ኢሳት (ግንቦት 7 ፥ 2009) የፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ በሌሎች የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ (ኦፌኮ) አባላት ላይ ሲሰጥ የነበረን የመጀመሪያ ዙር ብይን ለሁለተኛ ጊዜ አራዘመ። ፍርድ ቤት ተከሳሾቹ የቀረበባቸውን ክስ ይከላከሉ ወይም በነጻ ይሰናበቱ የሚል ብይን ሰኞ ያስተላልፋል ተብሎ ቢጠበቅም ለግንቦት መጨረሻ ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጠቱን አዲስ ስታንዳርድ መጽሄት ዘግቧል። አቃቤ ህግ በአቶ በቀለ ገርባ ላይ አቀርበዋለሁ ያለው ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የግብፅ መንግስት የአባይ ወንዝን አጠቃቀም በተመለከተ በዩጋንዳ ምክክር እንዲካሄድ ጥያቄ አቀረበ
ኢሳት (ግንቦት 7 ፥ 2009) የግብፅ መንግስት በአባይ ወንዝ አጠቃቀም ላይ ከሰባት አመት በፊት አቅርቦ የነበረው ሃሳብ በዩጋንዳ ዳግም ምክክር እንዲካሄደበት ጥያቄን አቀረበ። ግብፅ ያቀረበችውን ይህንኑ ጥያቄ ተከትሎ የዩጋንዳው ፕሬዚደንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ በናይል ምክር ቤት አባላት ዘንድ በፕሬዚደንቶች ደረጃ በቀጣዩ ሳምንት ምክክር እንዲካሄድ ጥሪ ማቅረባቸው ታውቋል። ይሁንና ኢትዮጵያ በግብፅ የቀረበውን ሃሳብ በአግባቡ ለመመልከት ጊዜ ያስፈልገኛል በማለት የውይይቱ ቀን እንዲፈጸም ጥያቄ ...
Read More »180ሺ የእጅ ኮምፒውተሮች (ታብሌቶች) እንዲገቡ የተካሄደው የግዢ ጨረታ ውዝግብ ማስነሳቱ ተገለጸ
ኢሳት (ግንቦት 7 ፥ 2009) መንግስት ለቀጣዩ አመት በሃገሪቱ ለሚካሄደው የህዝብና ቤት ቆጠራ 180ሺ የእጅ ኮምፒውተሮች (ታብሌቶች) እንዲገቡ ያካሄደው የግዢ ጨረታ ውዝግብ ማስነሳቱ ተገለጸ። የመንግስት ግዢዎችና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ሌኖቮ የተሰኘውን የቻይና ኩባንያ በተለያዩ መንገዶች በመገምገም ለጨረታው ተሳታፊ እንዳይሆን ቢወሰንም የኤጀንሲው የቅሬታ ሰሚ ቦርድ ግን ውሳኒው እንዲቀለበስ ማድረጉ ይታወሳል። አንድ ቢሊዮን ብር ወጪ ይደረግበታል የተባለው የኮምፒውተሮች ግዢ ከሌሎች አምስት ኩባንያዎች ...
Read More »በባህርዳር የደረሰውን ፍንዳታ ተከትሎ የፖሊስ አመራሮች ከሃላፊነት ተነሱ
ግንቦት ፯ ( አባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በባህርዳር ከተማ የደረሰውን ተደጋጋሚ የቦንብ ጥቃት መንስኤና የድርጊቱን ፈጻሚዎች ለመያዝ ባለመቻላቸው የተገመገሙት የባህርዳር ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር ውበቱ አለን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ፖሊሶች ከደረጃ ዝቅ እንዲሉ ተደርጓል። በተባረሩ አዛዦች ቦታ የሚተኩት አዲሶቹ አዛዦች፣ ነባሩ አመራር ሊደርስበት ያልቻለውን ህዋስ አጥንተው እንዲደርሱበት ልዩ ትእዛዝ የተሰጣቸው ሲሆን፣ ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ ደግሞ ...
Read More »ከ40 በላይ ወታደሮችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ ጎንደር አቅጣጫ ማምራታቸው ታወቀ
ግንቦት ፯ ( አባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወደ ሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የሚደረገውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ እየጨመረ ሲሆን፣ ዛሬም ከ40 በላይ ወታደሮችን የጫኑ ኦራል ተሽከርካሪዎች በወልድያ አድርገው ወደ ጎንደር አቅጣጫ አምርተዋል። ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ በርካታ ቁጥር ያላቸው ተሽከርከሪዎች ወታደሮችን ወደ ሰሜን ሲያጓጉዙ ሰንብተዋል። በቅርቡ በርካታ ቁጥር ያላቸው አዳዲስ ታንኮች ተገዝተው ወደ አገር ውስጥ የገቡ ...
