.የኢሳት አማርኛ ዜና

ሂልተን ሆቴል ሊሸጥ ነው

ሚያዝያ ፳፫ ( ሃያ ሦስት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ባለአምስት ኮከብ ሆቴል የነበረውን ሒልተን ሆቴል ሊሸጥ መሆኑን ሳምንታዊው ሪፖርተር ዘግቧል። እንደ ጋዜጣው ዘገባ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር የሂልተንን ሽያጭ አስመልክቶ ከሦስት ወራት በኋላ ጨረታ ያወጣል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፤ በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ ከአሥርያላነሱ አገር በቀልና ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች እየተጠባበቁ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ሂልተን አዲስ አበባን ለመግዛት ፍላጎት ...

Read More »

የደሴ ከተማ በተከታታይ ጎርፍ እየተጠቃች መሆኗን ነዋሪዎች ተናገሩ።

ሚያዝያ ፳፫ ( ሃያ ሦስት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ነዋሪዎቹ ለኢሳት እንደገለጹት በተለይ ከሰሞኑ የሚጥለው ተከታታይ ዝናም እየስከተለ ባለው ከባድ ጎርፍ ቤታቸው በመጥለቅለቁ በርካታ ንብረት እየወደመባቸው ይገኛል። ጉዳዩን አስመልክቶ ለአካባቢው መስተዳድር አካላት ተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርቡም ጊዜያዊም ሆነ ዘላቂ ምላሽ ሊያገኙ አለመቻላቸውን የሚናገሩት የከተማዋ ነዋሪዎች፣ አንዳንዶች ጎርፉ ክፉኛ ቤታቸው ዘልቆ በመግባቱ መኖሪያቸውን ጥለው በየዘመዶቻቸው ቤት መጠለላቸውን ይገልጻሉ። ከዚህም ...

Read More »

አልሸባብ በኢትዮ ሶማሌ ድንበር ላይ በምትገኘውን ስልታዊዋ የዋጅድ ከተማ ላይ ጥቃት ፈጸመ

ሚያዝያ ፳፫ ( ሃያ ሦስት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተሽከርካሪ ላይ የተጠመዱ ከባድ መሳሪያዎችን የጫኑ የአልሸባብ ሚሊሻዎች በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ አዋሳኝ ድንበር ላይ የምትገኘውን ስልታዊዋን የዋጅድ ከተማ ላይ ጥቃት መፈጸማቸውንም የሶማሊያ ወታደራዊ ባለስልጣናት እሁድ እለት አስታወቁ። በቦቆል ግዛት ውስጥ በደቡባዊ ምእራብ ሶማሊያ ከሞቃዲሾ 305 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው የሶማሊያ እና የኢትዮጵያ ወታደራዊ ቤዝ ላይም ጥቃት ፈጽመዋል። ...

Read More »

የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ባለፈው የፈረንጆች አመት በከፍተኛ ሁኔታ ማሽቆልቆሉ ተገለጸ

ኢሳት (ሚያዚያ 20 ፥ 2009) የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ባለፈው የፈረንጆች አመት በከፍተኛ ሁኔታ ማሽቆልቆል ማስመዝገቡን አመታዊ ሪፖርቱን ያወጣው ድንበር የለሹ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ተቋም ይፋ አደረገ። እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር የ2016 አም ሪፖርቱን ለንባብ ያበቃው አለም አቀፍ ተቋም ኢትዮጵያ ከነበራት 142ኛ ደረጃ ወደ 150ኛ ማሽቆልቆሏን አመልክቷል። ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ሳውዲ አረብያ፣ ማልዲቭስ እና ኡዝቤኪስታን በአለማችን በመገናኛ ብዙሃን ነጻነታቸው ከፍተኛ ማሽቆልቆል ያስመዘገቡ አራት ...

Read More »

በኬንያ የተሰማሩ የኢትዮጵያና ኬንያ ወታደሮች ሰላማዊ ሰዎች ላይ ከመጠን ያለፈ የሃይል ዕርምጃ ይወስዳሉ ተባለ

ኢሳት (ሚያዚያ 20 ፥ 2009) በሶማሊያ ተሰማርተው የሚገኙ የኢትዮጵያና የኬንያ ወታደሮች በሰላማዊ ሰዎች ላይ ከመጠን ያለፈ የሃይል ዕርምጃን ይወስዳሉ ሲል በእርዳታ ድርጅቶች የወጣ አለም አቀፍ ሪፖርት ገለጸ። ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ጋር በምትዋሰንበት የድንበር አካባቢ ልዩ ፖሊስ በመባል የሚታወቁ የጸጥታ አካላትን በማሰማራት በሶማሌ አርብቶ አደሮች ላይ የጾታ ጥቃትን ያካተተ ኢሰብዓዊ ድርጊት መፈጸማቸውን ቪኦኤ የሶማሌኛው ክፍል ሪፖርትን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል። ይኸው በዜና ተቋሙ ...

