ግንቦት ፲ ( አሥር ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለአንድ ሳምንት ያክል የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ከፍተኛ ገንዘብ በማውጣት ኢሳት ከአየር ላይ እንዲወርድ ለማድረግ የቻለ ቢሆንም፣ አስተዳዳሩ ባደረው ከፍተኛ ጥርት ወደ አየር ለመመለስ ችሎአል። ሰሞኑን ሲደረግ የነበረው ሙከራ በተሳካ ሁኔታ የተጠናቀቀ ሲሆን፣ በአሁኑ ሰአት ኢሳት ሙሉ በሙሉ የ24 ሰአት አገልግሎቱን ጀምሯል። ከ8 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን አስቸኳይ የምግብ እርዳታ በሚፈልጉበት በዚህ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በዮናታን ተስፋዬ ላይ የተላለፈው የጥፋተኝነት ብይን “አሳፋሪና በኢትዮጵያ የፍትህ መቀበርን” የሚያሳይ ነው ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል ተቃውሞ አቀረበ
ኢሳት (ግንቦት 9 ፥ 2009) የፌዴራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ማክሰኞ በቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር ላይ ያስተላለፈውን የጥፋተኝነት ብይን “አሳፋሪና በኢትዮጵያ የፍትህ መቀበርን” የሚያሳይ ዕርምጃ ነው ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል ተቃውሞ አቀረበ። መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ በሃገሪቱ ተግባራዊ ተደርጎ የሚገኘው የሽብርተኛ ወንጀል ህግ በመንግስት ላይ ትችት የሚያቀርቡ ሰዎች የሚደርስባቸውን በደል ማሳያ መሆኑንም በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣው መግለጫ ...
Read More »በሶማሌ ክልል የተከሰተው የድርቅ አደጋ ወደረሃብ ሊለወጥ ይችላል ተባለ
ኢሳት (ግንቦት 9 ፥ 2009) በኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል እየተባባሰ ያለው የድርቅ አደጋ ወደ ረሃብ ሊለወጥ እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አሳሰበ። ካለፈው ወር ጀምሮ በክልሉ መጣል የነበረበት የበልግ ዝናብ በአብዛኛው ባለመጣሉ ምክንያት በአካባቢው ጉዳትን እያደረሰ ያለው የድርቅ አደጋ በመባባስ ላይ መሆኑን በድርጅቱ ስር የሚገኘው የረሃብ ቅድመ ትንበያ መምሪያ ገልጿል። ይኸው የድርቅ አደጋ ወደ ረሃብ ለመድረስ አንድ ደረጃ ብቻ ወደሚቀረው ደረጃ አራት ...
Read More »70 ሚሊዮን የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን የኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎት እንደማያገኙ ተገለጸ
ኢሳት (ግንቦት 9 ፥ 2009) ኢትዮጵያ ካላት አጠቃላይ ህዝብ መካከል እስከ 70 ሚሊዮን አካባቢ የሚሆነው የኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎት እንደማያገኝ የውሃ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር ይፋ አደረገ። በአሁኑ ወቅት የኤሌክትሪክ አገልግሎቱን ለማስፋፋት መንግስት እየመደበ ያለው አንድ ቢሊዮን ብር አካባቢ በጀት እቅዱን ለማሳካት እንዳላስቻለው የሚኒስቴሩን የ10 ወራት ሪፖርት ለፓርላማ ያቀረቡት ሚኒስትሩ ስለሺ በቀለ መግለጻቸውን ሪፖርተር ዘግቧል። “ከ60 እስከ 70 ሚሊዮን ህዝብ በገጠር በጨለማ ...
Read More »ባለፉት 9 ወራት የተገኘው የውጭ ምንዛሪ ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ100 ሚሊዮን ዶላር አካባቢ ቅናሽ ማሳየቱ ተገለጸ
ኢሳት (ግንቦት 9 ፥ 2009) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ያገኘው የውጭ ምንዛሪ ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ100 ሚሊዮን ዶላር አካባቢ ቅናሽ ማሳየቱ ተገለጸ። ባንኩ በአጠቃላይ በአመቱ ለማግኘት ያቀደው የውጭ ምንዛሪ ከታቀደው በታች እንደሚሆን የተሰጋ ሲሆን፣ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተገኘው ወደ 3.3 ቢሊዮን ዶላር አካባቢ ከባለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር በ100 ሚሊዮን ዶላር መቀነሱን አዲስ ፎርቹን ጋዜጣ ዘግቧል። ...
