ሚያዝያ ፳ ( ሃያ ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ጉባኤ ዋና አዛዥ የሆኑት ዘይድ ራድ አል ሁሴኒ በመጪው ሳምንት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ባደረጉላቸው ግብዣ መሰረት ኢትዮጵያን እንደሚጎበኙ ድርጅቱ አስታውቋል። የእሳቸው ጉብኝት ከመካሄዱ አስቀድሞ በኢትዮጵያ ተከስቶ የነበረውና በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ያለቁበት ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ያቀረበውን ጥያቄ፣ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በሶማሊያ ሰላማዊ ዜጎች ላይ የኬንያ እና የኢትዮጵያ ወታደሮች ከመጠን በላይ ሃይል ተጠቅመው ዜጎችን መግደላቸውን ሪፖርቶች አጋለጡ
ሚያዝያ ፳ ( ሃያ ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኬኒያ እና ኢትዮጵያ ወታደሮች አልሸባብን ለማደን በሚል ምክንያት ድንበር አቆራርጠው ወደ ሶማሊያ ግዛት በመግባት በሰላማዊ ዜጎች ላይ ከመጠን በላይ የሆነ የሃይል እርምጃዎችን መውሰዳቸውን በሶማሊያ የተሰማሩ የረድኤት ድርጅቶች ለዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ባቀረቡት ሪፖርቶች አጋልጠዋል። በሶማሊያ ጌዶ ግዛት ውስጥ ከ2015 እ.ኤ.አ. ጀምሮ የኬንያ አየር ሃይል፣ አርብቶ አደሮች በተሰማሩባቸው አካባቢዎች ላይ በተደጋጋሚ ጊዜያት ድንበር ...
Read More »የአሜሪካ ኤምባሲ ዜጎቹ ወደጎንደር ከተማ በሚያደርጉት ጉዞ ላይ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳሰበ
ኢሳት (ሚያዚያ 19 ፥ 2009) በጎንደር ከተማ በተደጋጋሚ እየደረሰ ያለውን የቦምብ ፍንዳታ ተከትሎ አሜሪካ ዜጎቿ ወደ አካባቢው በሚያደርጉት ጉዞ ላይ የጥንቃቄ ዕርምጃን እንዲስወዱ ሃሙስ አሳሰበ። በተያዘው ወር ብቻ አራት የእጅ ቦምቦች ጥቃት መድረሱን ያረጋገጠው በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ፣ ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን ባወጣው መግለጫ አመልክቷል። ከሁለት ቀን በፊት በአንድ የቱሪስቶች ማረፊያ ላይ ጥቃት ተፈጽሞ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ማስረዳታቸውን ...
Read More »በህዝባዊ ተቃውሞ ወቅት የተገደሉት የሟች ቤተሰቦችን ካሳ ለመስጠት ምዝገባ ተጀመረ
ኢሳት (ሚያዚያ 19 ፥ 2009) በመንግስት የተቋቋመው የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በቅርቡ የወጣውን የሰብዓዊ መብት ሪፖርት ተከትሎ በአንዳንድ አካባቢ የሟች ቤተሰቦችን ካሳ ለማግኘት ተመዝገቡ የሚል እንቅስቃሴ መጀመሩ ተገልጿል። በዚህም የፌዲራል ፖሊስና የመከላከያ ሰራዊት አባላትና አዛዦችን ከተጠያቂነት ነጻ በማድረግ የአካባቢ ሚሊሺያ ታጣቂዎችና ሃላፊዎችን ለመክሰስ ጠበቃ እንደተቀጠላቸውም ተነግሯቸዋል። ከባህር ዳር ለኢሳት በደረሰው መረጃ መሰረት በሃምሌ 1 ፥ 2008 ብቻ ከመቶ ሰዎች በላይ ...
Read More »በኢትዮጵያ ኤምባሲ ድጋፍ በኢሳት ላይ የተመሰረተውን ክስ የአሌክሳንድሪያ ከተማ ፍ/ቤት ውድቅ አደረገው
ኢሳት (ሚያዚያ 19 ፥ 2009) በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ድጋፍ በኢሳት ላይ የተመሰረተውን ክስ የአሌክሳንድሪያ ከተማ ፍ/ቤት ውድቅ አደረገ። በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በገንዘብ ድጋፍ የሚያደርላቸው ግለሰቦችና አካላት በአሜሪካ ፍ/ቤቶች በኢትዮጵያውያን ተቋማት ግለሰቦች ላይ የመሰረቱት ክስ የቀጠለ ቢሆንም፣ እንደተለመደው በዚሁ ሳምንት ውድቅ መደረጉ ያበሳጫቸው አንድ ዲፕሎማት ነኝ ያሉ በአደባባ ዘለፋ ሲያካሄዱ ተደምጠዋል። በኢሳት፣ በኢሳት የቀድሞ ማኔጂንግ ዳይረክተር አቶ ...
