኘው ዶሎ ዞን በ30 አመት ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ድርቅ ምክያት በተከሰተ የኮሌራ ወረርሽኝ 16 ሺ ሰዎች መያዛቸውንና በየወሩም ከ3 ሺ 500 በላይ ሰዎች ወደ ህክምና ማእከል እንደሚገቡ ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን አስታውቋል። እንደ ድርጅቱ ዘገባ ከሆነ ወረርሽኙን ለመከላከል 1ሺ 200 ባለሞያዎች በ100 ጣቢያዎች አገልግሎት ለመስጠት ቢሞክሩም፣ ባካባቢው የመሰረተ ...

Read More »

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በአምቦ ከተማና አካባቢዋ ውጥረት ማንገሱ ተዘገበ

ኢሳት (ሚያዚያ 17 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ለተጨማሪ ወራቶች ተራዝሞ የሚገኘው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በአምቦ ከተማና አካባቢዋ ውጥረት ማንገሱን ዘ-ኢኮኖሚስት መጽሄት ዘገበ። በሃገሪቱ ወቅታዊ ጸጥታ ዙሪያ ሰኞ ሪፖርትን ይዞ የወጣው አለም አቀፍ መጽሄቱ በከተማዋ የሚገኘው የአምቦ ዩኒቨርስቲን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማት ወታደራዊ ጥበቃ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ አስነብቧል። ባለፈው አመት በአምቦ ከተማና ዙሪያዋ በሚገኙ የገጠር መንደሮች ሲካሄድ ከቆየው ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተገናኘ በርካታ ሰዎች ...

Read More »