ኢሳት (ሚያዚያ 24 ፥ 2009) የሳውዲ አረቢያ መንግስት ህጋዊ ፈቃድ የላቸውም በሚል በ90 ቀናት ውስጥ ሃገሪቱን ለቀው እንዲወጡ በማድረግ ላይ ካሉት ሰዎች መካከል አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ተገለጠ። የሳውዲ መንግስት ባለፈው ወር ተግባራዊ ባደረገው በዚሁ አዲስ መመሪያ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ የተለያዩ ሃገራት ዜጎች ሃገሪቱን ለቀው ይወጣሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ከ300 ሺ የሚበልጡ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ማይግራንትስ ራይትስ (Migrants’ Rights) የተሰኘ አለም ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተው ረሃብ የሃገር ገጽታ ሊያበላሽ ይችላል በሚል ችላ መባሉ ተገለጸ
ኢሳት (ሚያዚያ 24 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ተከስቶ ያለው የድርቅ አደጋ እያደረሰ ያለው ጉዳት የሃገሪቱን ገጽታ ሊያበላሽ ይችላል በሚል በመንግስት ችላ ተብሎ ቆይቷል የሚል ትችት በመቅረብ ላይ መሆኑን ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ማከሰኞ ዘገበ። በስልጣን ላይ ያለው ገዥው የኢህአዴግ መንግስት ኢትዮጵያ ዳግም ወደ ድርቅና ረሃብ አደጋ ተመልሳለች መባልን እንደማይፈልግ ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ አስነብቧል። ይሁንና፣ ድርቁ በተለይ በኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል እያደደረሰ ያለው ጉዳት ...
Read More »ከፊ ሚነራል የተባለ ኩባንያ በኦሮሚያ አድርሷል በተባለ የአካባቢ ተፅዕኖ ካሳ እንዲከፍል ጥያቄ ቀረበበት
ኢሳት (ሚያዚያ 24 ፥ 2009) በኦሮሚያ ክልል ወርቅ ለማውጣት በዝግጅት ላይ የሚገኘው የብሪታኒያ ከፊ ሚነራል ኩባንያ ከአመታት በፊት በክልሉ አድርሷል በተባለ የአካባቢ ተፅዕኖ የ12 ሚሊዮን ዶላር የካሳ ጉዳት ጥያቄ ቀረበበት። ኩባንያው በምዕራብ ወለጋ አካባቢ ቱሉ ቆቢ በተባለ ስፍራ ወርቅ ለማውጣት በዝግጅት ላይ ሲሆን፣ ይህንን ፕሮጄክት ከመረከቡ በፊት በአካባቢው በተመሳሳይ እንቅስቃሴ በቆየበት ከ1998 እስከ 2006 አም በስፍራው አካባቢያዊ ጉዳት አድርሷል ተብሎ ...
Read More »ባለፈው ሳምንት በጎንደር በፈነዳው ቦምብ አንድ የውጭ አገር ዜጋን ጨምሮ አምስት ሰዎች መጎዳታቸው ተገለጸ
ኢሳት (ሚያዚያ 23 ፥ 2009) የብሪታኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለፈው ሳምንት በጎንደር ከተማ ደርሶ በነበረው የእጅ ቦምብ ፍንዳታ አንድ የውጭ ሃገር ዜጋን ጨምሮ አምስት ሰዎች መጎዳታቸውን ሰኞ ይፋ አድርጓል። ይሁንና የብሪታኒያ መንግስት ጉዳት የደረሰበትን የውጭ ዜጋ ማንነት ከመግለጽ የተቆጠበ ሲሆን ዜጎቹ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ባሰራጨው የጉዞ ማሳሰቢያ አመልክቷል። ባለፈው ሳምንት በጎንደር ከተማ የእንግዶች ማረፊያ ሆቴል ላይ የደረሰውን የቦምብ ፍንዳታ አስመልክቶ ኢሳት ...
Read More »የአርጆ ዴዴሳ ስኳር ፋብሪካ በሸንኮራ እጥረት ተከትሎ ምርቱን አቋረጠ
ኢሳት (ሚያዚያ 23 ፥ 2009) የአርጆ ደዴሳ ስኳር ፋብሪካ ያጋጠመውን የሸንኮራ አገዳ አቅርቦት እጥረት ተከትሎ ምርቱን ሙሉ ለሙሉ አቋረጠ። ከ2007 አም ጀምሮ ስራውን በከፊል የጀመረው ፋብሪካው ችግሩን ለመቅረፍ በግንባታው ላይ ከሚገኝ ግድብ ውሃን በመጥለፍ የሸንኮራ አገዳ ለማምረት ቢሞከርም በኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት ችግር ጥረቱ ሳይሳካ መቅረቱን የፋብሪካው ስራ አስኪያጅ አቶ ካባ መርጋ ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል። ለዚሁ ፋብሪካ አገልግሎት አንዲሰጥ የታሰበ ...
