ግንቦት ፫ ( ሦስት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት ምንጮች እንዳደረሱን መረጃ በርካታ ወጣቶችን ሲገድልና ጠቁሞ ሲያስገድል በነበረው አበራ ቡልቻ ላይ የግድያ እርምጃ የተወሰደው በትናንትናው ዕለት ነው። አበራ ቡልቻ የህወኃት- ኦህዴድ ተላላኪ በመሆን ከደላቸውና ካስገደላቸው የከተማው ወጣቶች መካከል ወጣት ኢያሱ ሰሎሞን ይገኝበታል። ስውር ሕዝባዊ ግብረ-ኃይሉ ትናንት በወሰደው በዚህ እርምጃ አበራ ቡልቻ ከመገደሉም ባሻገር የግብር ተባባሪው የሆነው ወንድሙ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የኢትዮጵያ ብርድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፤ በሙስናና በብልሹ አሠራር ተተብትቧል በተባለው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ላይ ውሳኔ አሳለፈ።
ግንቦት ፫ ( ሦስት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሁለት ሳምንት በፊት ለፓርላማው ሪፖርታቸውን ያቀረቡት የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሥዩም መኮንን እና የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑትየመንግሥት ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትሩ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ፤በሥራቸው ጣልቃ የሚገቡ ባለስልጣናት ኮርፖሬሽኑ ተቋማዊ ነጻነቱ ጠብቆ እናዳይጓዝ እንቅፋት እንደፈጠሩባቸው መናገራቸው ይታወሳል።ሪፖርት አቅራቢዎቹ በኮርፖሬሽኑ ውስጥ ቡድንተኝነት፣ ዘረኝነት፣ ሙስናና ብልሹ አሠራር መኖሩን በይፋ ማመናቸውን ተከትሎ የሚመለከተው የምክር ...
Read More »የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ሊኖረው የሚገባውን ጥቅም በተመለከተ የኦህዴድ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ረቂቅ ሰነድ አዘጋጅቶ ለሚመለከተው አካል ማቅረቡ ተገለጸ።
ግንቦት ፫ ( ሦስት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሆኖም ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጬውን ሰነድ እንደማያውቀው አንድ የክልሉ ባለሥልጣን ተናግረዋል። የኦሮሚያ ክልል የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ለሰንደቅ እንደገለጹት ፣ ኦህዴድና የክልሉ መንግስት በህገ መንግስቱ አንቀጽ 49 ንኡስ አንቀጽ 5 መሰረት የልዩ ጥቅምን አተገባበርን በተመለከተ መካተት አሉባቸው ያሏቸውን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መብቶችን በዝርዝር ለሚመለከተው አካል አስተላልፈዋል። “ክልሉ ...
Read More »አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከሶማሊያው ፕሬዚዳንት ጋር የሰጡት መግለጫ የሶማሊ ላንድን ባለሥልጣናት አስቆጣ።
ግንቦት ፫ ( ሦስት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ሳምንት አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት መሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆ ወደ አዲስ አበባ መጥተው በነበረበት ወቅት በሰጡት የጋራ መግለጫ ላይ አቶ ኃይለማርያም ፦” ከ እንግዲህ ኢትዮጵያ የሶማሊያ ፌዴራል መንግስትን ሳታስፈቅድ ከሌሎች የሶማሊያ ትናንሽ ክልሎች ጋር ግንኙነት አታደርግም” ማለታቸው ነው የሶማሊ ላንድን ባለሥልጣናትና ሕዝብ እያነጋገረ ያለው። አቶ ኃይለማርያም አክለውም ፦” ዓለማቀፉ ማህበረሰብም ...
Read More »የአዲስ አበባ ነጋዴዎችን በግብር ስም መዝረፉ ተባብሶ ቀጥሏል
ግንቦት ፫ ( ሦስት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ ንግድና የገቢዎች ቢሮ በተጨማሪ የዋጋ ግብር ማለትም በቫት አዋጅ ስም የድርጅቱን ሠራተኞች ገንዘብ እየሰጠ በሰላይነት በማሰማራትነጋዴዎች ላይ ምዝበራ እየፈጸመ መሆኑን ነጋዴዎች አጋለጡ። ነጋዴዎቹ በተለይ ለኢሳት እንደገለጹት የአገዛዙ ሹመኞች ነጋዴዎችን ከሕግ አግባብ ውጪ በመክሰስና የሃሰት ምስክሮችን በማቆም የነጋዴው ማህበረሰብንማሰርና ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ መቀጮ ማስስከፈል ሥራዬ ብለው ተያይዘውታል። የንግድና ገቢዎች ...
