ኢሳት (ግንቦት 24 ፥ 2009) መንግስት የኢንተርኔት አገልግሎት ማቋረጡን ተከትሎ የብሪታኒያ መንግስት ወደ ኢትዮጵያ መጓዝ የሚፈልጉ የሃገሪቱ ዜጎች አማራጭ የመገናኛ መንገዶችን እንዲጠቀሙ አሳሰበ። ከማክሰኞ ጀምሮ በኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን የገለጸው የብሪታኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ወደ ኢትዮጵያ የመጓዝ እቅድ ያላቸው ዜጎች የሞባይልና የመደበኛ ስልኮችን በአማራጭነት እንዲጠቀሙ ባሰራጨው የጉዞ ጥንቃቄ ማሳሰቢያው አመልክቷል። እስራትን ጨምሮ የድብደባና ሌሎች አደጋዎች የሚያጋጥማቸው ብሪታኒያውያን ለአገልግሎቱ ሲባል በተከፈተ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በነቀምትና ደምቢዶሎ የግንቦት20 ቲሸርት ሳይከፋፈል ቀረ
ግንቦት ፳፬ ( ሃያ አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢህአዴግ ግንቦት20ን ምክንያት በማድረግ ያዘጋጀውን ግንቦት 20 ቲሸርት ወለጋ ነቀምት ላይ ለመሸጥ ሙከራ ሲያደርግ ህዝቡ “ የደም ቲሸርት ነው ወይ የምንገዛው? “ በማለት ለመግዛት ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል። የህዝቡን ሁኔታ ያዩት ካድሬዎች፣ ህዝቡ ቲሸርቱን በነጻ እንዲወስድ ቢጠይቁም፣ “ የልጆቻችንን ደም አንለብስም፣ የተደረገብንን አንረሳም፣ ድርጊታችሁ የኦሮሞን ህዝብ እንደመናቅ፣ እንደመድፈር ይቆጠራል” ...
Read More »የኢንተርኔት አገልግሎት መታፈኑን ተከትሎ በርካታ መስሪያ ቤቶች ችግር አጋጥሟቸዋል
ግንቦት ፳፬ ( ሃያ አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አገራቀፍ ፈተናዎችን ምክንያት በማድረግ ባለፈው ማክሰኞ የተጀመረው የኢንተርኔት አፈና ዛሬም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን፣ ባንኮች፣ እና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ስራቸውን ለማከናወን ተቸግረዋል። የኢንተርኔት አገልግሎት የሚሰጡ ደርጅቶች እንዲሁም ኢንትርኔት በስልካቸው የሚጠቀሙ፣ ከውጭ አገራት ጋር ግንኙነት በመፍጠር የንግድ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ድርጅቶች ሁሉ ስራቸው እንደተስተጓጎለባቸው ወኪላችን ገልጿል። በተለያዩ የመንግስት ና የግል ...
Read More »በቆሸ ከደረሰው እልቂት ጋር በተያያዘ ድጋፍ ያላገኙ ቤተሰቦች መኖራቸውን የተጎጂ ቤተሰቦች ተናገሩ
ግንቦት ፳፬ ( ሃያ አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው መጋቢት ወር ላይ በአዲስ አበባ በተለምዶ ቆሸ እየተባለ በሚጠራው የቆሻሻ መድፊያ ቦታ ላይ ቆሻሻ ተንዶ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት ካጠፋ በሁዋላ፣ በመላው አለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ቁጥር ያለው የገንዘብ እርዳታ ለግሰዋል። የገንዘብ ድጋፉ ገዢው መንግስት በበላይነት በሚቆጣጠረው የባንክ አካውንት እንዲገባ ከተደረገ በሁዋላ፣ ገንዘቡ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ...
Read More »ከ40 በላይ ሰዎች በሰሃራ በረሃ መሞታቸው ታወቀ
ግንቦት ፳፬ ( ሃያ አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአለም አቀፉ ቀይ መስቀል ድርጅት ለቢቢሲ እንደገለጸው ከሆነ ሀምሳ የሚጠጉ ሰዎችን ይዞ በሳህራ በርሀ በመጓጓዝ ላይ የነበረ አንድ የጭነት ተሽከርካሪ አደጋ የደረሰበት በመሆኑ አርባ አራት ሰዎች በውሃ ጥም ህይወታቸው አልፏል። የተረፉት ስድስት ሰዎች ረጅም የእግር መንገድ በመጓዝ በኒጀር ዲንኮ የቀይ መስቀሉ መስሪያ ቤት መድረሳቸውን የመስሪያ ቤቱ ሰራተኛ ሲገልጹ ...
