ግንቦት ፩ ( አንድ ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሱዳን ትሪቢዩን እንደዘገበው የደቡብ ሱዳን የደህንነት ባለሥልጣናት ጁባ ውስጥ የኢትዮጵያ አንድነት አርበኞች ግንባር አባላት እንደሆኑ የሚታመኑ ስድስት አማጽያንን አስረዋል። ኢትዮጵያውያን አማጽያኑ የታሰሩት የአካባቢው ሚሊሻዎች ከሚጠቀሙባቸው ህገ ወጥ የመሣሪያ ዝውውር ጋር በተያያዘ ነው። ቀደም ባለው ጊዜ ለኢትዮጵያ መንግስት እጃቸውን የሰጡት የኢትዮጵያ አንድነት አርበኞች ግንባር መሪ ጄነራል ቶዋት ፓል ቾይ የድርጅቱ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ዶክተር ቴዎድሮስ አድሀኖምን የሚቃወም ታላቅ አውሮፓ አቀፍ ሰልፍ ተጠራ
ግንቦት ፩ ( አንድ ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የህዝባዊ ወያነ ኃርነት ትግራይ ዋና የሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ዶክተር ቴዎድሮስ አድሀኖም ለዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተርነት መመረጥ የለባቸውም ያሉ እጅግ በርካታ ኢትዮጵያውያን ታላቅ አውሮፓ አቀፍ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን አስታወቁ። እንደ ሰልፉ አስተባባሪዎች ገለጻ በስዊዘርላንድ ጄኔቫ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጽህፈት ቤት ፊት ለፊት በሚደረገው በዚህ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ...
Read More »አስር ሚሊዮን ዶላር ወይም 230 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የኢትዮጵያ በርበሬ ጥራቱን ያልጠበቀ ነው ተብሎ ከአውሮፖ ተመለሰ።
ግንቦት ፩ ( አንድ ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሳምንታዊው ካፒታል እንደዘገበው ከፍተኛ መጠን ያለው ይህ የተፈጬ በርበሬ ከአውሮፓ ገበያ ሊመለስ የቻለው፤ በአውሮፓ መግቢያ ባሉ ላቦራቶሪዎች በተደረገ ምርመራና ቁጥጥር አፍላቶክሲን እና ኦክራቶክሲን የተባሉ በካይ ንጥረ ነገሮች ስለተገኙበት ነው ተብሏል። የኢትዮጵያ በርበሬው የተቀመጠውን የጥራት ደረጃ እስካላሟላ ድረስ ወደ ለንደን እንዳይገባ ባለፈው ዓመት የእንግሊዝ መንግስት እገዳ መጣሉ ይታወሳል። ይህም በመሆኑ ...
Read More »የወጣት ሙጂብ አሚኖ የምስክርነት የድምጽ ፋይል ጠፋ በሚል ምክንያት የፍርድ ብያኔ ተራዘመ::
ግንቦት ፩ ( አንድ ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሕግ አግባብ ውጪ በእስር ሲንገላታ በቆየው በወጣት ሙጂብ አሚኖ ክስ ጉዳይ ዛሬ ግንቦት 1 ቀን 2009 ዓ.ም ያስቻለው የከፍተኛው ፍርድ ቤት ችሎት፤ የመከላከያ ምስክሮች ላይብይን ለመስጠት የተሰጠውን የጊዜ ቀጠሮ አራዘመ። ወጣት ሙጂቦ ፣በእነ ኤሊያስ ከድር የክስ መዝገብ በሃሰት አልመሰክርም በማለቱ፣ እንዲሁም በእነ ከድር መሃመድ የክስ መዝገብ የተከሠሱትን እነ አቡበከር ...
Read More »ሞዛምቢክ 24 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ወደ አገራቸው መለሰች
ግንቦት ፩ ( አንድ ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሕገወጥ ቪዛ አስመትተው ከአዲስ አበባ ወደ ሞዛምቢኳ መዲና ማፑቶ የገቡ 24 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ማድረጋቸውን የአገሪቱ ባለስልጣናት አስታወቁ። ከኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች በተጨማሪም 11 የባንግላዲሽ ዜጎችም በተመሳሳይ ሁኔታ በመግባታቸው እነሱም ወደ ትውልድ አገራቸው ተልከዋል። ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች በማፑቶ አውራጃ በማቫሊ ድንበር አቆራርጠው ወደ ሞዛምቢክ መግባታቸውንም ባለስልጣኑ አክለው ገልጸዋል። ባለፈው ሚያዚያ ...
