.የኢሳት አማርኛ ዜና

ሱዳን ከኢህአዴግ ጋር በመተባበር በታጋዮች ላይ ዘመቻ ከፈተች

ሚያዝያ ፳፮ ( ሃያ ስድስት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ የሰሜን ጎንደር ወረዳዎች የሚፈጸሙ ጥቃቶች መበራከት ያሰጋው የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ፣ ከሱዳን ጋር ‘ የሰው እና የእጽ ዝውውርን መግታት” የሚል ሽፋን በሰጠው ዘመቻ፣ ራስ ምታት ሆነዋል ያላቸውን ታጋዮች የማደን ዘመቻ ጀምሯል። ኢሳት ቀደም ብሎ እንደዘገበው በሁለቱ ድንበሮች አካባቢ በሚገኙ ጫካዎች ይኖራሉ ተብለው የተጠረጠሩ ታጋዮችን ለማጥቃት የሄዱ ...

Read More »

በዶ/ር መረራ ጉዲና የክስ መቃወሚያ ላይ ዓቃቤ ሕግ ምላሽ ሰጠ

ሚያዝያ ፳፮ ( ሃያ ስድስት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ የአውሮፓ ሕብረት ባቀረበላቸው ግብዣ ላይ ተገኝተው ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ ከሕግ አግባብ ውጪ የታሰሩት ዶ/ር መረራ ጉዲና ክስ ላይ አቃቤ ሕግ መቃወሚያ አቅርቧል። ሚያዝያ 26 ቀን 2009 ዓ.ም በዋለው የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ 19ኛው ምድብ ችሎት ላይ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና ...

Read More »

በኢትዮጵያ የኑሮ ውድነቱ ማሻቀቡን የኢትዮጵያ ስታስቲክ ኤጀንሲ አስታወቀ

ሚያዝያ ፳፮ ( ሃያ ስድስት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ የዋጋ ንረት ከወር ወር እየባሰበት መምጣቱን የኢትዮጵያ ስታስቲክ ኤጀንሲ ወርሃዊ ጥናት አመላክቷል። ድርጅቱ ባወጣው ዝርዝር ጥናት መሰረት ባለፈው መጋቢት ወር ላይ የምግብ ሸቀጦች ከነበሩበት 9 ነጥብ 6 ከመቶ ወደ 12 ነጥብ 2 በመቶ ጭማሪ አሳይተዋል። ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦች በበኩላቸው በመጋቢት ወር ከነበሩበት 4 ነጥብ 6 ከመቶ ...

Read More »

አሜሪካ 2 መቶ ሚሊየን ዶላር እርዳታ ከኢትዮጵያና ዩጋንዳ እንደምትቀንስ ተዘገበ

ሚያዝያ ፳፮ ( ሃያ ስድስት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- እንደ አሜሪካው የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ዘገባ ከሆነ ለምስራቅ አፍሪካ በየአመቱ ይመደብ ከነበረው አጠቃላይ እርዳታ የ30.8% ቅናሽ መደረጉንና ይህም በሚቀጥለው በጀት አመት 2017/18 ዓ.ም ተግባራዊ እንደሚደረግ አስታውቋል። በዚሁ መሰረትም ከፍተኛ ቅናሽ ከተደረገባቸው አገሮች መካከል የኢትዮጵያው 131.2 ሚሊዮን ዶላር ከፍተኛው ሲሆን ፣ ዩጋንዳ 67.8 ሚሊዮን ዶላር፣ ሩዋንዳና ታንዛንያ እያንዳንዳቸው ...

Read More »

በአፋር በተነሳ ግጭት ከ20 በላይ ሰዎች ተገደሉ ።ሁለት የመከላከያ አባላትም ህይወታቸው አልፏል።

ሚያዝያ ፳፭ ( ሃያ አምስት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሚያዚያ 22 እስከ 23 ፣ 2009 ዓም የቀሰም ቀበና የስኳር ፕሮጀክትን የእርሻ መሬት ለማስፋት በጎሳዎች መካከል ሆን ተብሎ በተቀሰቀሰ ግጭት 23 ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል። የአብሌክ አድአሊ እና ሲድሃ ቡራ ጎሳዎች በጋራ ተነስተው የመሬት ወረራውን ለመቃወም እንዳይችሉ በመካከላቸው የመከፋፈል ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ ሁለቱ ጎሳዎች እርስ ...