Read More »የህዋ ሳይንስ ምሁር ዶ/ር ለገሰ ወትሮ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ
ኢሳት (ሚያዚያ 19 ፥ 2009) ታዋቂው የህዋ ሳይንስ ምሁር ኢትዮጵያዊው ዶ/ር ለገሰ ወትሮ በድንገተኛ ህመም ከዚህ አለም በሞት ተለዩ። በአስትሮ ፊዚክስ ሙያ የላቀ አስተዋጽዖ ያደረጉት ዶ/ር ለገሰ ወትሮ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር በመሆን አገልግለዋል። የተለያዩ የአለም አቀፍ ሽልማቶች ባለቤትም ነበሩ። በኢትዮጵያ የህዋ ሳይንስ እንዲጎለብት የተለያዩ ፕሮጄክቶችን ቀርጸው ሲንቀሳቀሱ የነበሩት ዶ/ር ለገሰ ወትሮ የኢትዮጵያ ህዋ ሳይንስ ማህበርን ከመሰረቱት ምሁራን እና የሙያ ...
Read More »አንድ የማዕድን ኩባንያ ለወርቅ ፍለጋ በተሰጠው መሬት ላይ የሚኖሩ ሰዎችን ወደ ሌላ ቦታ ለማስፈር ዝግጅት ጀመረ
ኢሳት (ሚያዚያ 19 ፥ 2009) መቀመጫውን በብሪታኒያ ያደረገ የማዕድን ኩባንያ በኦሮሚያ ክልል ለወርቅ ፍለጋ በተሰጠው መሬት ላይ የሚኖሩ በርካታ ሰዎችን ወደ ሌላ ቦታ ለማስፈር የሚያስችል ዝግጅት መጀመሩን ይፋ አደረገ። ከፊ ሚነራል የሚል መጠርያ ያለው ይኸው አለም አቀፍ ኩባንያ ከአንድ አመት በፊት ከመንግስት ጋር በደረሰው ስምምነት በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ዞን ስር በምትገኘው የቱሉ ቃቢ አካባቢ የወርቅ ማውጫ ሰፊ ይዞታ ለ20 ...
Read More »በሆለታ ከተማ ከገበሬዎች ለወሰደው የአበባ እርሻ መሬት ኪራይ ክፍያ ያልፈጸመ የህንድ ኩባንያ መሬቱን እንዲያስረክብ ተወሰነ
ኢሳት (ሚያዚያ 18 ፥ 2009) የኦሮሚያ ክልል ፍርድ ቤት በሆለታ ከተማ ከገበሬዎች ለወሰደው የአበባ እርሻ መሬት መክፈል የሚጠበቅበትን የኪራይ ክፍያ ያልፈጸመ አንድ የህንድ ኩባንያ መሬቱን እንዲያስረክብ ወሰነ። ፍርድ ቤቱ በቅርቡ የሰጠውን ይህንኑ ውሳኔ ተከትሎ ኢትዮጵያን ሚዶውስ የተሰኘው ኩባንያ ከ13 አርሶ አደሮች በኪራይ የወሰደውን 108 ሄክታር መሬት መመለሱን በሃገር ውስጥ ያሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ይሁንና የኩባንያውን ባለድርሻዎች ከሁለት አመት በፊት ጀምሮ ...
Read More »አልሸባብ በኢትዮጵያ ወታደራዊ ተሽከርካሪ ላይ የደፈጣ ጥቃት መፈጸሙ ተገለጸ
ኢሳት (ሚያዚያ 18 ፥ 2009) የሶማሌው ታጣቂ ሃይል አሸባብ በማዕከላዊ ሶማሊያ በኢትዮጵያ ወታደራዊ ተሽከርካሪ ላይ የደፈጣ ጥቃት መፈጸሙን የሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን ረቡዕ ዘገቡ። ይኸው ጥቃት በሂራን ግዛት ስር በምትገኘውና ከበለደወይን ከተማ 40 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው የቡርዳር ከተማ መፈጸሙን ጋሮዌ ኦንላይን የተሰኘ የመገናኛ ተቋም የአይን እማኞች ዋቢ በማድረግ በዘገባው አመልክቷል። በአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ሃይል ስር በሚያገለግሉት የኢትዮጵያ ወታደሮች ላይ ...
Read More »ግንባታቸው የተስተጓጎለው ፋብሪካዎች ወደ ግንባታ የሚገቡበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ከህንድ ባለስልጣናት ጋር ምክክር እያካሄዱ መሆኑ ታወቀ
ኢሳት (ሚያዚያ 18 ፥ 2009) በኢትዮጵያ የስኳር ኮርፖሬሽን ሃላፊዎች የተመራ የልዑካን ቡድን ግንባታቸው ተስተጓጎሎ የሚገኙ የስኳር ፋብሪካዎች ወደ ግንባታ የሚገቡበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ከህንድ ባለስልጣናት ጋር በሃገሪቱ ምክክር እያካሄዱ መሆኑ ታወቀ። የህንድ መንግስት ኮርፖሬሽኑ ሊያካሄዳቸው ላቀዳቸው 10 የስኳር ፋብሪካዎች ማስጀመሪያ ከአራት አመት በፊት የ600 ሚሊዮን ዶላር ብድር ሰጥቶ እንደነበር ይታወሳል። የህንድ መንግስት ለፋብሪካዎቹ ግንባታ ካቀረበው ብድር በተጨማሪ በርካታ ሰራተኞች በፕሮጄክቶቹ እንዲሰማሩ ...
Read More »