Read More »ኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፓርት አባላትንና የሰብዓዊ መብት ድርጅቶችን በነጻነት እንዲንቀሳቀሱ እንድትፈቅድ የተመድ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር ጠየቁ
ኢሳት (ሚያዚያ 30 ፥ 2009) የኢትዮጵያ መንግስት የተቃማዊ ፓርቲ አባላትን፣ ነጻ የመገናኛ ብዙሃንና፣ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች በነጻነት እንዲንቀሳቀሱ መፍቀድ እንዳለበት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ገለጸ። በቅርቡ ጊዜ በመንግስት ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ይፋ የተድረገውን ሪፖርት ማረጋገጥም መቀበልም እንዳልቻሉ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር ገልጸዋል። ባለፈው ሳምንት ኢትዮጵያን የጎበኙት ኮሚሽነሩ ዛይድ ራድ አል ሁሴን በተለይ ከዶቼ ዌሌ ሬዲዮ ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ፣ ...
Read More »ግብፅ ከሱዳን ጋር የምትዋዘግብበትን የሃይላብ ግዛትን አስመልክቶ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተቃውሞ አቀረበች
ኢሳት (ሚያዚያ 30 ፥ 2009) የሱዳን መንግስት በቀይ ባህር ላይ በሚገኘው የሃይላብ ግዛት ላይ ያነሳውን የይገባኛል ጥያቄ ተከትሎ ግብፅ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተቃውሞ አቀረበች። ግብፅና ሱዳን በአዲስ መልኩ የገቡበት ይኸው የድንበር ይዞታ ውዝግቡ በአባይ ግድብ ላይ በመካሄድ ላይ ባለው የሶስትዮሽ ድርድር ላይ አሉታዊ ተፅዕኖን ያሳድራል ተብሎ ተሰግቷል። የሱዳን መንግስት በግዛቱ ላይ ያነሳውን የይገባኛ ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ ይፈታል ያለውን አዲስ ሃሳብ ...
Read More »ኢሳት የ7ኛ አመት ምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ በሲልቨርስፕሪንግ የተሳካ ገቢ ማሰባሰቢያ አካሄዱን አስታወቀ
ኢሳት (ሚያዚያ 30 ፥ 2009) የኢትዮጵያ ሳተላይት ሬዲዮና ቴሌቪዥን (ኢሳት) የ7ኛ አመት ምስረታን በማድረግ በሲልቨር ስፕሪንግ ሜሪላንድ የተካሄደው የገቢ ማሳሰቢያ የተሳካ እንደነበር አስተባባሪዎች ገለጹ። የዋሽንግተን ዲሲ የኢሳት ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ያዘጋጀው የ7ኛ አመት የምስረታ በዓል በድምቀት መከበሩን ለማወቅ ተችሏል። በስነ-ስርዓቱ ታዋቂዎቹ ድምጻውያን ሻምበል በላይነህ እና ደሳለኝ መልኩ ኮሜዲያን ወንደወሰን ( ዶክሌ) ታዳሚዎችን ሲያዝናኑት አምሽተዋል። የኢሳት 7ኛ አመት የምስረታና የገቢ ማሰባሰቢ ...
Read More »ብሪታኒያዊው ዴቪድ ናባሮ የአለም ጤና ድርጅት ሆነው የመመረጥ እድላቸው አነስተኛ መሆኑ ተገለጸ
ኢሳት (ሚያዚያ 30 ፥ 2009) በተያዘው ወር የአለም ጤና ድርጅት ሃላፊን ለመምራት በሚደረገው የአባል ሃገራት ምርጫ ብሪታኒያዊው ተወዳዳሪ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ድንጋጌ መሰረት የመመረጥ እድላቸው አነስተኛ መሆኑ ተገለጸ። ብሪታኒያ በአባልነት ያለችበት የጸጥታው ምክር ቤት ደንብ መሰረት ሃገሪቱ ለአለም ጤና ድርጅት ሃላፊን ከመወከል እንደሚከለክላት ብሪኪንግ ታይም የተሰኘ የጤና መጽሄት ሰኞ በጉዳዩ ዙሪያ ባቀረበው ዘገባ አመልክቷል። ይኸው አለም አቀፍ ድንጋጌ ከሶስቱ የመጨረሻ ...
Read More »ከፊ ሚነራል ከቱሉ ቆቢ ፕሮጄክት የሚወጣውን የወርቅ ሃብት የሚያስተዳደር አካል ከመንግስት ጋር መቋቋሙን አስታወቀ
ኢሳት (ሚያዚያ 30 ፥ 2009) በኦሮሚያ ክልል የወርቅ ማውጣት ስራ ለመጀመር በዝግጅት ላይ የሚገኘው ከፊ ሚነራል ኩባንያ በቱሉ ቆቢ ፕሮጄክት የሚወጣውን የወርቅ ሃብት የሚያስተዳደር አካል ከመንግስት ጋር ማቋቁሙን ሰኞ አስታወቀ። በአካባቢው የሚወጣውን ከፍተኛ የወርቅ ሃብት ለማስተዳደር በሁለቱ ወገኖች በተደረሰ አዲስ ስምምነት መንግስት 25 በመቶ ድርሻ እንዲኖረው የተደረገ ሲሆን፣ ቀሪው 75 በመቶ ደግሞ የከፊ ሚነራል እንዲሆን ተወስኗል። መንግስት 25 በመቶ ድርሻን ...
Read More »