Read More »ኢህአዴግ በደንብ አስከባሪ ስም ያሰለጠናቸውን ከ1700 በላይ ሰዎች ሊያስመርቅ ነው
ግንቦት ፱ ( ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢህአዴግ የተለያዩ መረጃ የመሰብሰብ ስራዎችን እንዲሰሩለት ለወራት በጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ሲያሰለጥናቸው የነበሩትን ከ1700 በላይ ሰልጣኞች ሰሞኑን ያስመርቃል። ሰልጣኞቹ ከሁሉም የአዲስ አበባ ወረዳዎች የተውጣጡ ሲሆን፣ በመጀመሪያው ዙር ከገቡት 2 ሺ ሰልጣኞች መካከል 300 የሚሆኑት የተቃዋሚዎች አስተሳሰብ አለባችሁ በሚል ተገምግመው እንዲባረሩ ተደርጓል። በስልጠናው ወቅት የአገሪቱን ችግር እያነሱ ጥያቄዎችን ሲያቀርቡ የነበሩ ሰዎች፣ ...
Read More »በሜቴክ የሚሰራው የያዩ ማዳበሪያ ፋብሪካ ከመንግስት ከ4. 4 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ ክፍያ ጠየቀ
ግንቦት ፱ ( ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከ5 ዓመታት በፊት ተጀምሮ በ2008 ዓም ይጠናቀቃል ተብሎ የተጀመረውና በአሁኑ ሰዓት ከ35 በመቶ ያልበለጠ ግንባታ ያካሄደው እንዲሁም ከተፈጥሮ ውድመት ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ተቃውሞ ሲቅርብበት የቆየው ያዩ የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ በመጀመሪያ የተያዘለት የ9 ቢሊዮን 600 ሺ ብር በጀት እንደማይበቃው ግንባታውን በሚያካሂደው በመከላከያ ኢንጂነሪንግ በኩል ጥያቄ አቅርቧል። ኩባንያው ተጨማሪ 4 ቢሊዮን ...
Read More »አርበኞች ግንቦት7 ተጨማሪ ጥቃቶችን መፈጸሙን አስታወቀ
ግንቦት ፱ ( ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ግንባሩ ለኢሳት በላከው መረጃ እንደገለጸው ግንቦት 7 ከሌሊቱ 8 ሰአት ከ55 ደቂቃ ላይ ሲሆን በደቡብ ጎንደር ዞን በሊቦከምከም ወረዳ በጣራ ገዳም አካባቢ በነበሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ ድንገተኛ ጥቃት በመፈም ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል። ጦሩ በተጠቀሰው ቦታ ላይ በአካባቢው ማህበረሰብ ላይ ከፍተኛ ስቃይ ሲፈጽም እንደነበር ድርጅቱ ገልጿል። የንቅናቄው ታጋዮች ወደ ...
Read More »ዮናታን ተስፋዬ በፌስቡክ ላይ በመጻፉ በአሸባሪነት መከሰሱን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አወገዘ
ግንቦት ፱ ( ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት የሆነው አምነስቲ ኢንተርናሽናል የቀድሞው የሰማያዊ ፓርቲ ሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ ዮናታን ተስፋዬ መንግስትን በመተቸቱ ብቻ በሽብር ክስ መከሰሱን አውግዟል። ባለፈው ዓመት በኢትዮጵያ የተነሳውን ሕዝባዊ እምቢተኝነት ተከትሎ የመንግስት ታጣቂዎች በሰላማዊ ዜጎች ላይ ከቅም በላይ ሃይል መጠቀማቸውን በማህበራዊ ድረገጾች ማውገዙ ሊያስከስሰው አይገባም ብሏል። ወጣት ዮናታን ተስፋዬ በአንድ ወቅት ...
Read More »አልሸባብ ሂራን በሚገኘው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሰራዊት ላይ ጥቃት አደረሰ
ግንቦት ፱ ( ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ሰላም አስከባሪ ጦር አሜሶም ስር በሶማሊያ በተሰማራው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ላይ አሸባሪው አልሸባብ ጥቃት ፈጸመ። ረቡእ እለት በሂራን ግዛት በሃላጋን ከተማ በሁለቱም መሃከል በከባድ መሳሪያ የታገዘ ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ ተደርጓል። እስካሁን በግጭቱ ምን ያህል ጉዳት እንደደረሰ ማወቅ አልተቻለም። አልሸባብ በራሱ መገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ ወታደራዊ ቤዝ ...
Read More »