ግንቦት ፳፪ ( ሃያ ሁለት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቅርቡ ከኢትዮጵያ መሬት ተቆርሶ ለሱዳን ለመስጠት ከ12 ዓመታት በፊት የተጀመረው ድርድር ተግባራዊነት እውን ሊሆን ጫፍ መድረሱን ተከትሎ የሱዳን የመገናኛ ብዙሃን ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥተው እየዘገቡት ሲሆን፣ አሁን ደግሞ ገበሬዎቹ የሚሰጠን መሬት ትንሽ ነው በማለት እያማረሩ መሆኑን የሱዳን ሚዲያዎች እየዘገቡ ነው። በገዳሪፍ አካባቢ የሚኖሩ የሱዳን ገበሬዎች በቅርቡ የግዛቱ አስተዳዳሪ የሆኑት ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ለኢትዮጵያ ጉልህ አስተዋጽዖ ያደረጉ ኢትዮጵያውያን ሽልማት ተበረከተላቸው
ኢሳት (ግንቦት 21: 2009) ለኢትዮጵያ ሃገራቸው ጉልህ አስተዋጽዖ ያደረጉ 8 ታዋቂ ኢትዮጵያውያን መቀመጫውን በዚሁ በአሜሪካ ሃገር ባደረገ ተቋም ሽልማት ተበረከተላቸው። ማህበረ ጊወራን ዘረ ኢትዮጵያ ወይም /ሲድ/ የተባለው ይኸው ተቋም ላለፉት 25 አመታት ለሃገራቸው ጉልህ አስተዋጽዖ ያደረጉ ኢትዮጵያውያንን በመሸለም ይታወቃል። በሜሪላንድ ግዛት ኮሌጅ ፓርክ ዕሁድ ግንቦት 20/2019 ከተሸለሙት ስምንቱ ታዋቂ ኢትዮጵያውን መካከል አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን እና የትዝታው ንጉስ መሃመድ አህመድ ይገኙበታል። ...
Read More »በህይወት መኖራቸው ያልታወቁት የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ አቶ ልዑል ገብረማሪያም ከስራቸው እንዲሰናበቱ ተወሰነ
ኢሳት (ግንቦት 21: 2009) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በህይወት ይኑሩ አይኑሩ ያልታወቀ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ አቶ ልዑል ገብረማሪያም ከስራቸው እንዲሰናበቱ ወሰነ። ለበርካታ አመታት በፍትህ ስርዓት ውስጥ ያገለገሉት አቶ ልዑል ላለፉት ስምንት ወራት ውስጥ በስራ ገበታቸው ላይ ያልተገኙ ሲሆን፣ ቤተሰቦቻቸውም ሆኑ የመስሪያ ቤታቸው ባልደርቦች ዳኛው ያሉበትን ሁኔታ እንደማያውቁ ለፓርላማው የቀረበን ሪፖርት ዋቢ በማድረግ ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል። የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ...
Read More »የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽንን በመስራችነትና በዋና ስራ አስፈጻሚነት ያገለገሉት ዶ/ር ጌታቸው በትሩ በገዛ ፈቃዳቸው ስራ ለቀቁ
ኢሳት (ግንቦት 21: 2009) በቅርቡ የብድር መጠኑ ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ ደርሶ የነበረውን የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽንን በመስራችነትና በዋና ስራ አስፈጻሚነት ለ10 አመታት ያገለገሉት ዶ/ር ጌታቸው በትሩ በገዛ ፈቃዳቸው ስራ መልቀቃቸው ታውቋል። ሃላፊው ስራቸውን በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸው ቢረጋገጥም ምክንያቱ ግን በኮርፖሬሽኑም ሆነ በዶ/ር ጌታቸው አልተገለጸም። መንግስታዊ ተቋም በሃገሪቱ ሰፊ የባቡር መሰረተ ልማት ግንባታ ለማካሄድ ባቀደ ጊዜ ዶ/ር ጌታቸው ፕሮጄክቶችን በመቆጣጠርና ...
Read More »የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ እገታ የተፈጸመበትን አንድ ኢትዮጵያዊ ነጋዴ ማስለቀቁን ሰኞ አስታወቀ
ኢሳት (ግንቦት 21: 2009) የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ እገታ የተፈጸመበትን አንድ ኢትዮጵያዊ ነጋዴ ከእገታ ማስለቀቁን ሰኞ አስታወቀ። ስሙ ይፋ ባልተደረገው ኢትዮጵያዊ ነጋዴ ላይ እገታውን ፈጽመዋል የተባሉ ሶስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሚገኝ ኒውስ 24 የተሰኘ የሃገሪቱ ጋዜጣ ዘግቧል። ሶስቱ ግለሰቦች ኢትዮጵያዊ ነጋዴውን ከጆሃንስበርግ ከተማ በቅርቡ ርቀት ላይ ከሚገኘው የኦ አር ታምቦ (O R Tambo) አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የንግድ ...
