ኢሳት (ግንቦት 23 ፥ 2009) በመላው ኢትዮጵያ ረቡዕ መሰጠት ከጀመረው የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ጋር በተያያዘ በሃገሪቱ ከማክሰኞ ምሽት ጀምሮ የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋረጠ። ብሄራዊ ፈተናው ተሰርቆ ሊሰራጭ እንደሚችል ስጋት መኖሩ ለአገልግሎቱ መቋረጥ ዋነኛ ምክንያት መሆኑን ኳርትዝ አፍሪካ የተሰኘ መጽሄት የተለያዩ አካላትን ዋቢ በማድረግ ረቡዕ ዘግቧል። በመዲናይቱ አዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች በበኩላቸው ችግሩ ረቡዕ ድረስ የዘለቀ መሆኑን በመግለፅ ላይ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአስተዳደር ነጻነት እንዲኖራቸው ፕሮፌሰር አድማሱ ጸጋዬ ጥሪ አቀረቡ
ኢሳት (ግንቦት 23 ፥ 2009) የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአስተዳደር ስርዓት ነጻነት እንዲኖረው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚደንት ፕሮፌሰር አድማጹ ጸጋዬ ጥሪ አቀረቡ። የመንግስት የፋይናንስ ህግ ማዕቀፎችም የተሰጠውን ተልዕኮ ለማስፋፋት እንቅፋት መሆናቸውን የዩኒቨርስቲው ፕሬዚደንት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መግለጻቸውን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ዩኒቨርስቲው በራሱ እቅድ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገራት በሚያከናውናቸው ፕሮግራሞች የሚሰበሰበው የውስጥ ገቢ ቢኖረውም የመንግስት የፋይናንስ ስርዓት ግን ዩኒቨርስቲው ...
Read More »የመን ወደ መፈራረስ እያመራች መሆኑን ተመድ ገለጸ
ኢሳት (ግንቦት 23 ፥ 2009) በእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ የምትገኘው የመን ሙሉ ለሙሉ ወደ መፈራረስ እያመራች መሆኗን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ። ሃገሪቱ ያጋጠማት የረሃብ አደጋና ዕልባት ማግኘት ያልቻለው የዕርስ በርስ ጦርነት የማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና የመንግስታዊ ተቋማት መፈራረስ አደጋ እንዲጋረጥባቸው ማድረጉን የድርጅቱ የሰብዓዊ ዕርዳታ ማስተባበሪያ ሃላፊዎች ይፋ ማድረጋቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። ለተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት የየመን ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክቶ ሪፖርተን ያቀረቡት የማስተባሪያ ...
Read More »በኢትዮጵያ ስላለው የሰብዓዊ መብት ቀውስ ልዩ ትኩረት እንዲሰጥ 11 አለም አቀፍ የሰብዓዊ ተቋማት የተመድ ሰብዓዊ መብት ምክርቤትን ጠየቁ
ኢሳት (ግንቦት 22 ፥ 2009) የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት በቀጣዩ ሳምንት በሚካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ በኢትዮጵያ ስላለው የሰብዓዊ መብት ቀውስ ልዩ ትኩረት እንዲሰጥ አለም አቀፍ ተቋማት ጠየቁ። በአለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ዙሪያ የሚሰሩ 11 ድርጅቶች የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች አጀንዳ ሆኖ እንዲቀርብ በጋራ ያቀረቡትን ጥያቄ ከምክር ቤቱ እንዲያስገቡ ሂውማን ራይትስ ዎች አስታውቋል። ፍሪደም ሃውስ፣ ኢንተርናሽናል ሰርቪስ ፎር ሂውማን ራይትስ፣ ሪፖርተርስ ...
Read More »የህወሃት መሪዎች የትግራይ ተወላጅ ያልሆነ ኢትዮጵያዊ በአለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ በሃላፊነት እንዲሰራ ድጋፍ እንደማያደርጉ ተገለጸ
ኢሳት (ግንቦት 22 ፥ 2009) በኢትዮጵያ የፖለቲካ ስልጣኑን የያዙት የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት መሪዎች የትግራይ ተወላጅ ያልሆነ ኢትዮጵያዊ በአለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ በሃላፊነት እንዲሰራ ድጋፍ እንደማያደርጉ አንድ ታዋቂ ኢትዮጵያዊ ገለጹ። በአፍሪካ ልማት ባንክ እስከ ምክትል ፕሬዚደንትነት ለ15 አመታት ያገለገሉት አንጋፋው ኢትዮጵያዊ አቶ ተካልኝ ገዳሙ “Republican on the Throne” በተባለውና ከአመታት በፊት ለንባብ ባቀረቡት መጽሃፋቸው እንደገለጹት ለአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚደንትነት ሳይወዳደሩ የቀሩት ...