Read More »

በጋምቤላ እርሻ ስራ ላይ የተሰማሩ ባለሃብቶች የክልሉ መንግስት ፈቃዳቸውን እንደሰረዘባቸው ገለጹ

ኢሳት (ሚያዚያ 20 ፥ 2009) በጋምቤላ ክልል በእርሻ ልማት ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ከ260 በላይ ባለሃብቶች የክልሉ መንግስት ፈቃዳችንን ከስምምነት ውጭ ሰርዞብናል ሲሉ ቅሬታን አቀረቡ። ባለሃብቶቹ በክልሉ በአንድ መሬት ላይ ተደራርቦ የተሰጠን የብድር አሰራር ተከትሎ ጉዳዩ እስኪጣራ ድረስ ስራችሁን ለጊዜው አቋርጡ ተብለው ከአንድ አመት በላይ መቆየታቸውን አስታውቀዋል። ይሁንና፣ በመንግስት የተካሄደው ጥናት ከተጠናቀቀ በኋላ ወደ ቀድሞ ስራቸው እንመልሳለን ብለው ቢጠብቁም የጋምቤላ ክልል ...

Read More »

ከፊ ሚነራል የአንድ ሚሊዮን ፓውንድ ስትርሊግን እሴት ታክስ ተመላሽ ከመንግስት መቀበሉን ገለጸ

ኢሳት (ሚያዚያ 20 ፥ 2009) በኦሮሚያ ክልል የወርቅ ማውጣት ስራውን ለመጀመር በዝግጅት ላይ የሚገኘው ከፊ ሚነራል ኩባንያ የአንድ ሚሊዮን ፓውንድ ስተርሊንግ (ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ) የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመላሽ ከመንግስት መቀበሉን አርብ አስታወቀ። በለንደን አለም አቀፍ የአክሲዮን ንግድ ውስጥ ተመዝግቦ የሚገኘው ይኸው ድርጅት የቱሉ ቆጲ  ፕሮጄክቱ ከሌላ ኩባንያ በተረከበ ጊዜ ያለአግባብ የድርጅቱን የቫት ክፍያ እንድፈጸም ተደርጊያለሁ ሲል ከወራት በፊት ...

Read More »

የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሃላፊ ኢትዮጵያን ሊጎበኙ መሆኑ ተገለጸ

ኢሳት (ሚያዚያ 20 ፥ 2009) በኢትዮጵያ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እና ግድያዎችን ለመመርመር ጥያቄ ሲያቀርብ የቆየው የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሃላፊ በኢትዮጵያ ጉብኝት ሊያደርጉ መሆኑ ተገለጸ። የኮሚሽኑ ሃላፊ ዘይድ ራድ አል-ሁሴን በቀጣዩ ሳምንት ከሚያዚያ 24 እስከ 26 ፥2009 አም ድረስ በአዲስ አበባ ቆይታ እንደሚኖራቸው ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። የኮሚሽኑ ሃላፊ ራድ አል-ሁሴን በሃገሪቱ በተለይ በኦሮሚያ ክልል ለአንድ አመት ያህል ...

Read More »

በበለና እና በአማሮ ወረዳዎች መካከል በተነሳ ግጭት የዜጎች ህይወት እያለፈ ነው

ሚያዝያ ፳ ( ሃያ ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ምንጮች እንደገለጹት በደቡብ አካባቢ በሰገን ዞን በአማሮ ወረዳ እና አጎራባች በሆነው በጉጂ ዞን ውስጥ በሚገኘው በላና ወረዳ በተነሳ ግጭት የዜጎች ህይወት እያለፈ ነው። በአካባቢው የተነሳውን ከፍተኛ ድርቅ ተከትሎ በአካባቢው የሚኖሩ ማህበረሰቦች ለእንስሳት መኖና ውሃ በማጣታቸው ከአካባቢው አካባቢ መሰደዳቸውን ተከትሎ የተፈጠረ ግጭት መሆኑን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ ግጭቱ ከተጀመረበት ካለፉት 4 ...

Read More »

የይርጋለም መምህራን ለአባይ ቦንድ በግዳጅ እንዲገዙ መጠየቃቸውን ተቃወሙ

ሚያዝያ ፳ ( ሃያ ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በይርጋለም ከተማ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ለአባይ ግድብ ግንባታ በግዳጅ እንዲያወጡ መጠየቃቸውን ከተቃወሙ በሁዋላ፣ ዛሬ አርብ ደግሞ የይርጋለም መምህራን ለግድቡ እንዲያዋጡ የተጠየቁ ቢሆንም፣ መምህራን ተቃውመውታል። “መምህራኑ እኛ ያለን ዲግሪ ነው፣ ወረቀት ነው፣ ለራሳችን የሚሆን ፍጆታም የለንም” በማለት ተቃውመውታል። የካቢኔ ስብሰባ ላይ “የመንግስት ባለስልጣናትን ልብሳቸውንና ሰውነታቸውን ብታዩት ደረጃውን የጠበቀ ነው፣ ማሰብ ግን ...

Read More »