Read More »በሳውዲ ህጋዊ የመኖሪያ ሰነድ የሌላቸው ኢትዮጵያውያን እጣ ፈንታ አልታወቀም
ኢሳት (ግንቦት 21: 2009) በሳውዲ አረቢያ ህጋዊ የመኖሪያ ሰነድ የሌላቸው ከ700 መቶ ሺ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን እጣ ፈንታ አለመታወቁ ተገለጸ። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሳውዲ አረቢያ ያለፈቃድ ይኖሩ የነበሩ 40ሺ ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ ከሳውዲ አረቢያ ህጋዊ የመውጫ ቪዛ አግኝተዋል ቢልም፣ ሌሎች ከ700 ሺ በላይ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ አደጋ እንደተጋረጠባቸው ለማወቅ ተችሏል። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ እነዚህ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ቢመለሱ ...
Read More »የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከታወጀ በሁዋላ በርካታ ዜጎች መገደላቸው ሰመጉ አስታወቀ
ግንቦት ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ጉባኤ የአሁኑ ሰብአዊ መብት ጉባኤ (ሰመጉ) ባወጣው 142ኛ ልዩ መግለጫ፣የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከታወጀ ከመስከረም28 ቀን 2009 ዓም ጀምሮ ከህግ አግባብ ውጭ በርካታ ዜጎች ተገድለዋል፣ ቆስለዋል፣ ተደብድበዋል፣ በመደበኛ እስር ቤቶችና ከመደበና እስር ቤቶች ውጭ በርካታ ሰዎች ለእስር ተዳርገዋል፣ የደረሱበትም የማይታወቁ በርካታ ናቸው ብሎአል። ሰመጉ ከህግ ...
Read More »የደህንነት ሃይሎች የባህርዳርን ጸጥታ መቆጣጠር ተስኖዋቸዋል ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ
ግንቦት ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በባህርዳር ከተማ የተለያዩ ጥቃቶች እንደሚፈጸሙ የሚገልጹት ነዋሪዎች፣የጥቃቱን ፈጻሚዎች ማንነት ለማወቅ አለመቻሉ ግራ አጋብቷቸዋል፡፡ የክልሉን ደህንነት እንቅስቃሴ በበላይነት የሚመራው የህውሃት ደህንነት ክፍል ጥቃቶችና አፈናዎችን መመከት አለመቻሉን የከተማዋ ነዋሪኦች ለክልሉ ወኪላችን ገልጸውላታል። ሰሞኑን በባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ላይ የተካሄዱትን ግድያዎችና አፈናዎች መመከት ያልቻለው የደህንነት ኃይሉ፣ ፖሊስ ወንጀሉን የፈጸሙትን ግለሰቦች መያዝ ...
Read More »የጎርፍ አደጋ በረሃብ የተጎዳውን ህዝብ ቁጥር እንዲጨምር ማድረጉን ተመድ አስታወቀ
ግንቦት ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባወጣው መረጃ በኢትዮጵያ ከ3 ሳምንት በፊት በኦሮምያ በምዕራብ ሃረርጌ በሃዊ ጉዲና ወረዳ እና በአርሲ ዞን ሰሩ እና ጮሌ ወረዳዎች የጣለው ዝናብ በርካታ ዜጎችን አፈናቅሏል። በምዕራብ ሃረርጌ ዞን በሃዊ ጉዲና ወረዳ 8 ሰዎች በጎርፍ አደጋ ሲሞቱ 5ቱ ደግሞ ቆስለዋል። 3 ሺ 179 የቀንድ ከብቶች አልቀዋል። በአርሲ ...
Read More »ጋዜጠኛ ፍቅረማርያም አያናው ከስራ ታገደ
ግንቦት ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአማራ ማስ ሚዲያ ውስጥ ጋዜጠኛ የሆነውና በድፍረት በሚሰነዝራቸው ትችቶች የሚታወቀው ጋዜጠኛ ፍቅረማርያም አያናው ከስራ መታገዱንና የመንግስትን ስም በማጥፋት ሊከሰስ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል። ጋዜጠኛ ፍቅረማርያም ከስራ መታገደኑን ወደ መስሪያ ቤት ሲገባ መከልከሉን ኢሳት ለማረጋገጥ ችሎአል። ፍቅርማርያም ጥልቅ ተሃድሶ በሚል በአማራ ክልል የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ለጋዜጠኞች በተዘጋጀ ዝግጅት ላይ፣ የህወሃትን ...
Read More »