Read More »አንድ የአሜሪካ ወታደራዊ ኩባንያ አውሮፕላን በሶማሊያ ሞቃዲሾ ተከሰከሰ
ኢሳት (ግንቦት 22 ፥ 2009) ንብረትነቱ የአንድ የአሜሪካ ወታደራዊ ኩባንያ የሆነ አውሮፕላን በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ ከተማ በሚገኘው የኤዴን አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ መከስከሱን ባለስልጣናት አስታወቁ። መነሻውን ከዩንጋንዳ አድርጓል የተባለው ይኸው ወታደራዊ አውሮፕላን አራት የምዕራባውያን ሃገራት ዜጎችን አሳፍሮ የነበረ ሲሆን፣ በመንገደኞች ላይ ጉዳት አለመድረሱን የቻይናው ዜና አገልግሎት ሺንሁአ ማክሰኞ ዘግቧል። ባንክሮፍት የሚባል ኩባንያ ንብረት የሆነው ወታደራዊ አውሮፕላኑ በአውሮፕላን ማረፊያው ለማረፍ ...
Read More »ሁሉን አሳታፊ የሆነ ብሄራዊ ምክር ለመመስረት ስምምነት መደረጉን በሲያትል በተካሄደው ጉባዔ ተመለከተ
ኢሳት (ግንቦት 22 ፥ 2009) የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ሃይሎችን እና የተለያዩ የፖለቲካ አመለካከት ያላቸውን በማስተባበር ሁሉንም አሳታፊ የሆነ ብሄራዊ ምክር ቤት ለመመስረት ስምምነት መደረጉን በሲያትል የተካሄደው ጉባዔ የአቋም መግለጫ አመለከተ። በአቋም መግለጫው እንደተመለከተው በኢትዮጵያ የተካሄውን ህዝባዊ እምቢተኝነት የበለጠ ማጠናከር ያልተቻለው ጠንካራ የተቃዋሚ ሃይሎች ህብረት ባለመኖሩ ነው። ስለሆነም፣ የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት ዘላቂ ሰላም የሰፈነባት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመፍጠር በሽግግርነት ሁሉን አሳታፊ ብሄራዊ ምክር ...
Read More »የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3.5 ሚሊዮን ዶላር ወደ ዱባይ አሸሽተዋል የተባሉ አንድ የውጭ ዜጋ በ25 አመት እስራት እንዲቀጡ ወሰነ
ኢሳት (ግንቦት 22 ፥ 2009) የፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተበደሩትን 3.5 ሚሊዮን ዶላር ወደ ዱባይ አሸሽተዋል ከተባሉ ሁለት ተከሳሾች መካከል ትውልደ ግብጻዊና የአሜሪካ ዜግነት ያላቸውን ግለሰብ በ25 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ማክሰኞ ወሰነ። ሁለተኛ ተከሳሽና በትውልድ ደቡብ አፍሪካዊ ሆነው የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ግለሰብ ደግሞ የመከላከያ ምስክር እንዲያቀርቡ ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የፍርድ ...
Read More »ሰመጉ “በኮማንድ ፖስቱ የታሰሩ” ዜጎች በእስር ቤት ውስጥ የደረሰባቸውን ስቃይ ይፋ አደረገ
ግንቦት ፳፪ ( ሃያ ሁለት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሰብአዊ መብት ጉባኤ በ142ኛ ልዩ መግለጫው ላይ እንደጠቀሰው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከታወጀ ከመስከረም 29 ቀን 2009 ዓም ጀምሮ ከ22 ሺ በላይ ሰዎች የታሰሩ ሲሆን፣ በተለያዩ እስር ቤቶች ውስጥ አሰቃቂ የሆኑ የቅጣት እርምጃዎች በእስረኞች ላይ እንደሚፈጸሙ ገልጿል። ሰመጉ ወታደራዊ ካምፖች ኮሌጆችና ትምህርት ቤቶች እስርቤት ሆነው ማገልገላቸውን ገልጾ፣ በተለይ በወታደራዊ ...
Read More »አርበኞች ግንቦት7 በአንድ የደህንነት አባል ላይ ጥቃት መፈጸሙን አስታወቀ
ግንቦት ፳፪ ( ሃያ ሁለት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ንቅናቄው ለኢሳት በላከው መግለጫ በደንቢያ ወረዳ ቆላድባ ከተማ ልዩ ስሙ ጎርጎራ ክፍል እየተባለ በሚጠራው ስፍራ ግንቦት21 ቀን 2009 ዓም ከምሽቱ አራት ሰዓት ላይ በአንድ የህወሃት የደህንነት አባል ላይ ጥቃት መፈጸሙን ገልጿል። በደንቢያ ወረዳ የህወሃት ሰላይ በመሆን በአካባቢው ህዝብ ላይ ለሚደርሰው ግድያ ፣ አፈናና እስር ዋና ተጠያቂ ነው ባለው ...
Read More »