.የኢሳት አማርኛ ዜና

ገዚው ፓርቲ የአውሮፓ ፓርላማ በኢትዮጵያ ላይ ያወጣውን መግለጫ ተቃወመ

ግንቦት ፲፩ ( አሥራ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአውሮፓ ፓርላማ ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር ዶ.ር መረራ ጉዲና ከእስር እንዲፈቱና የቀረበባቸው ክስ ውድቅ እንዲሆን፣ በዶ/ር ብርሃኑ ነጋና አቶ ጃዋር ሙሃመድ ላይ የቀረበው ክስ እንዲነሳ እንዲሁም ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች ከእስር እንዲፈቱ፣ በቅርቡ በኦሮምያና በሌሎችም የአገሪቱ አካባቢዎች የተፈጸሙ ግድያዎች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሚመራው ገለልተኛ ቡድን እንዲጣራ ...

Read More »

የሶስት ልጆች እናት የሆኑት ወ/ሮ ነቢቡ በ3ኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው በፍትህ እጦት እየተሰቃዩ ነው

ግንቦት ፲፩ ( አሥራ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ምንጮች እንደገለጹት የ3 ልጆች እናት የሆኑት ወ/ሮ ነቢቡ ደሳለኝ ላለፉት 3 ወራት በ3ኛ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ታስረው እየተሰቃዩ ሲሆን፣ ሁለት ጊዜ ፍርድ ቤት ቢቀርቡም መልስ አለማግኘታቸውን ምንጮች ገልጸዋል። ወ/ሮ ነቢቡ በአሸባሪነት እንደምትከሰስ የተነገራቸው ቢሆንም፣ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ ግን ምንም የክስ ቻርጅ አልቀረበባቸውም። በመሃሉ በፍትህ እጦት እርሳቸውና ልጆቻቸው ለከፍተኛ ...

Read More »

ባለፈው ሳምንት ከአርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ጋር ቃለ ምልልስ ካደረገ በኋላ ፕሮግራሙ በጣቢያው እንዳይተላለፍ የታገደበት የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ሥራውን በገዛ ፈቃዱ መልቀቁን አስታወቀ።

ግንቦት ፲፩ ( አሥራ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ጋዜጠኛ ብሩክ እንዳለ ዛሬ በፌስ ቡክ ገጹ ላለፉት አራት ዓመታት ከኢቢሲ ጋር ደጉንም መልካሙን ግዜ መካፈሉን በመጥቀስ፤ “ሰሞኑን ከቴዲ አፍሮ ጉዳይ ጋር ተያይዞ በተከሰተው ነገር ግን ከህሊናዬ ጋር እየታገልኩ ልቀጥል አልችልም”ብሏል። “ጉዳዩ እንድን የኪነጥበብ ሰው ማቅረብና ያለመቅረብ ጉዳይ ብቻ አይደለም”ያለው ጋዜጠኛ ብሩክ፤ ነገሩን የጋዜጠኝነትን ልዕልና የሚጋፋ ሆኖ ስላገኘውና ...

Read More »

አለም አቀፍ የፕሬስ ተቋም የአመቱን የፕሬስ ነጻነት ሽልማት ለጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ሰጠ

ኢሳት (ግንቦት 10 ፥ 2009) አለም አቀፍ የፕሬስ ተቋም የአመቱ የፕሬስ ነጻነት ጀግና ሽልማቱን በዛሬው ዕለት ለጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ሰጠ። ሽልማቱን ጋዜጠኛ መስፍን ነጋሽ ጀርመን ሃምቡርግ ከተማ ተገኝቶ ተቀብሏል።  አለም አቀፉ የፕሬስ ኢንስቲቲዩት 69ኛው የፕሬስ ነጻነት ጀግና ሽልማት በጀርመን ሃምቡርግ ከተማ በሰጠበት ወቅት፣ ኮፐንሃገን ዴንማርክ የሚገኘው ኢንተርናሽናል ሚዲያ ሪፖርት ተቋም ተባባሪ መሆኑም ተመልክቷል። ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ባለፉት 2ሺ ቀናት እኤኣ ...

Read More »

የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻነት ግንባት (ኦብነግ) እና አርበኞች ግንቦት 7 በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራረሙ

ኢሳት (ግንቦት 10 ፥ 2009) የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻነት ግንባት (ኦብነግ) እና አርበኞች ግንቦት 7 በጋራ ለመስራት ተስማሙ። በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች በጋራ ለመታገልና ከሌሎች የኢትዮጵያ የለውጥ ሃይላት ጋር ለመተባበር መስማማታቸውን ድርጅቶቹ ጀርመን ፍራንክፈርት ባወጡት የጋራ መግለጫ አስታውቀዋል።  የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ) እና አርበኞች ግንቦት 7 እኤአ ከሜይ 15 እስከ ሜይ 17 በጀርመን ፍራንክፈርት ለሶስት ...