Read More »በአዲስ አበባ ቆሻሻ መድፊያ ቦታ ላይ የደረሰውን አሰቃቂ አደጋ ተከትሎ የተሰበሰበው ገንዘብ እስካሁን አለመከፋፈሉ በተፈናቃዮች ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ አስነስቷል።
ግንቦት ፯ ( አባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተለምዶ ቆሼ እየተባለ በሚጠራው የቆሻሻ መድፊያ ላይ በደረሰው ናዳ በርካታ ሰዎች መሞታቸውንና መፈናቀላቸውን ተከትሎ፣ ኢትዮጵያውያን የእርዳታ እጃቸውን በመዘርጋት በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ለተጎጂዎች ቢሰጡም፣ የባንክ ሂሳቡን የሚቆጣጠረው ገዢው ፓርቲ ገንዘቡን ለተጎጂዎች ባለማከፋፈሉ ማዘናቸውን የተጎጂ ቤተሰቦች ተናግረዋል። በቅርቡ የመስተዳድሩ ባለስልጣናት ለተጎጂዎች የሚሰጣቸውን የኮንዶሚኒየም ቤት እና ቦታ ቢያስታወቁም፣ እስካሁን ድረስ ቃል ...
Read More »ኢትዮጵያ ከቻይና መንግስት ብቻ 12.3 ቢሊዮን ዶላር በላይ እዳ አለባት
ግንቦት ፯ ( አባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢትዮጵያ ከቻይና ባንኮች ብቻ እኤአ ከ2000-2014 ከፍተኛ ብድር ከወሰዱ አምስት የአፍሪካ አገራት መካከል በሁለተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ በጆን ሆፕኪንስ ዩንቨርሲቲ የቻይና አፍሪካ ጥናት ማእከል አስታወቋል። ጥናቱ በተጠቀሱት ዓመታት ብቻ አንጎላ 21 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር ብድር ስትወስድ፣ ኢትዮጵያ በ12 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ሁለተኛ ብድር ወሳጅ አገር ተብላለች። ሱዳን ...
Read More »ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩና አቶ ዳንዔል ሺበሺ ከእስር እንዲፈቱ የሚጠይቅ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቀረቡ
ኢሳት (ግንቦት 4 ፥ 2009) ላለፉት አምስት ወራት ያለምንም የክስ ሂደት በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩና የቀድሞ የአንድነት አመራር አቶ ዳንዔል ሺበሺ ከእስር እንዲፈቱ የሚጠይቅ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቀረቡ። በቦሌ ክ/ከተማ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ በእስር ላይ የሚገኙት ሁለቱ አቤቱታ አቅራቢዎች በጥቅምት ወር በሃገሪቱ ተግባራዊ የተደረገውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ ለእስር መዳረጋቸው ይታወሳል። በማህበራዊ ድረገጾች የተለያዩ ጽሁፎችን ሲያቀርቡ የነበሩት ጋዜጠኛ ...
Read More »ቢቢሲ በስድስት ቋንቋዎች ለሚጀምረው የራዲዮ ስርጭት በኬኒያ አዲስ ቢሮ እንደሚከፍት አርብ አስታወቀ
ኢሳት ( ግንቦት 4 ፥ 2009) የብሪታኒያው የማሰራጫ ጣቢያ ቢቢሲ ሶስት የኢትዮጵያ ቋንቋዎችን ጨምሮ በስድስት ቋንቋዎች ለሚጀምረው የራዲዮ ስርጭት በኬኒያ አዲስ ቢሮ እንደሚከፍት አርብ አስታወቀ። በኬንያ መዲና ናይሮቤ ለሚከፈተው ለዚሁ ቢሮ 10 ሚሊዮን ዶላር በጀት ተመድቧል። ስቱዲዮው ለ250 ሰዎች የስራ እድልን እንደሚፈጥር የቢቢሲ ተወካዮች ገልጸዋል። የብሪታኒያ መንግስት የማሰራጫ ጣቢያው ለሚጀምረው አዲስ ስርጭት በየአመቱ 85 ሚሊዮን ፓውንድ ስተርሊንግ እንደሚመደብ ባለፈው አመት ...
Read More »በቱርኩ ጉለን ንቅናቄ ተቋቁመዋል የተባሉ ስድስት ትምህርት ቤቶች ማሪፍ ፋውንዴሽን ለተሰኘ የቱርክ መንግስታዊ ተቋም ተላልፈው ተሰጡ
ኢሳት ( ግንቦት 4 ፥ 2009) በኢትዮጵያ በቱርኩ ጉለን ንቅናቄ ተቋቁመዋል የተባሉ ስድስት ትምህርት ቤቶች ማሪፍ ፋውንዴሽን ለተሰኘ የሃገሪቱ መንግስታዊ ተቋም ተላልፈው ተሰጡ። ትምህርት ቤቶቹን የመረከብ ሂደት ከወራት በፊት የኢትዮጵያ መንግስት ትምህርት ቤቶቹን አስተላልፎ ለመስጠት የወሰነውን ውሳኔ ተከትሎ የተካሄደ መሆኑ የፋውንዴሽኑ ተወካይ አደም ኮክ ለቱርኩ ዜና አገልግሎት (አናዱሉ) ገልጸዋል። ባለፈው አመት በቱርክ የተካሄደውን የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተከትሎ የቱርክ ባለስልጣናት የጉለን ...
Read More »