Read More »ቅዳሜ በባህር ዳር ከተማ በፈንዳ ቦምብ አንድ ሲቪል ሲገደል ሶስት የልዩ ሃይል ፖሊስ አባላት መቁሰላቸው ተገለጸ
ኢሳት (ሚያዚያ 23 ፥ 2009) ቅዳሜ ባህርዳር በፈነዳው ቦምብ አንድ ሲቪል ሲገደል አንድ ኢንስፔክተርን ጨምሮ ሶስት የልዩ ሃይል ፖሊሶች መቁሰላቸውን የኢሳት ምንጮች ገለጹ። ዳሸን ቢራ በአዲስ ስያሜ “ባላገሩ” በሚል ራሱን ለማስተዋወቅ በጠራው የሙዚቃ ኮንሰርት አካባቢ በፈነዳው ቦምብ የሙዚቃ ኮንሰርቱ መቋረጡም ታውቋል። ከፍንዳታው ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች የታሰሩ ሲሆን፣ እስራቱ ይበልጥ በባጃጅ ተሽከርካሪ ሹፌሮች ላይ ያተኮረ እንደሆነም የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። የባጃጅ ...
Read More »በቅርቡ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የቀረበው ሪፖርት “ተዓማኒነት” የጎደለው ነው ሲል አንድ ተቋም ገለጸ
ኢሳት (ሚያዚያ 23 ፥ 2009) መቀመጫውን በቤልጂየም ያደረገ አንድ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም በቅርቡ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የቀረበን ሪፖርት “ተዓማኒነት” የጎደለው ነው ሲል አጣጣለው። ይኸው Unrepresented Nation and Peoples Organization የሚል መጠሪያ ያለው ተቋም በኮሚሽኑ ሪፖርት የተደረገው የሟቾች ቁጥር በትክክለኛ ያልተቀመጠና በገለልተኛ ያልተከናወነ ነው በማለት ምርመራው በገለልተኛ አካል እንዲካሄድ ጥሪውን አቅርቧል። በኦሮሚያ፣ አማራና የደቡብ ክልሎች የተካሄዱ ህዝባዊ ...
Read More »ዳሸን ቢራ “ባላገሩ ቢራ” በሚል የስያሜ ለውጥ በባህርዳር ከተማ ባዘጋጀው ኮንሰርት ላይ በፈነዳው ቦምብ 2 ሰዎች መሞታቸውና 31 ሰዎች መቁሰላቸው ተነገረ።
ሚያዝያ ፳፫ ( ሃያ ሦስት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዛሬ በባህር ዳር የጅምላ አፈሳ ሲካሄድ ውሏል። ኮንሰርቱ እየተካሄደ ያለበት ሥፍራ በሁለት ተከታታይ የቦምብ ፍንዳታዎች መናወጡን ተከትሎ ፕሮግራሙ ሙሉ በሙሉ የተቋረጠ ሲሆን፣ በርካታ ታዳሚዎች በፖሊስ ተከበው ወደ እስር ቤት ተወስደዋል። ኮንሰርቱ ላይ ሙዚቃ ስትጫዎት ፍንዳታ በመሰማቱ ክፉኛ የደነገጠችውን ድምጻሚ ኩኩ ሰብስቤን ጨምሮ ከባድና ቀላል የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ሰዎች ...
Read More »ከፍተኛ ወጪ የወጣበትና ትናንት ሚያዚያ 22 ቀን 2009 ዓ ም በጎንደር የተከፈተው 7ኛው የከተሞች ፎረም እንደተጠበቀው ሊደምቅ አለመቻሉ ተገለጸ።
ሚያዝያ ፳፫ ( ሃያ ሦስት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ህወኃት በዓሉን በልዩ ድምቀት ለማክበር በማሰብ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአቶ ደመቀ መኮንን የሚመራ ግብረ ሀይል አቋቁሞ በርካታ የሰው ሀይል በመመደብና እና ከፍተኛ ገንዘብበማፍሠስ በዓሉ ርብርብ ቢያደርግም፣ በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ የታሰበውን ያህል ውጤት ማግኘት ሳይቻል መቅረቱ ተመልክቷል። በጎንደር መከበር በጀመረው በዚህ በዓል ተይዞ የነበረው ዕቅድ ህብረተሰቡ በነቂስ ወደ አደባባይ ...
Read More »በዓለም ላይ ለ128ኛ፣ በሀገራችን ደግሞ ለ42ኛ ጊዜ የሚዘከረውን የላባደሮች ቀን -ሜይ ዴይን ምክንያት በማድረግ በውጪ ያሉ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ።
ሚያዝያ ፳፫ ( ሃያ ሦስት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተለይ በመካከለኛው ምሥራቅ በሊባኖስ፣ እንዲሁም በስዊድንና በኖርዌይ የሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያን ባደረጓቸው የተቃውሞ ሰልፎች በአኢትዮጵያ ውስጥ በነገሠው አምባገነን አገዛዝ የሠራተኛውም ሆነ የሁሉም ዜጋ መብት መረገጡን ድምጻቸውን ከፍ አድርገው አሰምተዋል። ሰላማዊ ዜጎችና ንጹሀን ሀሳባቸውን በመግለጻቸው ሳቢያ በእስር እየማቀቁ በሚገኙባት ኢትዮጵያ የዓለም ላባደሮች ከመቶ ዓመት በፊት የተቀዳጇቸው መብቶች ሊከበሩ እንዳልቻሉ የጠቀሱት ...
Read More »