Read More »

ዶ/ር መረራ ጉዲና በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀቁ የአውሮፓ ህብረት ጥሪ አቀረበ

ኢሳት (ግንቦት 10 ፥ 2009) የአውሮፓ ህብረት በእስር ላይ የሚገኙት ዶ/ር መረራ ጉዲና የተመሰረተባቸው ክስ ውድቅ ተደርጎ በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀቁ ጥሪ ቀረበ። በኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ ሪፖርትን በተመለከተ መግለጫ ያወጣው የአውሮፓ ፓርላማ በሃገሪቱና በኦሮሚያ ክልል ከተካሄደው ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተገናኘ በመቶዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው ግድያ በገለልተኛ አካል ምርመራ እንዲካሄድበት አሳስቧል። በእስር ላይ የሚገኙት ዶ/ር መረራ ጉዲና ከወራት በፊት በህብረቱ ...

Read More »

በጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ ግንባታ ምክንያት የተፈናቀሉ አርሶ አደሮች ምትክ ቦታ አላገኙም ተባለ

ኢሳት (ግንቦት 10 ፥ 2009) በአማራ ክልል ለጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ ግንባታ ከቀያቸው የተፈናቀሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ አርሶ አደሮች ለአመታት ምትክ ቦታ አለማግኘታቸው ተገለጸ። ለፋብሪካው ግንባታ ተብሎ ከመኖሪያ ይዞታቸው እንዲፈናቀሉ ከተደረጉት 213 አርሶ አደሮች መካከል 11 ዱ ብቻ ምትክ ቦታ እንደተሰጣቸው የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ሃሙስ ዘግበዋል። የስኳር ፋብሪካው ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን በበኩሉ በፕሮጄክቱ ምክንያት ተፈናቅለው ካሳ ይገባቸዋል ከተባሉ ሁሉ ...

Read More »

ግብፅ ሱዳንና ኢትዮጵያ በአባይ ግድብ ግንባታ ዙሪያ በባለሙያዎች ደረጃ ሲያካሄዱ የነበረው ውይይት ባለመግባባት ተበተነ

ኢሳት (ግንቦት 10 ፥ 2009) ኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን ለ14ኛ ጊዜ በአባይ ግድብ ግንባታ ዙሪያ በባለሙያዎች ደረጃ ሲያካሄዱ የነበረው ውይይት ባለመግባባት ተበተነ። የሶስቱ ሃገራት ተወካዮች ግድቡ በታችኛው ተፋሰስ ሃገራት ላይ በሚኖረው ተፅዕኖ ዙሪያ በአዲስ አበባ በመሰባሰብ የሁለት ቀን ምክክር ቢያደርጉም፣ 14ኛ ዙር ውይይት ያለውጤት መጠናቀቁን የግብፅ ባለስልጣናት ይፋ ማደረጋቸውን ሚድል ኢስት ሞኒተር የተሰኘ ጋዜጣ ሃሙስ ዘግቧል። ኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን ...

Read More »

አርበኞች ግንቦት7 እና ኦብነግ በጋራ ለመታገል ተስማሙ

ግንቦት ፲ ( አሥር ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአርበኞች ግንቦት7 የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄና የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጭ ግንባር በጋራ ባወጡት መግለጫ፣ ከግንቦት 7 እስከ ግንቦት9 ቀን 2009 ዓም በፍራንክፈርት ከተማ፣ በሁለቱም ድርጅቶች ተወካዮች አማካኝነት ባደረጉት ስብሰባ የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝና የኢትዮጵያ ህዝብ ሰቆቃና ስቃይ እንዲያበቃ በጋራ ለመታገል፣ ሌሎች ዲሞክራሲ ሃይሎችን በማሳተፍ የኢትዮጵያ ህዝብ አማራጭ ሃይል እንዲያገኝ በግንባር ቀደምትነት ለመታገል ...

Read More »

በዶ/ር ቴዶዎድሮስ አድሃኖም ላይ የሚቀርበው ተቃውሞ ጨምሯል

ግንቦት ፲ ( አሥር ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ውስጥ በጤና ጥበቃ እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ያገለገሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ ገዢው ፓርቲ፣ ታላላቅ አለማቀፍ ሃብታሞች የሚያፈሱትን የገንዘብ ድጋፍ እንዲሁም የአፍሪካ ህብረትን እርዳታ በመተማመን የአለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ለመመረጥ ከፍተኛ ዘመቻ እያካሄዱ ሲሆን ፣ በተቃራኒው ደግሞ በአገዛዙ ከፍተኛ በደል የደረሰባቸው ኢትዮጵያውያን የግለሰቡን መመረጥ አጥብቀው በመቃወም ...

Read More »