Read More »ለሱዳን የሚሰጠውን መሬት አስመልክቶ ኢትዮጵያውያን ተቃውሟቸውን እየገለጹ ነው
የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት የኢትዮጵያ ህዝብ ባላወቀውና ባልወሰነበት ሁኔታ ለሱዳን መሬት ለመስጠት መንቀሳቀሱ በእጅጉ እንዳበሳጫቸው ኢትዮጵያውያን ገልጸዋል። “እንዲህ አይነት መንግስት አይቼ አላውቅም፣ መንግስት ሊባል አይችልም፣ በአገር ላይ የሚሰሩት ስራ ሁሉ እጅግ የሚያሳዝን ነው፣ የኢትዮጵያ ወገን አይደሉም” በማለት አስተያየት የሰጡት አንድ የሰሜን ጎንደር ነዋሪ፤ ስርዓቱን ተባብረን እስካልገታነው ድረስ መዋረዳችን ይቀጥላል ብለዋል። ሌላው አስተያየት ሰጪ ደግሞ “ በኢትዮጵያ ‘አፈሮቿ ባህር ተሻግረው እንዳይሄዱ የወራሪዎቿን እግር ...
Read More »ከመቼውም ጊዜ በላይ ኢህአዴግ ውስጥ መናበብ ጠፍቷል ተባለ
ግንቦት ፳፫ ( ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢህአዴግ አባላት ለኢሳት የአዲስ አበባ ዘጋቢ እንደገለጹት፣ ኢህአዴግን በመሰረቱት አራት ድርጅቶች መካከል ያለው መናበብ፣ ከዚህ ቀደም ባልታየ መልኩ በመዳከሙ፣ አቅጣጫ ሰጥቶ የሚመራ አካል እየጠፋ ነው። በኢህአዴግ ታሪክ የአባላቱ መንፈስ በዚህ ደረጃ የወደቀበትን ጊዜ አናስታውስም የሚሉት አባሎቹ፣ ማእከላዊነት የሚባል ነገር በመጥፋቱ ሁሉም በራሱ የመሰለውን ውሳኔ እየሰጠ ነው ይላሉ። “አለመግባባቱ፣ ...
Read More »አገር አቀፍ ብሄራዊ ፈተናን ምክንያት በማድረግ በመላው ኢትዮጵያ ኢንተርኔት ተቋረጠ
ግንቦት ፳፫ ( ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ረቡዕ ለሚጀመረው ፈተና ከማክሰኞ ጀምሮ የኢንተርኔት አገልግሎት መቁዋረጡ በማህበራዊ ድረገጾች ተጠቃሚዎች ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ፈጥሯል። ቁጥራቸው 1.2 ሚሊዮን የሚሆኑ የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች ብሄራዊ ፈተናውን የሚወስዱ ሲሆን በተጨማሪም 288 ሽህ የ12ኛ ክፍል የዩንቨርሲቲ መሰናዶ ብሄራዊ ፈተናውን በቀጣይ ሳምንት እንደሚወስዱ ሪፖርቶች አመላክተዋል። የኢንተርኔት አገልግሎት ለ12 ሰዓታት ዝግ ሆነው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል። ከትናንት ...
Read More »ሱዳን የግብጽ የግብርና እና የእንሣት ተዋጽኦ ምርቶች ወደ አገሯ እንዳይገቡ እገዳ ጣለች
ግንቦት ፳፫ ( ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሱዳን መንግስት የካቢኔ አባላት የግብጽ የግብርና እና የእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶች ወደ አገራቸው እንዳይገባ ማገዳቸውን የሱዳን መንግስት ልሳን የሆነው ሱና የዜና አውታር ማክሰኞ እለት ዘገቧል። ካቢኔው አክሎም በቀጥታ ከጎረቤት ግብጽ በኩል ወደ ሱዳን የሚገቡ ማንኛውንም ምርቶች እንዳያስገቡ ለግል ባለሃብቶችም ማሳሰቢያ ሰጥቷል። በሱዳን እና በግብጽ መሃከል የተነሳው ውጥረት ከጊዜ ወደ ...
Read More »ለተረጂዎች ሲሰጥ የነበረ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ከሰኔ ወር ጀምሮ ሊያልቅ እንደሚችል ተመድ አሳሰበ
ኢሳት (ግንቦት 23 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ለአስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ ተጋልጠው የሚገኙ ከሰባት ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከቀጣዩ ሰኔ ወር ጀምሮ የሚቀርብላቸው የምግብ ድጋፍ አቅርቦት ሊያልቅ እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አሳሰበ። የተረጂዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣትና የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ለእርዳታ ጥሪው የሰጠው ምላሽ አነስተኛ መሆን የእርዳታ አቅርቦቱ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ማሳደሩን ድርጅቱ የድርቁን ሁኔታ አስመልክቶ ባወጣው አዲስ ሪፖርት ገልጿል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና መንግስት ...
Read More »