Read More »

የተባበሩት መንግስታት ለ130 ሺህ ሕጻናት አፋጣኝ የምግብ እርዳታ ሊያደርግ መሆኑን አስታወቀ

ሚያዝያ ፳፭ ( ሃያ አምስት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ተመድ በኢትዮጵያ እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ የምግብ እጥረት ላጋጠማቸው ታዳጊ ህጻናት ተጎጂዎች በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዓለም ሕጻናት አድን ድርጅት ዩኒሴፍ በኩል የ3 ሚሊዮን ዩሮ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያደርግ አስታወቀ። የተገኘውም እርዳታ ክፉኛ ለተጎዱ ህጻናት ህይወት ለማዳን እንደሚውልም ድርጅቱ አስታውቋል። ከፍተኛ ድርቅን ተከትሎ ርሃብ በተከሰተባቸው የአፋር፣ ሶማሊያ፣ ኦሮምያ ...

Read More »

“ኢትዮጵያ” የተሰኘው አዲሱ የአርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን አልበም በህዝብ ዘንድ ያለው ተቀባይነት ከተጠበቀው በላይ መሆኑን የአርቲስቱ የቅርብ አማካሪዎች በተለይ ለኢሳት ገለጹ።

ሚያዝያ ፳፭ ( ሃያ አምስት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመጀመሪያው ዙር የታተመው 500 ሺህ ኮፒ በቂ ላይሆን ይችላል የሚል ሥጋት በማሳደሩና በበርካታ አፍሪካ ሀገሮች ካሉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ተጨማሪ ጥያቄ በመቅረቡ ሁለተኛ ዙር ሕትመት መቀጠሉን አስተባባሪዎቹ አስረድተዋል። አልበሙ ከወጣበት ማክሰኞ ከቀኑ 6 ፡00 ሰዓት ጀምሮ በጉጉት ሲጠብቅ የነበረው ሕዝብ ወደ ሲዲ መደብሮች በመትመሙ አከፋፋዮችና ነጋዴዎች በአዲስ አበባ ለህዝብ ...

Read More »

በጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ

ሚያዝያ ፳፭ ( ሃያ አምስት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሃገራችን ካለችበት አደገኛ የሆነ የጥፋት አዘቅት ውስጥ እንድትወጣም ሆነ ፤የስርዓት ለውጥም መምጣት የሚቻለው እያንዳንዱ ዜጋ በተደራጀ መልኩ ሲታገል ፤ድርጅቶችም ሳይጠላለፉ በመመካከር ስራዎችን በጋራ መስራት ሲችሉ መሆኑን በውይይቱ ላይ ተነስቷል። የትብብር መድረኩ በጀርመን አካባቢ የሚጠሩ ማናቸውም ሰላማዊ ሰልፎችና የተቃዋሚ እንቅስቃሴዎች በታቻለ መጠን በተቀናጀና በተናበበ መልኩ በጋራ እንዲዘጋጁ፣ በአካባቢው የሚካሄዱ ...

Read More »

በሱዳንና ኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ የሁለቱ ሃገራት ሰራዊቶች መስፈራቸው ተገለጸ

ኢሳት (ሚያዚያ 25 ፥ 2009) በቅርቡ በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል በድንበር ዙሪያ ቁጥጥርን ለማጠናከር የተደረገውን ስምምነት ተከትሎ የሁለቱ ሃገራት ሰራዊቶች በአዋሳኝ ድንበር ዙሪያ መስፈራቸውን የሱዳን ባለስልጣናት ረቡዕ አስታወቁ። የሁለቱ ሃገራት ተወካዮች ባለፈው ወር በባህር ዳር ከተማ ባካሄዱት የድንበር ውይይት በአካባቢው ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር እና የአደንዛዥ ዕፅን ይቆጣጠራል የተባለ የጋራ ሰራዊት እንዲሰፍር የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው ይታወሳል። የዚህኑ የመግባቢያ ሰነድ መፈረም ተከትሎ የኢትዮጵያና ...

Read More »

ከ300 ሺ በላይ ህጻናት አስከፊ የምግብ እጥረት ጉዳት እየደረሰባቸው እንደሆነ ዩኒሴፍ ገለጸ

ኢሳት (ሚያዚያ 25 ፥ 2009) በኢትዮጵያ በአራት ክልሎች እየተባባሰ ባለው የድርቅ አደጋ ዕድሚያቸው ከአምስት አመት በታች የሆነ ከ300 ሺ በላይ ህጻናት በአስከፊ የምግብ እጥረት ጉዳት እየደረሰባቸው መሆኑን የተባበሩት መንግስት የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) ገለጸ። የአለም ባንክ በበኩሉ ተደጋጋሚ የድርቅ አደጋ እያጋጠማት ያለው ኢትዮጵያ አደጋውን በዘላቂነት መከላከል በሚቻልበት ጉዳይ ዙሪያ ማተኮር እንዳለበት አሳስስቧል። አዲስ ተከስቶ ባለው በዚሁ የድርቅ አደጋ በኦሮሚያ፣ አፋር፣ ...

Read More »