Read More »የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አበድሮ የማይሰበስበው የገንዘብ መጠን በሃላፊዎች መካከል አለመግባባት መፍጠሩ ተነገረ
ኢሳት (ግንቦት 2 ፥ 2009) የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለተለያዩ ተበዳሪዎች አበድሮ የማይሰበስበው የገንዘብ መጠን በሃላፊዎች መካከል አለመግባባት ፈጠረ። ባለፈው ሳምንት ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ የተደረጉ አራት ምክትል ፕሬዚደንቶች በዚሁ ተመላሽ በማይሆን የብድር መጠን ከባንኩ ፕሬዚደንት ጋር ባለመስማማታቸው ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ ምክንያት መሆኑን አዲስ ፎርቹን ጋዜጣ ዘግቧል። አዲሱ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚደንት አቶ ጌታሁን ናና የባንኩ የተበላሸ ብድር (nonperforming loans) መጠን ወደ 50 በመቶ ...
Read More »ለኢትዮጵያ የሚሰጠው የብድርና የእርዳታ ፍሰት እየቀነሰ እንደሆነ ተገለጸ
ኢሳት (ግንቦት 2 ፥ 2009) የኢትዮጵያ መንግስት ከተለያዩ አለም አቀፍ ሃገራትና አበዳሪ አካላት የሚያገኘው የብድርና የእርዳታ ፍሰት እየቀነሰ መምጣቱ ጉዳዩን የሚከታተለው የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን ረቡዕ አስታወቀ። በተለይ ያደጉ አገሮች በራሳቸው ችግር ምክንያት ሲያደርጉ የቆዩትን የፋይናንስ ድጋፍ እያቋረጡ መሆኑን የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ጌታቸው አዳም ለሪፖርተር ጋዜጣ ገልጸዋል። የብድርና የእርዳታ ፍሰቱ መቀነስ ከአጠቃላይ ወጪ አንጻር ተጽዕኖ ይኖረዋል ያሉት ሃላፊው ...
Read More »ለምግብ እርዳታ የተጋለጡ ሰዎች ቁጥር በድጋሚ ጭማሪ ያሳያል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተመድ ገለጸ
ኢሳት (ግንቦት 2 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ለአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ የተጋለጡ ሰዎች ቁጥር በድጋሚ ጭማሪን ያሳያል ተብሎ እንደሚጠበቅ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገለጸ። በቅርቡ መንግስትና ድርጅቱ ባወጡት የተረጂዎች ቁጥር መረጃ 5.6 ሚሊዮን አካባቢ የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ተረጂዎች በ2.2 ሚሊዮን በማደግ 7.8 ሚሊዮን መድረሱ ይፋ ተደርጓል። የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ለእርዳታ ጥሪ እየሰጠ ያለው ምላሽ አነስተኛ መሆንና በድርቁ በተጎዱ አካባቢዎች በበልግ ወቅት ...
Read More »የማላዊ መንግስትና የኢትዮጵያ አየር መንገድ የማላዊ አየር መንገድን በሽርክና ለማስተዳደር ያደረጉት ስምምነት ተቃውሞ ቀረበበት
ኢሳት (ግንቦት 2 ፥ 2009) በቅርቡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከማላዊ መንግስት ጋር የማላዊን አየር መንገድ በሽርክና ለማስተዳደር ያደረጉት ስምምነት በማላዊ የፓርላማ አባላት ዘንድ ተቃውሞ ቀረበበት። በሃገሪቱ ፓርላማ ተሰሚ እንደሆኑ የሚነገርላቸው የፓርላማ አባሏ ጁሊያን ሉንጉዚ የሃገራቸው መንግስት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ያደረገው ስምምነት ማላዊን የሚጠቅም አይደለም በማለት ውሉ መጣራት እንዲካሄድበት ጥያቄ ማቅረባቸውን ኒያሳ ታይምስ የተሰኘ የሃገሪቱ ጋዜጣ ዘግቧል። የማላዊ ኮንግረስ ፓርቲ ...
Read More »አቶ ፈቃደ ሸዋቀና ባደረባቸው ህመም ከዚህ አለም በሞት ተለዩ
ኢሳት (ግንቦት 2 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ከፍተኛ ተሳትፎ በማድረግ የሚታወቁትና የቀድሞ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር አቶ ፈቃደ ሸዋቀና ባደረባቸው ድንገተኛ ህምም ማክሰኞ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ። ላለፉት 23 አመታት በዚህ በአሜሪካ በስደት ይኖሩ የነበሩት አቶ ፈቃደ የኢህአዴግን ስልጣን መያዝ ተከትሎ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከተባረሩ 42 መምህራን አንዱ እንደነበሩ የህይወት ታሪካቸው ያመለክታል። በዚህ በአሜሪካ በነበሩበት ረጅም ጊዚያቶች አቶ ፈቀደ ...
Read More »